Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilsc — ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™
የሰርጥ አድራሻ: @fasilsc
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

የአፄዎቹ ፈጣን የመረጃ ምንጭ
The oldest and most popular Fasil Kenema Sport Club was established in 1960. This legendary Emperors Club has been around for 55 years.
🔴 ለአስተያየት @FASILKFCBOT

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 59

2022-08-31 08:40:40
241 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:38:46
አገኘሁ ተፈራን (አኩ) እናግዘው

እግርኳስን በመተሐራ ስኳር፣ ድሬዳዋ ፖሊስ፣ ናሽናል ሲሚንት፣ ወራቤ ከነማ፣ ሀምበሪቾ እና የካ ክ/ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን የጉልበት ጉዳት አጋጥሞት ከሚወደው ኳስ ጋር ተለያይቷል።

አኩ የሚወደውን እግርኳስ በተጨዋችነት ባይኖረውም በሌላ ዘርፍ ብቅ ብሎ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግን በውብ ምስሎቹ ለተከታዮቹ እያደረሰ ይገኛል።

ፎቶግራፈር አኩ ተጫዋቾችን ፎቶ አንስቶ በሚያገኘው ገቢ ጉልበቱን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቢያስብም አልተሳካም። ይባስ ብሎ ረጅም ሰአት የሚቆምበት ህመሙን አባብሶታል። ስለዚህ በቶሎ ቀዶ ጥገናውን ማድረግ ይኖርበታል።

አኩ ለህክምናው እስከ 120,000 ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ክራንች ሲይዝ እስከ ሦስት ወር ደግሞ ስራ አይሰራም።

አኩ ባለ ትዳር እና የአንድ ልጅ አባት መሆኑን ተከትሎ ሦስት ወር ስራ ካልሰራ ሊደርስበት የሚችለውን ጫና ታሳቢ በማድረግ የስፖርት ቤተሰቡ ይሄንን አመለ ሸጋ የሆነ ልጅ ወደ ጤንነቱ እንዲመለስ እንረባረብ


1000416117946
አገኘሁ ተፈራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ሼር በማድረግ ለሁሉም እናድርስ
3.6K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:22:54
#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽን በዋና አሰልጣኝነት ሹሟል!!

ኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ክለባችን ፋሲል ከነማ ከቀድሞ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በምክትል አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) እየተመራ በጥሩ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ገብቶ ከመሪው ክለብ ጋር የነበረውን ሰፊ የነጥብ ልዩነት በማጥበብ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በአስደናቂ ሁኔታ ማገባደዱ የሚታወስ ሲሆን የክለባችን የቦርድ አመራሮች በክለባችን ውስጥ በምክትል አሰልጣኝነት ለአራት አመት በማሳለፍ ያገለገለውን ባለብሩህ ተስፋ ሰጭ ወጣት አሰልጣኝ ለአንድ አመት በሚያቆይ ስምምነት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሉን አፅድቋል።

ፋሲል ከነማ በምክትል አሰልጣኝነት ሚና ሙሉቀን አቡሃይን ያስቀጠለ ሲሆን ክለባችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የአሰልጣኝ ዘማርያም ምክትል የነበረው እና ከዛም በዋና አሰልጣኝነት አፄዎቹን የመራው አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ደግሞ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በመሆን የአሰልጣኝ ቡድኑን የቀላቅሏል።

ከዋና አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ (ቲጋና) ጋር ስለ 2015 አመት የውድድር አመት የጨዋታ አቀራረብ፣ ስለ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ አጠቃላይ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ያቀረብነውን መጠይቅ ከዝግጅት ምስሎች ጋር በቅርቡ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

. #ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
6.1K views21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:22:39
#ፋሲል_ከነማ ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ አስፈርሟል!!

