Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @fasilsc
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

የአፄዎቹ ፈጣን የመረጃ ምንጭ
The oldest and most popular Fasil Kenema Sport Club was established in 1960. This legendary Emperors Club has been around for 55 years.
🔴 ለአስተያየት @FASILKFCBOT

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 60

2022-07-15 19:40:33
4.7K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:39:53
4.4K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:59:08
አፄዎቹ የመስመር አጥቂ አስፈርመዋል

አፄዎቹ የመስመር አጥቂ አስፈርመዋል
በሲዳማ ቡና መለያ የሚታወቀው አጥቂ ቀጣይ ማረፊያው ፋሲል ከነማ ሆኗል፡፡
ከሰሞኑ ውል ማራዘም እና መለያየት ላይ ቆይቶ የነበረው ፋሲል ከነማ ወደ ዝውውሩ በዛሬው ዕለት በመግባት አዲስ ቅጥሮችን እየፈፀመ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂው ሀብታሙ ገዛኸኝን የግሉ አድርጓል፡፡
ሀብታሙ በደቡብ ፖሊስ እግርኳስን መጫወት የጀመረ ሲሆን ያለፉትን አምስት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቤት ዕድገቱን ማስቀጠል ችሎ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሦስተኛ ክለቡ ወደሆነው ፋሲል ከነማ በሁለት ዓመት ውል አምርቷል፡፡
ክለቡ በዛሬው ዕለት ካስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የይድነቃቸው ኪዳኔ እና ዓለምብርሀን ይግዛውን ውል ማደሱ ይታወሳል፡፡

@FASILSC
4.5K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:13:06
ፋሲል ከነማ የመስመር ተከላካዮች አስፈርሟል

ፋሲል ከነማ የመስመር ተከላካዮች አስፈርሟል
አፄዎቹ የኋላ መስመራቸውን በዝውውር ማጠከራቸውን በመቀጠል ሁለት የመስመር ተከላካዮችን ሲያስፈርሙ የአንድ ተጫዋች ዉልም አድሰዋል።
የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ ወዲህ ከተወሰኑ ተጫዋቾች ጋር ሲለያዩ የሌሎች ተጫዋቾችን ውል ማራዘም ላይ ትኩረት አድርገው ቆይተዋል። አዲስ ቅጥር በመፈፀሙ በኩል ትናንት መናፍ ዐወልን በመጀመሪያ ፈራሚነት ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለሁለት ዓመታት በሚዘልቅ ውል የቡድናቸው አካል አድርገዋል።
ከአፄዎቹ ፈራሚዎች አንዱ ተስፋዬ ነጋሽ ሆኗል። በቀኝ መስመር ተከላካይነት አልፎ አልፎም በመስመር አጥቂነት ሚና የሚጫወተው ተስፋዬ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወልቂጤ ከተማ ሲጫወት የቆየ ሲሆን ከዛ ቀድመ ብሎ በጥቁር አባይ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ አዳማ ከተማ እና ወልዲያ ማሳለፉ ይታወቃል። ሌላኛው አዲሱ የፋሲል ከነማ ተጫዋች ደግሞ በጅማ አባ ጅፋር የምናውቀው ወንድምአገኝ ማርቆስ ሆኗል። በመስመር እና በመሀል ተከላካይነት ሲጫወት የምናወቀው ወንድምአገኝ ከዚህ ቀደም ለሌላኛው የጅማ ክለብ ጅማ አባ ቡና ሲጫወት መቆየቱ የሚታወስ ነው።
ከእንየው ካሳሁን መልቀቅ በኋላ በቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታ ላይ አሁን የሌሉትን አብዱልከሪም መሀመድ እና ሰዒድ ሀሰንን ሲጠቀም የቆየው ፋሲል በሳለፍነው የውድድር ዓመት አመዛኙን የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ዓለምብርሀን ይግዛውን ውልም አራዝሟል። በመሆኑም ከዓለምብርሀን በተጨማሪ ሁለቱን ተጫዋቾች በመጨመር ክለቡ በተለይም የቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታውን በማያዳግም መልኩ ለማጠናከር ያለሙ ዝውውሮችን ፈፅሟል ማለት ይቻላል።

@FASILSC
4.7K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:34:17
4.7K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:19:14
ፋሲል ከነማ ትልቅ ቡድን ነው!

