Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @fasilsc
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

የአፄዎቹ ፈጣን የመረጃ ምንጭ
The oldest and most popular Fasil Kenema Sport Club was established in 1960. This legendary Emperors Club has been around for 55 years.
🔴 ለአስተያየት @FASILKFCBOT

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-30 19:06:42 ፋሲል ከነማ 2-ኤሌክትሪክ 0
5.4K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 19:06:00 ጎሎልልል ፋሲል
5.3K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 19:05:52 ሁለተኛ አጋማሽ ተጀምሯል

ፋሲል ከነማ 1- ኢትዮ ኤሌክትሪክ 0
5.2K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 17:29:10
ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

የዛሬው አሰላለፍ ይሄን ይመስላል በዛብህ መለዮ፣ሱራፌል ዳኛቸው፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና አስቻለው ታመነ በጉዳት ሲሆን ሽመክት ጉግሳ እና አምሳሉ ጥላሁን በግል ጉዳይ የዛሬው ጨዋታ እሚያልፋቸው ይሆናል

እናሸንፋለን



@FASILESC
5.3K viewsedited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 22:31:22
ፋሲል ከነማ ከ ኢቶዮ ኤሌክትሪክ

አርብ ምሽት 12 ሰአት አዳማ ዩኒበርስቲ

ሽመክት ጉግሳ እና በዛብህ መለዮ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው


እናሸንፋለን



FASILESC
5.3K viewsedited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 11:32:42
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2016 የውድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከወዲሁ ስራ የጀመረ ሲሆን የክለባችን ደጋፊዎች ደግሞ የአባልነት መታወቂያ በማውጣት ደጋፊነታቸውን በተግባር እያስመሰከሩ ይገኛሉ!!
ውድ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የአባልነት መታወቂያ የማውጣት ንቅናቄውን ሁሉም የክለባችን ቤተሰቦች የተመዘገቡ ደጋፊዎች እንዲሆኑ መታወቂያ የማውጣት ስራው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በውጭ ሀገር ያላችሁ ደጋፊዎች ይሄን በጎ ተግባር እንድትቀላቀሉ ጥሪው ተላልፏል::

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
5.8K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 06:33:07
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በአል!

@FASILSC
5.1K viewsedited  03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 19:03:41
ቀጣይ ጨዋታ

ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

አርብ ሰኔ 23

12 ሰአት አዳማ ዩኒበርስቲ


@FASILE
8.5K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 19:12:36
ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ 0-0 ማላዊ

@FASILSC
9.7K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 15:36:04 ፋሲል ከነማና ውስጥ አዋቂው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዳግም ተጣመሩ

ኢትዮጵያ ቡና ያቀረበው 350 ሺህ ብር ደመወዝ ተቀባይነት አጥቷል አጼዎቹ የንግስና ቦታቸውን ለማስመለስና በአፍሪካ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ ክለብ ለመሆን በማለም አሰልጣኝ ውበቱ አባተን አሰልጣኝ ለማድረግ ተስማሙ።
ዋሊያዎቹን ለአፍሪካና ለቻን ሻምፒዮና የማብቃት ታሪክ የሰሩት አሰልጣኝ ውበቱ በጠንካራ ሁኔታ ሲፈልጓቸው ከነበሩትና ሙያዊ ግልጋሎታቸውን ካገኙት ከፋሲል ከነማና ከኢትዮጵያ ቡና ተወካዮች ጋር ድርድር ሲያደርጉ ቆይተው ከፋሲል ከነማ ጋር ተስማምተዋል።
አሰልጣኙ በ2003 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ካደረጉት የኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሁለት ጊዜ የተደራደሩ ሲሆን ከክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከአንድ የቦርድና ከደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይት ያለ ስምምነት ተቋጭቷል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ 400 ሺህ ብር የወር ደመወዝ በሶስት አመት የሚከፈለው 14,400,000 ለሁለት ተካፍሎ 7,200,000 ሺህ ብር በቅድሚያ ክፍያ ተከፍሎት ግማሹ በ36 ወር ተካፍሎ በደመወዝ 200 ሺህ ብር እንዲከፈላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ቀርቷል። በተለይ የቦርድ አባሉ አቶ ዳንኤል ገንዘቡ መብዛቱን በመግለፅ አቅሙ የለንም ለቦርድም አይቀርብም በማለታቸው ያለ ስምምነት ተለያይተዋል።

