Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ተባለ! በኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይሎች | Fano Media

ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ተባለ!

በኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይሎች ጠቅለው መውጣታቸውን እንዲሁም የፋኖን መበተን ተከትሎ ህወሓት ለኮረምና አላማጣ አመራር በመመደብ ላይ ነው ሲሉ በሥፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡በዚህም ህብረተሰቡ ተረብሿል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ “የመከላከያ ሠራዊት እኛ አለን ተረጋጉ እያለ ቢሆንም፣ መንግሥት እያደረገ ያለው እና በህወሓት በኩል እየተወራ ያለው የተናበበ ስለሆነ ህዝቡ ማመን አልቻለም።” ብለዋል፡፡

ህወሓት “የአማራ ልዩ ኃይል ከኮረምና አላማጣ ከወጣ እና ፋኖ ከተበተነ መከላከያ ቦታውን ተረክቦ ቆይቶ ለትግራይ ክልል ይመልሳል” ሲል ነው የከረመው ያሉት ነዋሪዎች፤ “የፌደራል መንግሥቱም ይህን እያስፈጸመ እንዳለ ነው የምናምነው።” በማለት ያላቸውን ከፍተኛ ስጋት ገልጸዋል፡፡መንግሥት ኮረምና አላማጣን ለህወሓት አሳልፎ ለመስጠት በእርግጠኝነት እኛ የማናውቀው ሴራ እየሰራ እንደሆነ ነው የምናምነውም ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ለገበያ ከሚመጡ የማይጨው ነዋሪዎች እንዲሁም እየደወሉ አመራርና ፖሊስ ተመድቦልናል በቅርቡ ወደ ቦታችሁ ትሄዳላችሁ ተብለናል ከሚሉ ሰዎች አረጋግጠናል ባሉት መሰረት፤ ህወሓት በአማጣና ኮረም ለሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ካቢኔ አዋቅሮና ፖሊስ መድቦ ጨርሷል ብለዋል፡፡

ኮረም የነበሩ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ትናንት ጠቅልለው መውጣታቸውን ጠቁመው፤ አላማጣ ውስጥ ያሉት የአማራ ልዩ ኃይልም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይወጣል ነው ያሉት፡፡ወልድያ ከተማ የሚገኙ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ወደ መከላከያ ሠራዊት አልያም ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ደግሞ ወደ ክልል ፖሊስ ለመግባት ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡

[Addis Maleda]
@FanoMedia24