Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ~ ጽድቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የሰርጥ አድራሻ: @fenote_tsedek
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.62K
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ይህ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ቻናል ነው። እባካችሁን ይከታተሉን ለሌሎች ያጋሩ ።
#በጽድቅ_መንገድ_ላይ_ሕይወት_አለ።
#በጎዳናዋም_ሞት_የለም። ምሳሌ 12፥28
ሌሎችንም ይጋብዙ ➟ @fenote_tsedek
ለመልዕክት እና ለአስታያየት➟ @fenote_tsedekbot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-26 09:44:53 #የልቤ_ደስታ

የልቤ ደስታ የነብሴ መከታ
ማን እንደ እግዚአብሔር
ማን እንደ ጌታ

ተራራው በፊቴ ተደለደለልኝ
የሚያስፈራው መንገድ
ለምለም መስክ ሆነልኝ
ያጨናነቀኝ ባላጋራየ
ተወገደልኝ አዚሙ ከላየ
ያደካከመኝ ክፉ ጠላቴ
ወዳደቀልኝ በርሱ በአባቴ

ስብራቴንም እርሱ ጠገነ
በፍቅሩ ዘይት ቁስሌ ደረቀ
እውነተኛ ነው ደግ ሳምራዊ
እሩሩህ ጌታ ቸር ሰማያዊ
ምንም ሳልከብደው
ያዘኝ ትከሻው
ባልንጀራየ ወዳጄ እርሱ ነው

እርቃኑን ሆኖ ጸጋ አለበሰኝ
በመዋረዱ ከፍ አደረገኝ
እየደከመ አሸነፈልኝ
ዘንዶውን ከእግሬ በታች ጣለልኝ
እንዴት አድርጌ እንደምን ላውራ
ያረገልኝን የአምላኬን ስራ

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.3K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 10:04:05 ▬▬✟ ▬ የዝማሬ ጊዜ ▬ ✟▬▬
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
▬ ● #ስምህ_አርማዬ_ነው ● ▬▬
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

ልትሰሙት የሚገባ ድንቅ መዝሙር

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.2K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 12:03:18 የሕይወትህን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ብታደርግ ያን ጊዜ እውነተኛውን እረፍት ታገኛለህ።

አባ ሙሴ ጸሊም

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.4K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 17:00:47 የበጉ ደም
ፈረኦን ህዝብ እስራኤልን አለቅም በማለቱ ምክንያት ብዙ መቅሰፍቶች ወደ ግዛቱ ወደ ግብጽ መጥቶ ነበር ከሁሉም ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ሀዘን የፈጠረበት እና ህዝበ እስራኤልን እንዲለቅ ያደረገው ግን የበኩር ልጆች ሞት ነው። ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ህዝቡ(እስራኤላዊ) የዚህ የሞት ቅጣት እንዳያገኘው የበግ ደም በበራቸው ላይ እንዲቀቡ እና ከበጉ ደም የተነሳ በዛ ቤት ያሉ ሁሉ ከዚህ ሞት እንዲያመልጡ አድርጓል። በግብጻውያን እና በእስራኤላውያኑ መካከል ልዩነት የፈጠረው የበጉ ደሙ ነው። “ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።” ዘጸአት 12፥13

ጌታችን ኢየሱስ የአለምን ኃጢአት ሊያስወግድ የመጣ የእግዚአብሔር በግ እንደ ሆነ መጻሐፍ ይናገራል(ዮሐንስ 1፥29) የእግዚአብሔር ህዝብ የተባለው ህዝብ ሊመጣ ካለው ቁጣ እና መቅሰፍ እንዲተርፍ እራሱ እግዚአብሔር የመፍትሄ አቅጣጫ በመጠቆም ህዝቡን ከሞት አትርፏል። የኢየሱስ ወደ ምድር መምጣት ዋና ምክንያት የጠፋውን የሰው ልጅ ፈልጎ የእግዚአብሔር ልጅ ወደ መሆን የክብር ማማ ለማምጣት ነው። ይህም በበጉ ደም የሚሆን ክብር ነው። የበጉ ደም የኃጢአትን እጥበት ያደርጋል። “ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።” ተብሎ በሮሜ መልዕክት 5፥9 ላይ እንደተጻፈ ጽድቀን የማግኘ መንገድ ነው።

