Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ~ ጽድቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የሰርጥ አድራሻ: @fenote_tsedek
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.62K
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ይህ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ቻናል ነው። እባካችሁን ይከታተሉን ለሌሎች ያጋሩ ።
#በጽድቅ_መንገድ_ላይ_ሕይወት_አለ።
#በጎዳናዋም_ሞት_የለም። ምሳሌ 12፥28
ሌሎችንም ይጋብዙ ➟ @fenote_tsedek
ለመልዕክት እና ለአስታያየት➟ @fenote_tsedekbot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-09 15:01:48 " ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነው. "
ያዕ 5:11


ሰው ቢጨክንብህ እግዚአብሔር ላንተ ይራራል፤ ሰው ተፈራርሞ ቢያድምብህ እግዚአብሔር ለጠላቶችህ ሳይሆን ላንተ ይወግናል፤ ሰው ቢፀየፍህ እግዚአብሔር በልቡ ያኖርሀል፤ ሰው ባያይህ እግዚአብሔር እንደ ዓይኑ ብሌን ይጠነቀቅልሃል፤ ብትከፋ እግዚአብሔር ደስታህ ይሆናል።

በትልቅ ውቅያኖስ ውስጥ አንዲት ጠብታ ደም " ጠብ " ብትል ያንን ሁሉ ውቅያኖስ ማደፍረስ ይቻላታል? አይቻላትም! ወዳጄ ኃጢያትህ እግዚአብሔር ለአንተ ያለውን ፍቅሩን ሳያደፈርስ ዛሬም ድንቅ ተአምራቱን የሚገልፅልህ ከዚህ የተነሳ ነው። የአንተም ኃጢአት መስራት ተስፋ ቆርጠህ ከቤቱ እስክትወጣ ከቃሉ መግቦት እስክትለይ ድረስ የሚያደርስህ አይደለም። የፍቅሩን ታላቅነት ቀምሰህ እንድትመጣ የሚያደርግህ እንጂ።

እግዚአብሔር ከእናት በላይ እንስፍስፍ ነው። በዚህ ቀን ይህን በድለሻል፣ በዚህ ቀን ይህን አጥፍተሻል ብሎ የክስ ዶሴ ይዞ ሊወነጅልሽ አይጠባበቅሽም።ልጄ ሆይ ነይ እያለ በፍቅሩ እየሳበሽ በምህረቱ እያቀፈሽ ከልቡ እየራራልሽ ይቀበልሻል።


ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.7K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 12:04:36 #ፍሬያማ_ቅርንጫፍ

አንድ ቅርንጫፍ ቅርንጫፍ የሚባለው ግንድ ሲኖር ወይም ከግንዱ ጋር የተገናኘ ሲሆን። ቅርንጫፍ ያለ ግንዱ ላፍራ ላብብ ካለ እጣፋንታው መድረቅ እና መማገድ ነው። ከፍሬያማነት ጋር ዝምድና የሚኖረው ከግንዱ ጋር ባለ ወዳጅነት ቅርርብ ነው። በገብስ ግንድ ላይ ቦቆሎ እንደማይፈራ ሁሉ አንድም ቅርንጫፍ ፍሬው ከግንዱ ጋር የተለየየ መሆን አይችልም።

በታላቁ መጽሐፍ እንደ ተገለጠው እኛ ክርስቲያኞች ቅርንጫፎች ተብለናል ግንዱስ ማን ነው ካላችሁ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው እግዚአብሔር አብ ደግሞ ገበሬ በመባል ተጠቅሷል።(“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።” ዮሐንስ 15፥1) ከቅርንጫፍ ሁሌ የሚጠበቅ ነገር ቢኖር ፍሬ ነው የማያፈራ ቅርንጫፍ የለም።

እኛም ቅርንጫፍ ስንሆን በግንዱ ጋር ካልተጣበቅን በራሳችን ማፍራት የሚባል ነገር ከቶ አይታሰብም (በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። ዮሐንስ 15:4) ያለ ክርስቶስ ፍሬን ማሰብ ያለ እርሱ ድጋፍ መቆምን ማሰብ ያለ እርሱ ፀጋ ጽድቅን ማሰብ ያለጥበቃው ሰላምን ማሰብ የሰውን ልጅ ካለ አዕምሮው ከማሰብ በላይ ይከፋል። አለማችን ያለ እግር፣ ያለ እጅ፣ ያለ አይን፣ ያለ ጆሮ የሚኖሩ ሰዎችን አሳይታናለች ያለ አዕምሮ የሚኖር አንድም ሰው አላስተናገደችም።

