Get Mystery Box with random crypto!

Fano Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanomedia24 — Fano Media F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanomedia24 — Fano Media
የሰርጥ አድራሻ: @fanomedia24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.42K
የሰርጥ መግለጫ

ፋኖነት የአባቶቻችን ውርስ መንገድ ነው።
https://t.me/FanoMedia24

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-13 21:49:39
1.4K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:49:28 #ሰበር_ዜና

ትጥቅ በፈቱ በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ።

ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት በሁለት መኪና ተጭነው ይጓዙ በነበሩ ትጥቅ የፈቱ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት የከፈተው ኦነግ ሸኔ መሆኑን ለፋኖ ሚዲያ መረጃውን ያደረሱ ምንጮች ገልጸዋል።እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ጥቃቱ የተከፈተባቸው፤ ገርቢና ባልጪ በተባለ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ ነው።

የጥቃቱንና የተጎጂዎችን መጠን ለማወቅ ከሚመለከተው የክልሉ ቢሮ ደጋግመን ያደረግነው ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም። ሆኖም እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የአማራ ልዩ ሀይል የህይወት መስዋዕት መክፈላቸውን ለማወቅ ችለናል።

በተያያዘ ዜና በወልቃይትና በራያ አላማጣ እና በኮረም በኩል ህወሓት ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ ሲሆን፤ በመተማ ዮሀንስ ሰፈር 4 የልማት ቦታ ደግሞ የሱዳን ጦር ዘልቆ መግባቱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።
1.4K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:21:37
1.6K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:08:33 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዶክተሬር ዲግሪ ለመሰረዝ የሚያበቃ መረጃ ተገኘ

ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዶክተሬት ዲግሪን ሊያሰርዝ የሚችል በቂ የጥናት “ስርቆት” ማስረጃ ማግኘቱን የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እ.ኤ.አ. በ2017 የዶክተሬት ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) ከተቀበሉበት ጊዜ አንስቶ፤ በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ የሕጋዊነት  ጥያቄዎች ሲነሱ እንደነበር ተቋሙ አስታውሷል፡፡

ፋውነዴሽኑ ከዚህ በፊት ጥያቄ ሲነሳበት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዶክተሬት ድግሪ ላይ ሰፊ ማጣራት በማድረግ ያገኘው ማስረጃ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥናት እንደገና ሊመረምር የሚችልበት በቂ ማስረጃ ማግኘቱን ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ የዶክትሬት ዲግሪውን ለማገድ ወይም ለመሻር በቂ ነው ያለውን ማስረጃ ሲያቀርብ፤ በሌሎች ጥናቶች ላይ የተጠቀሱ ጽሑፎች በቀጥታና በጥቂት ማሻሻያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናት ላይ ተደግመው መገኘታቸው በማስረጃ አስደግፎ አብራርቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት መመረቂያ ፅሑፍ ላይ “የሌብነት” ምልክቶች እንዳሉ ባደረገው ማጠራት መታዘቡን ፋውንዴሽኑ ይፋ ባደረገበት ጽሑፍ ላይ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጉዳዩን እንደገና ሊመለከት የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁሟል፡፡

በዚህም ዩኒቨርስቲው ፕላጂያሪዝምን ወይም የሰው ጥናት ስርቆትን በሚከለክለው አሰራር እንደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መሰረዝ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡ በኹለተኛ ደረጃ እንደ አማራጭ የተጠቆመው፤ ጥናቱ እንደገና ተሻሽሎ ድጋሚ እንዲሰራ በማድረግ እሰከዚያው የዶክተሬት ዲግሪ ማገድ ነው፡፡

የመመረቂያ ጥናቱ “Social Capital and its Role in Traditional Conflict Resolution: The Case of Inter-religious Conflict in Jimma Zone of the Oromia Regional State in Ethiopia” በሚል ርዕስ የተሰራ ሲሆን፤ የጥናቱ ትኩርት ማኅበራዊ ካፒታል በባህላዊ የግጭት አፈታት ውስጥ ያለው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

“ፕላጂያሪዝም” የሰውን ጽሑፍ ወይም ሥራ መስረቅ ወይም የራስ አስመስሎ ማቀረብ የሚል ተቀራራቢ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናትም ይህ አይነቱ ችግር እንደታየበት ፋይንደሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ጽሑፍ አስታውቋል፡፡

የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት ዲግሪ ላይ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች ለመመልከት https://t.co/rnnNneqRIl
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:https://t.me/ethiotube
1.7K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:03:45 ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ተባለ!

በኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይሎች ጠቅለው መውጣታቸውን እንዲሁም የፋኖን መበተን ተከትሎ ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ሲሉ በሥፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡በዚህም ህብረተሰቡ ተረብሿል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ “የመከላከያ ሠራዊት እኛ አለን ተረጋጉ እያለ ቢሆንም፣ መንግሥት እያደረገ ያለው እና በህወሓት በኩል እየተወራ ያለው የተናበበ ስለሆነ ህዝቡ ማመን አልቻለም።” ብለዋል፡፡

ህወሓት “የአማራ ልዩ ኃይል ከኮረምና አላማጣ ከወጣ እና ፋኖ ከተበተነ መከላከያ ቦታውን ተረክቦ ቆይቶ ለትግራይ ክልል ይመልሳል” ሲል ነው የከረመው ያሉት ነዋሪዎች፤ “የፌደራል መንግሥቱም ይህን እያስፈጸመ እንዳለ ነው የምናምነው።” በማለት ያላቸውን ከፍተኛ ስጋት ገልጸዋል፡፡መንግሥት ኮረምና አላማጣን ለህወሓት አሳልፎ ለመስጠት በእርግጠኝነት እኛ የማናውቀው ሴራ እየሰራ እንደሆነ ነው የምናምነውም ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ለገበያ ከሚመጡ የማይጨው ነዋሪዎች እንዲሁም እየደወሉ አመራርና ፖሊስ ተመድቦልናል በቅርቡ ወደ ቦታችሁ ትሄዳላችሁ ተብለናል ከሚሉ ሰዎች አረጋግጠናል ባሉት መሰረት፤ ህወሓት በአማጣና ኮረም ለሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ካቢኔ አዋቅሮና ፖሊስ መድቦ ጨርሷል ብለዋል፡፡

ኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ትናንት ጠቅልለው መውጣታቸውን ጠቁመው፤ አላማጣ ውስጥ ያሉት የአማራ ልዩ ኃይልም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይወጣል ነው ያሉት፡፡ወልድያ ከተማ የሚገኙ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ወደ መከላከያ ሠራዊት አልያም ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ደግሞ ወደ ክልል ፖሊስ ለመግባት ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡

[Addis Maleda]
@FanoMedia24
1.5K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:19:37 ሱዳን..!

የሱዳን ወራሪ ጦር የወያኔ ጦርነት ከተጀመረ (Nov 2020) ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር 50 ኪሎሜትር ዘልቆ ገብቶ መውረሩ ይታወሳል። ከዛ በኋላ የአማራ ልዮ ኃይል ድንበር ጠባቂ ሆኖ ሰፍሮ በመኖሩ የሱዳን ጦርነት ወደፊት መግፋት አልቻለም ነበር።

አሁን የአማራ ልዮ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር መነሳቱን ተከትሎ በዚህ 2ና 3 ቀናት የሱዳን ጦር ይዞታውን በእጅጉ እንዳሰፋ ተነግሯል።
1.8K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:06:41
1.8K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:06:34 "ትጥቅ ፍቱ" በተባለበት በዚህ ወቅት ባለፉት አርባ ዓመታት ስሁት ትርክት ፈጥሮ፣ ለዚህ ማስፈጸሚያ ፓኬጅ ቀርጾ፣ ስነልቦናዊ፣ ሰብዓዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሥነ ብዕላዊ  ቀውስ እና  የዘር ማጥፋት ወንጀል በዐማራው ላይ የፈጸመው ሕወሓት ራያን መልሶ ለመውረር ኮረም ላይ ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሷል።  በአካሉ አብርሃና ሀጎስ መስፍን የሚመራ የሕወሓት ኃይል ቆላ ተንቤን የደበቀውን መሳሪያ ይዞ በጠለምት በኩል ወረራ ፈጽሟል። ዘመናዊ ትጥቅ የነበረውና ትጥቁን ያልፈታው በሱዳን የሚገኘው የሕወሓት ቡድን ሸረሪና ላይ መሽጎ ይገኛል። የዐማራ ህዝብ ቢያንስ በስነልቦና ተዘጋጅቶና ተነቃቅቶ ራሱን አደራጅቶ እንዳይጠብቅ "የትጥቅ ፍቱ" አጀንዳ አምጥተው ኅብረሰተሰባዊ እረፍት ነስተውታል። ሕወሓት በበኩሉ የአሸባሪነቱን መዝገብ ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር በመተባበር ከአስረዘ በኋላ እንደገና አፈር ልሶ ተነስቷል። ልዩ ኃይላችን ደግሞ ትጥቅ ይፍታ ተብሏል።

