Get Mystery Box with random crypto!

*አትምጪ* አለመምጣትሽን ልቤ ይከጅለዋል ጠብቄሽ መቅረትሽን ውስጤ ይሽተዋል የመጣሽ እንደሆን 'መሄ | የስንኝ ቋጠሮ

*አትምጪ*
አለመምጣትሽን ልቤ ይከጅለዋል
ጠብቄሽ መቅረትሽን ውስጤ ይሽተዋል
የመጣሽ እንደሆን 'መሄድሽ ነው' እያልኩ ሰዓቱን እያየሁ
ከመቅረትሽ ይባስ በሃሳብ እዋኛለሁ
ናፍቆት ያጎበጠው፤ድካም የተጫነው ልብ እና አካሌን
መምጣትሽ አይደለም እቅፍሽም እንዲሁ መዳኛ 'ሚሆነው
በዛው መቅረትሽ ነው ከደዌ 'ሚያርቀው።
Ab
17/11/2014