ያለ ክርስቶስ ደም ክርስትናችንን ማሰብ ስህተት እና ውድቀት ነው። የበጉን ደም ኃይል አልፎ ቤታችን የሚገባ ሞት፤ ከበጉ ደም የማንጻት አቅም በላይ የሚሆን የኃጢአት እድፍ በፍጹም የለም። ብዙ ክርስቲያኖች በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር እቅፍ ሲርቁ ወደ ጉያው የመመለስ አቅም የሚያጡት ኃጢአታቸውን እና የበጉን ደም ሚዛን ላይ በማስቀመጥ የኃጢአታቸው ግዝፈት ስለሚታያቸው ነው። እውነታው ግን የአለም ሁሉ ኃጢአት ሚዛን ላይ ቢሆን ከበጉ ደም በላይ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ስለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የአለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስን የሚጠራው። የታረደልን እርሱ ስላለን በሞት እና በእኛ መካከል ድንበር አለ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.6K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 08:10:48
ባለስልጣኑ አዞ የማያነጋው፣ ሀብታም ከፍሎ የማያነጋው፣ የደግ ሰዎች ደግነት ጨለማውን ያልገፈፈው፣ የተንኮለኛ ሰዎች ክፋት ንጋቱን ያልከለከለው፣ የእኔ ምኞት ነጋቴን ያልሳበው፣ የሰው እቅድ ያላመጣው፣ የማንም ብርታት ያልጎተተው፣ ምሽቱ ያለፈው ከአንተ ምህረት፣ በአንተ ቸርነት ነውና የስልጣናት ሁሉ ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን። የንጋት ጠሪ የሆንከው አንተ የውሎዬን ጤናማነት ጠብቅልኝ። አሜን

በአንተ ቸርነት ከመጣ ንጋቴ
አንተ ባልዋልክበት አልዋል አባቴ

በቸር ዋሉ

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
3.0K viewsedited  05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:18:02 የዕለቱ መልእክት

“ የጥበብ መጀመሪያ #እግዚአብሔርን_መፍራት_ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።”
— መዝሙር 111፥10

“ የጥበብ መጀመሪያ #እግዚአብሔርን_መፍራት_ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።”
— ምሳሌ 1፥7

“ የጥበብ መጀመሪያ #እግዚአብሔርን_መፍራት_ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።”
— ምሳሌ 9፥10



ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.7K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:22:15 #ኢትዮጵያን

ሁሉ በፊትህ ግልጥ የሆነልህ የሁሉ አስገኚ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ ሃገራችንን ኢትዮጵያን እንድታስባት እንለምንሃለን። ብዙ ከአንተ ፍቃድ ርቀን ኖረናል ይቅር በለን እንመለሳለን። አሁንም የአንተ ምህረት ያስፈልገናል የይቅርታህ አቅም ያቆመናል። አባት እግዚአብሔር ሆይ ሃገራችንን ካለችበት ውጥረት እንድትታደጋት በቃሽ ብለህ እንድታቆማት እንለምንሃለን። ወንድም በወንድሙ ላይ ሰይፍ የሚያነሳበት ጊዜ እንዲበቃ፣ የጎረቤት ክስ እንዲቆም፣ የእርስ ለእርስ እልቂት እንዲቋጭ በፊትህ እንሆናለን። አባታችን ከአንተ መንገድ አፈንግጠን ለእኛ ሰፊ በመሰለን ጎዳና ላይ ተራምደናል፣ ያየህልንን ትተን የታየንን ልንይዝ ታግለናል፣ ቅዱሱን አርክሰን እርኩሱን ከፍ አርገናል፣ የሰማዩን አቅልለን የምድሩን አሞካሽተናል፣ እልልታችን ላልከበረው፣ ዝምታችን ከፍ ላልከው ሆኖ ዘመናችን ነጉዷልና የማስተዋላችንን ማስተዋል እንትረዳው እንለምንሃለን። የምንሰማው ሀዘን መሆኑ እንዲበቃ የአንተን ምህረት እንለምንሃለን።