@FanoMedia24
1.7K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:00:36 ከአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ሕዝብን ትጥቅ በማስፈታት የዘር ፍጅት ለመፈጸም የተደረገው ጅምር ተግባር በተባበረ የከተማ አመጽ እና ህዝባዊ እምቢተኝነት  ልዩ ኃይላችን ከሞላ ጎደል መታደግ ተችሏል።ይህ የምዕራፍ አንድ እንቅስቃሴ ያስገኘው ውጤት እጅግ ማራኪ ነበር። ውጤቶችም ፦

ሀ/ ህዝባችን የደረሰበትን በደል ተረድቶ በአንድነት መቆም መቻሉ እና መንግስታዊ ሰርዓቱን  በቃን ለማለትና ትግሉን ለማቀጣጠል ያለው ቁርጠኝነት አሳይቷል ።

ለ/ ሁሉም የክልሉ ከተሞች መንገድ በመዝጋት በመንግስት  ላይ  ከፍተኛ ተፅዕኖ  መፍጠር ተችሏል  ።

ሐ/ የልዩ ኃይላችን ከመበተንና ትጥቅ ከመፍታት መታደግ መቻሉ

መ/ ለልዩ ኃይላችን ምግብና ውኃ እንዲሁም የትራንስፓርት አገልግሎት ማቅረብ የተደረገው እንቅስቃሴ በጠንካራነት ታይቷል

ሠ/ እንደ ወሎ ፣ሸዋ ወዘተ  ከመከላከያ ሠራዊት ጋር የተደረገው ትንቅንቅ  አሸንፈን  መውጣት ተችሏል ።
እና መሰል ተግባራት በመልካም የተገመገሙ ሲሆን  መንግስታዊው የአማራ ልዩ ሀይልን የማፍረስ ፣ክንድህን የማስጣል  እና በቀጣይ ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ የዘር ማጥፋት  ድርጊቱን ለማሰፈፀም  የጀመረው ድንገት በአንድ ሌሊት በመሆኑ አስተባባሪው በአካል ተገናኝቶ የመምከር እና ውሳኔዎችን ቶሎ ቶሎ አለመስጠት እንደ ችግር ታይተዋል።

በመሆኑም  ምዕራፍ ሁለት  እንቅስቃሴን  ለማስጀመር የህዝባዊ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል። ስለሆነም ህዝባችን በፆምና ፀሎት  ውስጥ ሆኖ   ፤የህልውና ችግር ላይ ፤ የመኖር እና ያለመኖር የዋስትና አደጋ ላይ ሆኖም በጉጉት የሚጠብቃቸውን የፋሲካ እና የኢድ አልፈጥር በዓላትን እንደተለመደው ባይሆንም በሰላም አክብሮ  እንዲያሳልፍ የከተማ ውስጥ አመፁ  እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱ  ከነገ ሚያዚያ 5/2015  ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም ተወስኗል።

በመሆኑም ፦
1/  የአማራ ህዝብ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በእዬ ከተሞች መንገድ የተዘጋባቸው ድንጋይ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በማንሳት ከተሞችን የማጽዳትና ሠላሙን የማስጠበቅ ስራ እንዲሰራ፤

2/ መንግስት የተጠየቀውን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ካልሰጠ በቀጣይ የሚሰጡ ተግባራትን ለመፈጸም እንዲዘጋጅ

3/ የልዩ ኃይል አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ባሉበት ሆነው ለሚሰጠው ተልዕኮ እንዲጠብቁ

4/ የመንግስት አካላት የህዝባዊ አመጹን አስተባብረዋል በሚል የጠረጠራቸውን ወጣቶች ከማንገላታት እንዲታቀብ ይህን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ካሉም እርምጃ እንዲወሰድባቸው

5/ የአገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት አባቶች የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ትሆኑ ዘንድ መልዕክት ተላልፏል። ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነው ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ፣ፍትህ እና እኩልነት ነው ።

    (የአማራ ሕዝብ ኮሚቴ )

@FanoMedia24
2.7K viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 11:57:59
1.6K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