Get Mystery Box with random crypto!

እናመሰግናለን 'ይሄ ክብር ያንስብሃል ስዩም ዋርካው' አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በፋሲል ከነማ ቤት | ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ™

እናመሰግናለን

"ይሄ ክብር ያንስብሃል ስዩም ዋርካው"

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በፋሲል ከነማ ቤት ላስመዘገቡት የማይረሳ ህያው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ የክለቡ አንድ ደጋፊ ስፖንሰር አድርጓቸው በግሪክ በጉብኝት ላይ ነው።

የአሰልጣኙን የግሪክና የፈረንሳይ ጉዞ ሙሉ ወጭ የሸፈነው የፋሲል ከነማ የቦርድ አባል፣ የቶፕኬር ማኑፋክቼሪንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ አዱኛ ነው።

አሰልጣኝ ስዩም ፋሲል ከነማን የኢትዮጵያ ዋንጫና የኘሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ በማድረጋቸው ለአሰልጣኙ ይሄ ክብር የሚያንስ እንጅ የሚበዛ አለመሆኑን ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከባለቤታቸው ጋር በግሪኳ አቴንስ ከተማ በጉብኝትና በመዝናናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ነገ ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ የሚያቀኑ ይሆናል።

@FASILSC