Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ~ ጽድቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenote_tsedek — ፍኖተ ~ ጽድቅ
የሰርጥ አድራሻ: @fenote_tsedek
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.62K
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ይህ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ቻናል ነው። እባካችሁን ይከታተሉን ለሌሎች ያጋሩ ።
#በጽድቅ_መንገድ_ላይ_ሕይወት_አለ።
#በጎዳናዋም_ሞት_የለም። ምሳሌ 12፥28
ሌሎችንም ይጋብዙ ➟ @fenote_tsedek
ለመልዕክት እና ለአስታያየት➟ @fenote_tsedekbot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-06 00:41:16 የዕለቱ መልእክት

የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

1ኛ ዮሐንስ 5:20-21

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
855 views21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 22:43:00
ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
1.4K views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 09:30:55 #ተመስገን

በላይ በሰማያት ያለህ፣ ከፍ ብለህ የምትከብር፣ የምስጋና መስዋዕት የሚቀርብልህ፣ የማይቋረጥ አምልኮ የሚደረግልህ፣ ምድርን ያበጀህ፣ ሰማይን የዘረጋህ፣ የሁሉ ገዢ የሆንክ፣ ከዘመን በፊት ገነህ የኖርክ፣ ሁሉም አርጅቶ ዛሬም ያለህ፣ ሁሉን አሳልፈህ ለዘላለም የምትኖር፣ የፍጥረት አስገኚ የሆንክ፣ ሁሉን በፍቃድህ ያበጀህ፣ ይሁን ብለህ የሆነልህ፣ ሁሉን በቃልህ ያስዋብክ፣ የዘመን ቆጣሪዋ የፍጻሜ አዋቂዋ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን። በእኔ የማክበር ጥግ የማትከብር፣ በማንም ምርጫ ስልጣን ያላገኘህ፣ በአመኑህ እልልታ ክብርህ ከፍ የማይል፣ በፍጥረት ዝምታ ምስጋና የማይጎድልብህ፣ በሆታ የማትደምቅ፣ በእጅ ብልጫ የማትሾም ህያው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ምስጋና ይድረስህ።

ለውለታህ አንዳች የምከፍለው የለኝምና ተመስገን እልሃለሁ። የእኔን መተላለፍ ሳትመለከት የዳግም እድል ዝናብ ያዘነብክልኝ፣ ከከብት በረት በላይ በከረፋው ልቤ ልትኖር ያልተጸየፍክ፣ በኃጢአት የጎረበጠው ሰውነቴ ያልቆረቆረህ፣ ዘወትር የሚስተው ህሊናዬ ያላራቀህ፣ ለተንኮል የተጋው አቅሜ ያላሸሸህ፣ በራሱ መንገድ የሚራመደው እግሬ ያላስቀረህ፣ የአለምን የሚመለከት አይኔ ያልሰወረህ፣ ለአለም ያጨበጨበው እጄ ያልሰበሰበህ፣ ከአንተ ለመራቅ የሚደረግ ጥረት አንተን ያልጎተተህ፣ ይህም ሁሉ ሆኖ ውለታ የምትውል፣ የምትመግብ፣ የምታሳርፍ እና የምታናቃ እሩሩ አባት ነህና ክብር ይሁንልህ።

የቱ ፊደል፣ የቱስ ቃል፣ የቱ ሀረግ፣ የትኛው አረፍተ ነገር፣ የቱ አንቀጽ፣ የቱስ መጽሐፍ፣ የትኛው ጸሓፊ፣ የቱ ተራኪ፣ የቱ አንባቢ፣ የቱስ ምሁር፣ የቱ ገጣሚ፣ የቱስ ሰባኪ፣ የቱ መምህር፣ የቱ አዋቂ የትኛው የቱ.... እኮ የቱ ብርቱ? ውለታህን ሊገልጥ የሚቻለው እኮ ማነው ብቁ? .....ማንም....የለም አባት እግዚአብሔር ሆይ አንተ ህሊናን የሚያልፍ ውለታ ውለህልናል። አዕምሮን የሚሻገር ዋጋ ከፍለህብናል። ምስጋና ያለንን ማቅረባችን እንጂ የሚገባህ ሆኖ አይደለም። እልልታው ዝም ከምንል ብለን እንጂ ውለታህን ይክሰዋል ብለን በፍጹም አይደለም። ሰው ውለታ ቢውልልን በሌላ ውለታ እንክሰዋለን። የአንተ ውለታ እኮ አሳሪ ውለታ ነው ማርኮ የሚያሰቀር፣ ስቦ የሚያቅፍ፣ ይዞ የማይለቅ፣ ጠርቶ የሚያከብር፣ ያለፈውን ዘመን የሚያስጥል፣ የከንቱ የሆነውን የሚያስተው ውለታ ነው። ውለታህ መባዘኔን ያስቀረ፣ መጥፋቴን ያገኘ፣ ትላንቴን የለወጠ ነውና ክብር እና ምስጋና ለአንተ ይሁንልህ። አሜን

ውለታህን ከንቱ በሚያደርግ ኑሮ ውስጥ እንዳልሆን በጸጋህ ደግፈኝ። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
ሰኔ 23/2014 ዓ.ም