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።(ዮሐ 15:5) የፍሬያማነታችን ቁልፍ ሚስጥር ያለው በክርስቶስ የመኖራችን ጉዳይ ላይ ነው። በእርሱ ሳንኖር እናፍራ ማለት ዘበት በእርሱ ኑረን አናፍራ ማለት ሞኝነት ነው። ያለ ግንዱ ቅርንጫፍ እንዳያፈራ በግንዱ ያለ ደግሞ እንደሚያፈራ እናውቃለን።

ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።(ዮሐ 15:8) ከግንዱ መጣበቅ ቅርንጫፉ የሚያመጣው ፍሬ ለገበሬው ክብር እንደሚያመጣው ሁሉ ብዙ በማፍራታችን የሚከብረው እግዚአብሔር አብ ነው።


ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.4K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 23:24:57 የእግዚአብሔር ቃል ንባብ

..... በአንድ ቀን አንድ ምዕራፍ......

➟ ቀን ▬ 13
➟ ምዕራፍ ▬ 13
➟ ንባብ ▬ ዲተመ

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎችን በ 13 ቀን አንብቦ የመጨረስ መረሃ ግብር። ትረካውን በመስማት ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
-የዕብራውያን መልዕክት ትረካ ተጠናቀቀ-
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.6K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 22:39:39 የእግዚአብሔር ቃል ንባብ

..... በአንድ ቀን አንድ ምዕራፍ.......

➟ ቀን ▬ 12
➟ ምዕራፍ ▬ 12
➟ ንባብ ▬ ዲተመ

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎችን በ 13 ቀን አንብቦ የመጨረስ መረሃ ግብር። ትረካውን በመስማት ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.4K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 13:49:45 የእግዚአብሔር ቃል ንባብ

..... በአንድ ቀን አንድ ምዕራፍ.......

➟ ቀን ▬ 11
➟ ምዕራፍ ▬ 11
➟ ንባብ ▬ ዲተመ

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎችን በ 13 ቀን አንብቦ የመጨረስ መረሃ ግብር። ትረካውን በመስማት ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.6K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 09:26:41 #ባያድነኝም_እንኳን

እግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እና መደገፍ መቼም መዋዠቅ የሌለበት እና የጸና መሆን እንዳለበት ለሁላችንም ግልጽ ነው። እግዚአብሔር ለታመኑት እና እርሱን ለተጠጉ ዘወትር የእርዳታ እጁ ወደ ኋላ አይልም። እግዚአብሔርን በምቹ ጊዜ ማመን እና አንተ መታመኛዬ ነህ ማለት ለብዙ ሰው ይቀላል ነገር ግን ሁኔታ በላተመቻቸ ጊዜስ?.... ምናልባት ባልደለን ጊዜስ?..

ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 3 ላይ ያለውን አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ ሰዎቹ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎም ይባላሉ ንጉሱ ላቆመው የወርቅ ምስል(ጣዖት) አንሰግድም በማለታቸው ንጉስ ፊት ተገኝተው ይህን ይናገራሉ። ¹⁷ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ¹⁸ ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።

እግዚአብሔር ያድነናል ብሎ ሙሉ እምነትን እርሱ ላይ መጣል የአማኝ ተግባሩ ነው ነገር ግን በእግዚአብሔር ያለው እምነት ምክንያት ሆኖ መከራ የሚገጥመው ከሆነ እግዚአብሔር ባለመተው ፈንተ መከራውን አሜን ብሎ ይቀበላል። እነኚህ ሰለስቱ ደቂቅ ያደረጉት ይሄኑ ነው። የእግዚአብሔር እርዳታ ሁሌ የማያጠራጠር ነው እግዚአብሔርን የሚያስክድ ነገር በህይወታችን ቢገጥመን ግን እግዚአብሔርን ከመተው ያለንን ሁሉ ማጣት ይሻላል።

ብዙ ክርስቲያን የሚፈተነው በዚህ ነገር ነው። አብዛኞቻችን በተመቻቸ ህይወት ለመኖር ስንል የዘላለም ምቾታችንን እንተዋለን። ለምድር ድሎት እና ተድላ ስንል ከምድር ጋር ተስማምተን ከሚስማመን እንርቃለን። ክርስትና ያለእግዚአብሔር በመኖር ከማለፍ ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ መሞትን ያስችላል።

ክርስቲያን በህያው በእግዚአብሔር አምኖ እና የእርሱ ልጅ ሆኖ ለምን ይፈተናል ለምን ይቸገራል ለምንስ ይሰቀያል ማለት አንችልም የእግዚአብሔር መሆናችን ለምድሪቱ ፈተና እና የማንመች ስለምንሆን ከምድር የሚደርሰን የመልስ ምት የእግዚአብሔር በመሆናችን የሚመጣ ነው። ከአለም ጋር ተስማምተን ብንኖርማ ይሄ ሁሉ ባልሆነ ወደ ፊትም ምንም ባልመጣ ነበር።