አንተ ልጅህን የሰዋህለት መሰዋቱ እንዲቆም፣ አንተ ልጅህን የገደልክለት በአንተ ሳይሆን የሞት ሲሳይ መሆኑ እንዲያበቃ፣ ያን ሁሉ ዋጋ የከፈልክበት የሰው ልጅ የትም መውደቁ እንዳይቀጥል አባታችን እግዚአብሔር ሆይ አክብረህ የፈጥረከው ክቡር ፍጡር እንደ እንስሳ በሜዳ ሞቶ የምናይበት ዘመን እንዲቋጭ እንማልድሃለን። ሃገራችን የምህረትህን መዳፍ ተራምዳ በክፉ እጆች ላይ እንዳታርፍ የትውልዱን ማስተዋል እንድታግዝ እንለምንሃለን። ያላንተ ጥበቃ ጠባቂ እንደሚደክም፣ እንተ በቃ ካላልልክ ጸጥታ እንደማይሰፍን ተረድተን ወደ አንተ እንድንመለስ እንድትረዳን እንለምንሃለን። በልጅህ ደም አጥበህ እንድታነጻን ክፉ የሆኑትን ያለፉትን ዘመናችንን በፊትህ እናቀርባቸዋለን። ማረን ይቅርም በለን ፊትህን ለመያት አቅም ያጣው እኛነታችን በምህረትህ ብርታት እንዲጸና እለምንሃለን። ለእኛ ስትል ለሞት አሳልፈህ በሰጠኽው በአንድ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ፣ ሕያው እና ዘላለማዊ ስም አሜን።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.6K viewsedited  05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:18:29
ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.5K views20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:23:40 #ሽሽ_እናም_ተከተል

መንፈሳዊነት የሚሸሽ አለው? በትክክል
ከምን? ከክፋ የጎልማሳነት ምኞት

በመሸሽ ምን አገኛለሁ?
የተቀደሰ፣ለጌታው የሚጠቅም
ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ምርጥ ዕቃ ትሆናለህ

በመሸሽ የተጠቀመ ምሳሌ ልትሰጠኝ ትችላለህ? በትክክል ዮሴፍ (ዘፍ 39:1)

ባለመሸሽ የተጎዳ አለ? ? ብዙ ለምሳሌ አዳምና ሔዋን ፣ዳዊት፣ሰሎሞን፣ሶምሶን ወዘተ (ዘፍ 3:1 2ሳሙ 11:1 1ነገ1:1 መሳ 16:1)

መሸሽ ይበቃኛል? አይበቃህም
ምን ቀረኝ ? የሸሸ የሚከተለው አለው

ምን ልከተል? በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል(2ጢሞ 2:20—23)

ወዳጆቼ ውድቀታችን ከክፋ ካለመሸሽ፣ ፍሬያማ አለመሆናችን ካለመከተል ይመነጫል። ከምን እየሸሽን ምንስ እየተከተልን ነው? የክርስትና ጉዞ ትክክለኛ መንገዱ የምንሸሸውም የምንከተለውም እንዳለ በማወቅ ላይ ይመሰረታል።በዚህ መርህ ከተጓዝን ራሳችንንም ሌሎቻችንም እናድናለን።እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ተረፈ አበራ

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
3.0K viewsedited  20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:52:12 የያዕቆብ ጉድጓድ

ለብዙ ዘመናት ያገኘነው እና የተሰጠን መልካም ነገር ከእርሱ የተሻለ ነገር እስካላየን ድረስ የዘመን ቆጠራው ይቀጥላል የረካን ይመስለናል ደግሞ እርካታችን እየጠፋ የሚመጣ ስለሆነ በተደጋጋሚ ለመርካት ስንል በዛ ልምምድ ውስጥ እንመላለሳለን። ብዙ ዘመን ከያዕቆብ ጉድጓድ የፈለቀን ውሃ መጠጣት በውስጡ ብዙ ጥማት እንጂ የጸና እርካታ ውስጡ የለም። ብዙ ዘመን በራስ ድካም መመካት ውለታውን መግፋፋት እንጂ እረፍት የሚባል የለውም። ከያዕቆብብ ጉድጓድ ስትቀዳ የነበረችው ሳምራዊቷ ሴት ለመርካት ስትል በየ ጊዜው ወደ ወንዝ ትሄድ ነበር ክርስቶስ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ከቶ አይጠማም ባላት ጊዜ ይህን ውሃ ለመጠጣት በውስጧ ያለው ጉጉት ደስ የሚል ዘመናትን ያሳለፍ ድካሟን በቅጽበት የሚያስረሳ እና ከፊቷ የተሰጣት ዘመን እንደሚበልጥ ያስረዳ ነገር።

