Get Mystery Box with random crypto!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዶክተሬር ዲግሪ ለመሰረዝ የሚያበቃ መረጃ ተገኘ ጥያቄ ሲነሳበ | Fano Media

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዶክተሬር ዲግሪ ለመሰረዝ የሚያበቃ መረጃ ተገኘ

ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዶክተሬት ዲግሪን ሊያሰርዝ የሚችል በቂ የጥናት “ስርቆት” ማስረጃ ማግኘቱን የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እ.ኤ.አ. በ2017 የዶክተሬት ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) ከተቀበሉበት ጊዜ አንስቶ፤ በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ የሕጋዊነት  ጥያቄዎች ሲነሱ እንደነበር ተቋሙ አስታውሷል፡፡

ፋውነዴሽኑ ከዚህ በፊት ጥያቄ ሲነሳበት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዶክተሬት ድግሪ ላይ ሰፊ ማጣራት በማድረግ ያገኘው ማስረጃ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥናት እንደገና ሊመረምር የሚችልበት በቂ ማስረጃ ማግኘቱን ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ የዶክትሬት ዲግሪውን ለማገድ ወይም ለመሻር በቂ ነው ያለውን ማስረጃ ሲያቀርብ፤ በሌሎች ጥናቶች ላይ የተጠቀሱ ጽሑፎች በቀጥታና በጥቂት ማሻሻያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናት ላይ ተደግመው መገኘታቸው በማስረጃ አስደግፎ አብራርቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት መመረቂያ ፅሑፍ ላይ “የሌብነት” ምልክቶች እንዳሉ ባደረገው ማጠራት መታዘቡን ፋውንዴሽኑ ይፋ ባደረገበት ጽሑፍ ላይ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጉዳዩን እንደገና ሊመለከት የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁሟል፡፡

በዚህም ዩኒቨርስቲው ፕላጂያሪዝምን ወይም የሰው ጥናት ስርቆትን በሚከለክለው አሰራር እንደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መሰረዝ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡ በኹለተኛ ደረጃ እንደ አማራጭ የተጠቆመው፤ ጥናቱ እንደገና ተሻሽሎ ድጋሚ እንዲሰራ በማድረግ እሰከዚያው የዶክተሬት ዲግሪ ማገድ ነው፡፡

የመመረቂያ ጥናቱ “Social Capital and its Role in Traditional Conflict Resolution: The Case of Inter-religious Conflict in Jimma Zone of the Oromia Regional State in Ethiopia” በሚል ርዕስ የተሰራ ሲሆን፤ የጥናቱ ትኩርት ማኅበራዊ ካፒታል በባህላዊ የግጭት አፈታት ውስጥ ያለው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

“ፕላጂያሪዝም” የሰውን ጽሑፍ ወይም ሥራ መስረቅ ወይም የራስ አስመስሎ ማቀረብ የሚል ተቀራራቢ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናትም ይህ አይነቱ ችግር እንደታየበት ፋይንደሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ጽሑፍ አስታውቋል፡፡

የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተሬት ዲግሪ ላይ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች ለመመልከት https://t.co/rnnNneqRIl
YouTube: https://youtube.com/ethiotube
Instagram: https://instagram.com/ethiotube
Twitter: https://twitter.com/EthioTube
Facebook: https://facebook.com/EthioTube
Telegram:https://t.me/ethiotube