ነገር ግን የክርስትና ባህሪው እየሞቱ መብዛት፣ እየተገፉ ማባብ፣ እየተሰቃዩ ማንጸባረቅ ነውና ከተያን ከሰማያዊው ክብር የተነሳ በሚመጣን በማንኛው ፈተና ወደ ኋላ የምንመለስ አንሆንም። እግዚአብሔር ከማንኛውም ነገር ያደነናል ግን እርሱ እግዚአብሔር ምክንያት ሆኖ በህይወታችን አንዳች ነገር ቢመጣ ከእግዚአብሔር ተለየትን ከሚኖረው ደስታ ይልቅ ከእርሱ ጋር ተጣብቀን የሚመጣብን ሞት ወደ እርሱ መድረሻ መንገዳችን ነውና በጸጋ እንቀበለዋለን። እኛ በሞት ምክንያት ወደ ዘላለም ሞት የምንሄድ ሳንሆን በሞት ምከንያት ወደ ዘላለም ህይወት የምንጉዝ ነንና ሞት ወደ ወደደን ወደ ጌታችን የሚወስደን መንገድ ነው።

አምላካችንን በግርማው የማየት ነፍቆት ውስጣችን ሲሞላ ለሞት ያለን ፍራቻ ይጠፋል። ባያድነንም እንኳን እርሱን አንክድም የማለትን ድፍረት ያለን እንደሆነ የእኛ የሆነው ሁሉ ቢነጠቀን ምንም ግድ የለንም ያለን አንዱ አምላካችንን የሚያስክድ ማንኛው መከራ ግን አንገት አያስደፋንም። በሸንጎም ፊት በነገስታትም ፊት ያለን ምስክርነት ይሄ ነው እርሱን አምላካችንን አንክደውም አንተወውም ከእርሱ ውጪ ለምንም አንሰግድም።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
ግንቦት 25/2014 ዓ.ም

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.7K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 21:02:33 #ከመጽሐፍት_አለም

ነፍስ አትሞትም። እርሷ ስለ ዘላለም ሕይወት ወይም ስለ ዘላለም ቅጣት ለዘላለም ትኖራለች። ነፍስ የሕይወቷ አስገኒ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር የምትለያይ ከሆነ በቅጣት ትኖራለች። እኛ ነፍሳችንን የምንከብርና ከፍ ከፍ የምናደርጋት ከሆንን ስጋዊ ፍላጎታችንን መተው ቀላል ነገር ነው።

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እነሆ የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት"(ሉቃ 17:21) ብሎናል። አይሁድ ይሹት የነበረው ምድራዊውን መንግስት ነበር፤ ክርስቶስ በልባችን ውስጥ የገነባው ግን ዘላለማዊ መንግስት ነው። ስለሆነም ንጹህ መሆን ከፈለጋችሁ ውስጣዊው ሰዋችሁን በመመልከት ለነፍሳችሁ ድህነት ጥንቃቄ አድርጉ።

ወደ ልባችሁ ውስጥ ተመልክታችሁ ለውስጣዊው ሰዋችሁ በእውነት የምትታገሉ ከሆናችሁ፤ ሕይወታችሁን በእግዚአብሔር እጆች ላይ የምትጥሉና በልባችሁ ውስጥ ላለው ለመንፈስ ቅዱስ ስራ ምላሽ የምትሰጡ ከሆናችሁ፤ በዓለም ውስጥ እጅግ ደስተኛዎቹ ሰዎች ትሆናላችሁ! ጉዳዩ ይህ ከሆነ በማንኛውም ስጋዊ ምኞት ወይም ርኩሰት ፈጽሞ ልትሸነፉ አትችሉም። ስለዚህ ንጽሕናን በሕይወታችሁ ውስጥ በሚገኙት በሁሉም ሁኔታዎች ላይ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ።



#ርዕስ: ወጣቶችና የንጽሕና ህይወት
#ጸሐፊ፡ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#ገጽ: 20 እና 21



ይቀላቀሉን ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.1K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 14:07:41 የእግዚአብሔር ቃል ንባብ

..... በአንድ ቀን አንድ ምዕራፍ.......

➟ ቀን ▬ 10
➟ ምዕራፍ ▬ 10
➟ ንባብ ▬ ዲተመ

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎችን በ 13 ቀን አንብቦ የመጨረስ መረሃ ግብር። ትረካውን በመስማት ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.0K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 10:02:34 የእግዚአብሔር ቃል ንባብ

..... በአንድ ቀን አንድ ምዕራፍ.......

➟ ቀን ▬ 9
➟ ምዕራፍ ▬ 9
➟ ንባብ ▬ ዲተመ

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎችን በ 13 ቀን አንብቦ የመጨረስ መረሃ ግብር። ትረካውን በመስማት ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.0K views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