ክለቡን የወከሉት ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ ድርድር ከመቀመጣቸው በፊት በአሰልጣኞቹ ወገን ሌላ የመደራደሪያ ሀሳብ ቀርቧል። በመጀመሪያ አመት የሚከፈለው የአንድ አመት ደመወዝ 4,733,000 በቅድሚያ ተከፍሎ ቀሪው ለሁለት አመት ለ24 ወር በደመወዝ እንዲከፈለው ቢጠይቅም የደጋፊ ማህበሩ አመራሮችና ቦርዱ ሳይስማሙ ቀርተዋል።
ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ቦርዱና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ተወያይተው ክለቡ 300 ሺህ ብር ደጋፊ ማህበሩ 50 ሺህ ብሩን ሸፍነው 350 ሺህ ብር ለመክፈል ቢጠይቁም ለውሳኔ በመዘግየታቸውና አሰልጣኙን ማሳመን ሳይችሉ በመቅረታቸው ፊታቸውን ወደ ሌላ የውጪ ሀገር አሰልጣኝ ማዞራቸው ታውቋል።
ጠንካራ ድርድር ያደረጉትና አሰልጣኙን ለማሳመን ሽንጣቸውን ገትረው የተደራደሩት አጼዎቹ ፋሲል ከነማዎች በኢትዮጵያ ቡና በአርባ ምንጭና በድሬዳዋ ከተሞች ከንቲባዎች ሳይቀር የተፈለገውን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት አሰልጣኛቸው አድርገው መርጠዋል።
የ2013ና የ2014 ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ያጣው ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢን አቶ ባዩ አቦሀይ ድርድሩን እንዲመሩ ያደርገው ጥረት በስምምነት መቋጨቱ ታውቋል። ከንቲባው ከዚህ ሀላፊነታቸው አስቀድሞ የፋሲል ከነማ ደጋፊ በመሆን ስታዲየም ተገኝተው ቡድኑን ያበረታቱ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ከንቲባው ለፋሲል ቅርብ መሆናቸው ለለውጥ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን ይታመናል።
የክለቡ የውስጥ አዋቂ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አሰልጣኝ ውበቱ አስቀድሞ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የመሆን እድል የነበራቸው ሲሆን በወቅቱ ሀላፊነት ላይ የነበሩትን አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽ /ቲጋናን/ ለመጀመሪያ ጊዜ ምክትል አድርገው እንደሾሙ በመጥቀስ ምክትሌ አድርጌ አሁን ደግሞ በመንገዱ ላይ አልቆምም በማለት ጥያቄውን አለመቀበላቸው ይታወሳል።
ፋሲል ከነማዎች እስከ ሰኔ 30/2015 ድረስ ያለው የአሁኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ውል እስኪያልቅ ድረስ ውሉን ይፋ ባያደርጉትም በኢትዮጵያ ቡና የቀረበላቸውን 350 ሺህ ብር ያልተቀበሉትን አሰልጣኝ ውበቱ ከቀጣዮቹ ሶስት አመታት አጼዎቹን እንዲያሰለጥኑ ኢትዮጵያ ቡናዎች ካቀረቡት የተሻለ እስከ 400 ሺህ ብር አካባቢ እንዲከፈላቸው ሳይስማሙ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሹመትና ዝርዝር ስምምነት ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ይፋ የተደረገ መረጃ ባይኖርም የውል ስምምነታቸውን የሚገልጸው ሰነድ ባለፈው አርብ ፌዴሬሽን መግባቱን ከፌዴሬሽኑና ከክለቡ ታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በ250 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ እየሰሩበት ከነበረው የዋሊያዎቹ ሀላፊነታቸው ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት በስምምነት እንለያይ ጥያቄ በስምምነት ከተለያዩ በሳምንታት ውስጥ ከተሻለ የደመወዝ ክፍያ ጋር ጠንካራ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሀላፊነት ለመረከብ መስማማታቸው ታውቋል።

አሰልጣኙ ቡድኑን በደንብ እንዲያጠናክሩ የፈለጓቸውን ተጨዋቾች የማስቀረት ሌሎች ቡድኑን የሚያጠናክሩ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙ ሞቅ ያለ የዝውውር በጀት እንደተመደበላቸው የታወቀ ሲሆን በዲሲፕሊን ላይ ድርድር የማያውቁት አሰልጣኝ ውበቱ መልበሻ ቤቱን የመቆጣጠርና የመምራት ሙሉ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ ፋሲል ከነማን በአንደኛው አመት ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በሁለኛው አመት ወደ ሻምፒዮንነት እንዲመልሱ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በእቅድ ደረጃ ማሳወቃቸው የወጣው መረጃ ያስረዳል።


ፋሲል ከነማዎች በ2013 በፕሪሚየር ሊጉ ላይ የነገሱ ሲሆን በ2014 ሁለተኛ ሆነው ጨርሰዋል ክለቡ በ2015 አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽና አሰልጣኘ አሸናፊ በቀለን ቢሾምም በእስካሁኑ 28ኛ ሳምንት መርሀግብር በ39 ነጥብና 4 ግብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የፊታችን ዓርብ ሳምንት ሰኔ 23/2015 ደግሞ ከወረደው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር 29ኛ ሳምንት መርሀግብሩን ያካሂዳል።

ፋሲል ከነማ ቀጣዮቹን ሁለት ጨዋታዎችን ቢያሸንፍ እንኳ የሚደርሰው 45 ነጥብ ላይ በመሆኑ ከአራተኛነት የዘለለ ደረጃ እንደማይኖረው በመረጋገጡ የዝውውርና የሹመት ስራው ከአሁኑ ለቀጣዮቹ አመታት እየተዘጋጀ መሆኑን እንደሚያሳይ ከክለቡ ታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Hatrick Sport

@FASILSC
8.5K viewsedited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