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ክለባችን ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን ለቀጣይ የ2015 አመት የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቡድኑን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቃል ደረጃ ከስምምነት ደርሶ የነበረውን ጋምቢያዊ ዜግነት ያለውን አጥቂ በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል፡፡

ፋሲል ከነማ ያስፈረመው አጥቂ ጋራይ ጆፋን ዜግነቱ ጋምቢያዊ ሲሆን እድሜው 24 ቁመቱ 1-82 ሲሆን በሀገሩ ጋምቢያ የጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ በእስራኤል እና ጆርጂያ ክለቦች ቀጥሎ በጥሩ አቋም ላይ እንዳሳለፈ መረጃዎች የሚገልፁ ሲሆን #ጆፋን ወጣት ፣ ፈጣን እና ባለክህሎት ተጫዋች በመሆኑ በክለባችን ውስጥ ትልቅ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ታምኖበት ለአንድ አመት በሚያቆይ ውል ፈርሟል።

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
6.5K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:37:23
አሠልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ በዋና አሠልጣኝነት ሚና ከፋሲል ከነማ ጋር በቀጣዩ ዓመት ለመቆየት ውላቸውን አድሰዋል።
በተጠናቀቀው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ከቀድሞ አሠልጣኙ ሥዩም ከበደ ጋር ተለያይቶ ዓመቱን በምክትል አሠልጣኙ ኃይሉ ነጋሽ እየተመራ ማገባደዱ ይታወቃል። በቀጣዩ ዓመት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ሀገራችንን የሚወክለው ቡድኑም ዝግጅቱን ባህር ዳር ከተማ ላይ መቀመጫውን በማድረግ እየሰራ ይገኛል።

ክለቡን በጊዜያዊነት እያሰለጠኑ የነበሩት አሠልጣኝ ኃይሉ ነጋሽም ከደቂቃዎች በፊት በዋና አሠልጣኝነት መንበር የአንድ ዓመት ውል መፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች የነበሩት አሠልጣኝ ኃይሉ ከ2010 ጀምሮ ክለቡን በምክትል አሠልጣኝነት ሲያገለግሉ እንደነበር አይዘነጋም። ከላይ እንደገለፅነውም ዘንድሮ ከአሠልጣኝ ሥዩም ስንብት በኋላ ክለቡን በጊዜያዊነት መርተው 2ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ረድተው ነበር። አሁን ደግሞ ለከርሞ በዋና አሠልጣኝነት ለመዝለቅ የአንድ ዓመት ፊርማቸውን አኑረዋል።

በምክትል አሠልጣኝነት ሚና ሙሉቀን አቡሀይ እንደሚቀጥሉ ሲገለፅ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የአሠልጣኝ ዘማርያም ምክትል የነበሩት እና ዋናው አሠልጣኝ ከቦታቸው ሲነሱ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በመንበሩ የቆዩት አሠልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ደግሞ የአካል ብቃት አሠልጣኝ ሆነው የአሠልጣኝ ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

@FASILSC
9.3K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:36:53

https://vm.tiktok.com/ZMNnbKpH5/
https://vm.tiktok.com/ZMNnbKpH5/
7.8K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 19:28:35 #የቀጠለ የስፖርት ዞን የ 2014ዓ.ም የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማነው ?
anonymous poll

ፍሪምፖንግ ሜንሱ – 297
46%

ይሁን እንደሻው – 286
44%

ዳዊት ተፈራ – 64
10%

647 people voted so far.
7.8K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 18:52:37
Gondar, Camelot City Of Africa

The former capital of Ethiopia, Gondar is famous for its imposing castles, built in the 17th and 18th centuries by several generations of Ethiopia’s kings. Once the seat of Ethiopian emperors, the walled Fasil Ghebbi fortress and palace compound contains the immense 17th-century castle of Emperor

Visit Gondar, Spend an unforgettable time

መናገሻዋን ጎንደር ይጎብኙ ፣ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ

@FASILSC
7.1K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:33:44
ሴሙኤል ዮሐንስ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል !

ከፋሲል ከነማ ጋር ውሉ የተጠናቀቀው የግራ መስመር ተከላካዩ ሳሙኤል ዮሐንስ ወደ አዲስ አደጊዎቹ ኢትዮጵያ መድኖች አምርቷል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች የነበረው ሳሙኤል ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ አሳልፎ እንደነበር አይዘነጋል። ዓምናም የሊጉን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ከፍ አድርጎ አንስቶ ነበር። አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል መዳረሻው ኢትዮጵያ መድን ሆኗል።

ሳሙኤል ዮሐንስ በሄድክበት ሁሉ መልካሙን እና ስኬት ይግጠምህ በክለባችን ለነበረህ ቆይታ በቻናላችን፣በክለቡ እና በደጋፊያችን ስም ከልብ እናመሰግናለን

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው
3.2K viewsedited  11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:39:16
4.8K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