ማንም ምርጫው ሊያደርገው የሚችል ክለብ ነው!

ሀገራችን ውስጥ ለመጫዎት ከሚመረጡ ሁለት ቡድኖች ውስጥ አንዱ ነው!

ምን ተፈጥሮ ነው ታዲያ እንዲህ አይነት ግራ የገባው ዝውውር የተፈፀመው?

@FASILSC
5.2K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:33:06
#የፋሲል_ከነማ ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ ውሉን አራዝሟል!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በተጫዋቾች ዝውውር የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረ የሚገኝ ሲሆን የግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔን ውል ለሁለት አመት በማራዘም ቆይታውን አረጋግጧል::

ይድነቃቸው ኪዳኔ በአፄዎቹ ቤት መልካም ቆይታ እንዲሆንልህ እንመኛለን!!

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
5.9K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:01:19
#ፋሲል_ከነማ ከአጥቂው ሙጅብ ቃሲም ጋር ተለያይቷል...

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በተጫዋቾች ዝውውር በርካታ ተጫዋቾቹ ውል ጨራሽ መሆናቸውን ተከትሎ ሁሉንም ልጆች አግባብቶ ለማስቀጠል የክለባችን ቦርድ አመራሮች ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም በክለባችን የ4 አመታት ቆይተው የዋንጫ ክብሮች በማንሳት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈውን ሙጅብ ቃሲምን ማቆየት ባለመቻሉ ኮብራው ማረፊያውን ወደ ሀዋሳ ከተማ አድርጏል::

#ሙጅብ_ቃሲም በሄድክበት ሁሉ መልካም ጊዜ እንድታሳልፍ እንመኛለን!!

#እናመሰግናለን!!

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
5.7K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:51:57
#ፋሲል_ከነማ መናፍ አወልን አስፈርሟል!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ 2015 የውድድር አመት በአዲስ መልክ ትእጠናክሮ ለመቅርብ አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ (ቲጋና) ያስፈልጉኛል የሚላቸውን ተጫዋቾች የክለባችን ቦርድ አመራሮች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማነጋገር ላይ የሚገኙ ሲሆን የመጀመሪያ የሆነውን የተከላይ ቦታ ተጫዋች ወጣቱ መናፍ አወልን ለሁለት አመት በሚያቆይ የውል ስምምነት አስፈርመዋል::

መናፍ አወል በአዳማ ከተማ እና በባህርዳር ከተማ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ከ23 አመት በታች እና ዋናው ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት በመስጠት አሳልፏል!!

አፄዎቹን ተቀላቅሎ ፊርማውን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስቀመጠው ወጣቱ ተጫዋች መናፍ አወል ፋሲል ከነማ በመፈረሙ በጣም ደስተኛ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን በቅርብ ደጋፊዎችን አውቃቸዋለሁና በነሱ ድጋፍ ትልቅ ክለብ ላይ ትልቅ ተጫዋች የመሆን እቅድ አለኝ በማለት ለክለባችን ይፋዊ ገፅ ተናግሯል!!

የፋሲል ከነማ አዲሱ ፈራሚ አፄው መናፍ አወል እንኳን ደህና መጣህ!!

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
5.5K viewsedited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:42:10
እናመሰግናለን

"ይሄ ክብር ያንስብሃል ስዩም ዋርካው"

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በፋሲል ከነማ ቤት ላስመዘገቡት የማይረሳ ህያው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ የክለቡ አንድ ደጋፊ ስፖንሰር አድርጓቸው በግሪክ በጉብኝት ላይ ነው።

የአሰልጣኙን የግሪክና የፈረንሳይ ጉዞ ሙሉ ወጭ የሸፈነው የፋሲል ከነማ የቦርድ አባል፣ የቶፕኬር ማኑፋክቼሪንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ አዱኛ ነው።

አሰልጣኝ ስዩም ፋሲል ከነማን የኢትዮጵያ ዋንጫና የኘሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ በማድረጋቸው ለአሰልጣኙ ይሄ ክብር የሚያንስ እንጅ የሚበዛ አለመሆኑን ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከባለቤታቸው ጋር በግሪኳ አቴንስ ከተማ በጉብኝትና በመዝናናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ነገ ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ የሚያቀኑ ይሆናል።

@FASILSC
6.3K viewsedited  20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