Get Mystery Box with random crypto!

*የማይድን...* ምን ብንታገል ከሆድ የማናወጣው በጊዜ ሂደት እንርሳው ብንል የማንረሳው ስንት ህ | የስንኝ ቋጠሮ

*የማይድን...*
ምን ብንታገል ከሆድ የማናወጣው
በጊዜ ሂደት እንርሳው ብንል የማንረሳው
ስንት ህመም አለን
ሰርክ የሚያደማን
'እህህ' ብለን የማይወጣልን
በሚመሽ እድሜ የማይመሽልን
እልፍ ህመም አለን
ከቀን እስከሌት ከዘመን ዘመን
ከጉያችን ስር 'ሚበረታብን።
Ab
07/11/2014