ለማረፍ ብላችሁ ለዘመናት ስታደርጉ የነበራችሁት ነገር ምንድን ነው? ከጥማችሁ ለመርካት ከስንት ጉድጓድ ጠጣችሁ? ልረፍ ብለን ያደረግነው ግን ያላሳረፈን ለመርካት ብለን የጠጣነው ግን ያላረካን እንደውም እየደጋገመ የሚያስጠማን ህይወታችን በድግምግሞሽ ተሞልቶ መሰልቸትን እንድንላበስ ያደረገን እንጂ መፍትሄ የሆነን አንድም ነገር የለም። ሳምራዊቷ ሴት ሰለማያስጠማው የዘላለም ውሃ ከክርስቶስ በሰማች ጊዜ ድጋሚ እንዳልጠማ ይህን ውሃ ስጠኝ በማለት ጠየቀች። ዘላቂ መፍትሄ ትፈልግ ነገር። ይህ የክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት ትልቁ መንስኤ ጭምር ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የመምጣቱ ሚስጥር ድካማችን አላመጣ ያለውን እረፍት ሊሰጠን አላረካ ባለን ውሃ ፈንታ እርሱ የዘላለም የህይወት ውሃ ሆኖ ሊያረካን ነው።

ዘመናችንን ሁሉ ያላገኘነው ክብር እና ሰላም፣ እረፍት እና ደስታ የሚገኘው ለእኛ ሲል ሰው የሆነው ክርስቶስ ጋር ብቻ ነው። የያዕቆብ ጉድጓድ ሊያረካው ከሚችለው በላይ የህይወት ውሃ ክርስቶስ ለዘላለም ያረካል። የያዕቆብ ጉድጓዱ በሆነ ስፍራ ያለ፣ በብዙ ድካም የሚገኝ፣ በማመላለስ የሚያደክም፣ በተደጋጋሚም የሚያስጠማ ጊዜያዊ እና አላፊ ውሃ ነው የህይወት ውሃ የሆነ ክርስቶስ ግን በሁሉ ስፍራ የሚኖር፣ ያለ ስፍራ ወሰን የሚሰራ፣ በእርሱ በማመን የሚገኝ፣ አንዴ ተጠጥቶ ዘላለም የሚያረካ፣ ከጥማት እስከ መጨረሻው የሚለይ፣ ሁሉም ቢጠጣው የማይደርቅ እያረካ የሚያረካ የህይወት ውሃ ነው።

ብዙ ዘመን ከፍታችን ብለን የወጣንበት ከታየልኝ ከፍታ አንጻር ሲታይ በእጅጉ ያንሳል የተሻለ ነገር ማየት ከቻልንና ማመን ከሆነልን ያለፈውን ዘመን የሚያስረሳ ድንቅ ለውጥ በህይወታችን ይሆናል። እርሱን ለሚወዱ የተዘጋጀ በዙ ክብር እና ከፍታ ስላለ እርሱን መውደድ እና ከእርሱ ጋር መጣበቅ ያስፈልጋል። ሃዋርያቱ ጌታ ሆይ አንተን ትተን ወዴት እንሄዳን አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ እንዳሉት እርሱ አለመልቀቅ ከእርሱ አለመራቅ ያስፈልጋል። እንድንናውቀው ማስተዋሉን መለመን እንዳወቅነው መኖር እና እንዳወቅነው መሞት ጥቅማችን ነው።

ዲያቆን ተስፋ መሠረት

መልካም ቀን

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
657 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