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
1.9K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 14:26:56 ▬▬ ✟ ▬ የዝማሬ ጊዜ ▬ ✟ ▬▬
▬▬▬▬▬▬ . . ▬▬▬▬▬▬▬
▬● #እግዚአብሔር_የወደቁትን ●▬▬
▬▬▬▬▬▬ . . ▬▬▬▬▬▬▬

ዘማሪ አቤል

ልትሰሙት የሚገባ ድንቅ መዝሙር

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.3K viewsedited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 12:04:17 የእለቱ መልእክት

አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ችግረኛና ምስኪን ነኝና። ቅዱስ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ አንተን የታመነውን ባሪያህን አድነው። አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ።

የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና። አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ምሕረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና። አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ።

ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ። አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ እንደ ሥራህም ያለ የለም።

መዝ 86:1-8

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.5K viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 22:10:44 ? የጥያቄ እና መልስ ጊዜ ?

“ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” የዚህ ቃል ትክክለኛ ጥቅስ የቱ ነው ?

Ⓐ ማቴዎስ 1፥3
Ⓑ ማርቆስ 1፥3
Ⓒ ሉቃስ 1፥3
Ⓓ ዮሐንስ 1፥3

መልስ ያላችሁትን ስትመርጡ የሚመጣላችሁን Ok በማለት ብቻ መሳተፍ ትችላላችሁ።

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.9K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 11:06:18 ▬ ✟ ▬ የዝማሬ ጊዜ ▬ ✟ ▬
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬
▬● #እኛን_ከወደደበት ●▬▬
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬

ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ

ልትሰሙት የሚገባ ድንቅ መዝሙር

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.6K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 11:02:31 ? የጥያቄ እና መልስ ጊዜ ? “ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ___ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።” — 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥13 Ⓐ እምነት Ⓑ ፀጋ Ⓒ አባት Ⓓ ተስፋ ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.3K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 10:13:38 ይገርመኛል

የመገረም ጫፉን እስካልፈው ድረስ አንተ ለእኔ ያለህ ምህረት ወሰን ያጣብኛል። በምን መስፈርት እንደምትምረኝ ላሰብ ስሰናዳ ከእኔ የሆነው ሁሉ በዶ ሆኖ ሳየው የምህረትህን አቅም ብቻ አድንቄ አርፋለሁ። እኔ ወደ ወደቤ የደረስኩት በምህረትህ ጀልባ ላይ ተሳፍሬ በፍቅርህ አብርሆት ተከብቤ ነው። ግን የሚገርመኝ ሁሌ የሚደንቀኝ ይሄ ነው። ባሳፈርኩህ ፈንታ፣ ባስቀየምኩህ ምትክ፣ ችል ባልኩህ ምላሽ፣ አንተ የሰጠኸኝ ምህረት ገርሞኝ አያበቃም። የአንተን ምህረት ቀምሶ የማይገረም ይኖር ይሆን?

ማን በራሱ ቆሞ ያለምህረትህ እራሱን ያስባል? ምንስ በምህረትህ ያልተገረመ መገረምን ተረዳሁ ይላል? ስትምር የማትቆጥር ባለመሰልቸት ይቅር የምትል መሃሪው አባቴ ሆይ የይቅርባይነትህን ወሰኑን ልደርሰው እሻና ትርፉ ደካም ብቻ ሲሆንብኝ ተገርሜ ድካሜን እራሳለሁ። ይህም የመገረሜ ጋኑ ሞልቶ እንዲፈስ ያደርገዋል። እኔ ለአንተ የሚሆን አንዲት ደቂቃ ባጣ አንተ ግን ያለመሰልቸት ትጠብቀኛል ከአንተ ከመራቄ ርቀት በላይ የአንተ ከጎኔ መሆን ይሰማኛል። የምህረትህ ብዛት የህይወቴን አርምጃ ይወስናል።

ሰው ሲምር ይቆጥራል ደግሞ ቢምር የቀድሞውንም ያስባል የሚምረው እስከ በሚባል ምህረት ነው አንተ ግን እስከ ባለሆነ ምህረት ትምረኛለህ። ይህ የሚትረፈረፈው ምህረትህ እኮ ነው የሚገርመኝ። ኃጢአተኛ ብላኝ አለም እውቅናውን ለሰጠችን ለእኔ የሚሆን ምህረት አለህ። ማንም አይምረኝም ብሎ እንዳይርቅህ ኃጢአቱን የሚያጥብትን የደምህን አቅም ትገልጥለታለህ። የቱም የበደል ክምር ከአንተ ምህረት በላይ እንዳልሆነ ምስክሩ እኔ ነኝ።

ምህረትህን ሊገልጹ ቃላት እንኳን አቅማቸውን ያጣሉ። ምህረትህ ከህሊናዬ የማሰብ አቅም በላይ ይሆንና መገረምን ምርጫዬ አደርጋለሁኝ። ተመስገን ልብልህ እንጂ ሌላ ቃል የለኝም። የምህረትህ ብዛት ለኃጢአት ፍቃድ እንዳይሆነኝ በፀጋህ ጠብቀኝ። አሜን


ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek
2.8K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 10:21:47 ? የጥያቄ እና መልስ ጊዜ ?

“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ___ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥13

Ⓐ እምነት
Ⓑ ፀጋ
Ⓒ አባት
Ⓓ ተስፋ

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ➟ @fenote_tsedek
2.5K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