Get Mystery Box with random crypto!

ሆያ ሆዬ ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣ ሆያ ሆዬ ስንል ያኔ በልጅነት፡፡ የሙልሙሉ ዳቦ የ | የስንኝ ቋጠሮ

ሆያ ሆዬ

ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ሆያ ሆዬ ስንል ያኔ በልጅነት፡፡
የሙልሙሉ ዳቦ የኩበቱ ሽታ፣
መቼም አይረሳም የቡሄ ትዝታ፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
የዚ ቤት ጌታ ጥርሰ በረዶ፣
"እንለው ነበረ"
ጥርሱ ግን ወላልቆ ቢሆንም ባዶ፡፡
ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ጆሮዬን ተሠማው የጅራፉ ጩኸት፣
ተሠማኝ ሙቀቱ የችቦውም እሳት፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
የዚ ቤት ጌታ የኢትዮጵያ አርበኛ፣
" እንለው ነበረ"
ለራሱም ቢያስፈልግ ጠባቂ ዘበኛ፡፡
ዳቦውም ይበላል ችቦው ይለኮሳል፣
ሆያ ሆዬ ተብሎ ቡሄ ይከበራል፡፡
እጅጉን ደነቀኝ ገረመኝ ሳስበው፣
ሆያ ሆዬ ማለት ራሡ ጥበብ ነው፡፡

Afe.Z.eth @gitmv