Get Mystery Box with random crypto!

ከአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ! የአማራ ሕዝብን ትጥቅ በማስፈታት የዘር ፍጅት ለመፈጸም የ | Fano Media

ከአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ሕዝብን ትጥቅ በማስፈታት የዘር ፍጅት ለመፈጸም የተደረገው ጅምር ተግባር በተባበረ የከተማ አመጽ እና ህዝባዊ እምቢተኝነት  ልዩ ኃይላችን ከሞላ ጎደል መታደግ ተችሏል።ይህ የምዕራፍ አንድ እንቅስቃሴ ያስገኘው ውጤት እጅግ ማራኪ ነበር። ውጤቶችም ፦

ሀ/ ህዝባችን የደረሰበትን በደል ተረድቶ በአንድነት መቆም መቻሉ እና መንግስታዊ ሰርዓቱን  በቃን ለማለትና ትግሉን ለማቀጣጠል ያለው ቁርጠኝነት አሳይቷል ።

ለ/ ሁሉም የክልሉ ከተሞች መንገድ በመዝጋት በመንግስት  ላይ  ከፍተኛ ተፅዕኖ  መፍጠር ተችሏል  ።

ሐ/ የልዩ ኃይላችን ከመበተንና ትጥቅ ከመፍታት መታደግ መቻሉ

መ/ ለልዩ ኃይላችን ምግብና ውኃ እንዲሁም የትራንስፓርት አገልግሎት ማቅረብ የተደረገው እንቅስቃሴ በጠንካራነት ታይቷል

ሠ/ እንደ ወሎ ፣ሸዋ ወዘተ  ከመከላከያ ሠራዊት ጋር የተደረገው ትንቅንቅ  አሸንፈን  መውጣት ተችሏል ።
እና መሰል ተግባራት በመልካም የተገመገሙ ሲሆን  መንግስታዊው የአማራ ልዩ ሀይልን የማፍረስ ፣ክንድህን የማስጣል  እና በቀጣይ ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ የዘር ማጥፋት  ድርጊቱን ለማሰፈፀም  የጀመረው ድንገት በአንድ ሌሊት በመሆኑ አስተባባሪው በአካል ተገናኝቶ የመምከር እና ውሳኔዎችን ቶሎ ቶሎ አለመስጠት እንደ ችግር ታይተዋል።

በመሆኑም  ምዕራፍ ሁለት  እንቅስቃሴን  ለማስጀመር የህዝባዊ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል። ስለሆነም ህዝባችን በፆምና ፀሎት  ውስጥ ሆኖ   ፤የህልውና ችግር ላይ ፤ የመኖር እና ያለመኖር የዋስትና አደጋ ላይ ሆኖም በጉጉት የሚጠብቃቸውን የፋሲካ እና የኢድ አልፈጥር በዓላትን እንደተለመደው ባይሆንም በሰላም አክብሮ  እንዲያሳልፍ የከተማ ውስጥ አመፁ  እና ህዝባዊ እምቢተኝነቱ  ከነገ ሚያዚያ 5/2015  ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም ተወስኗል።

በመሆኑም ፦
1/  የአማራ ህዝብ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በእዬ ከተሞች መንገድ የተዘጋባቸው ድንጋይ እና ሌሎች ቁሳቁሶች በማንሳት ከተሞችን የማጽዳትና ሠላሙን የማስጠበቅ ስራ እንዲሰራ፤

2/ መንግስት የተጠየቀውን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ካልሰጠ በቀጣይ የሚሰጡ ተግባራትን ለመፈጸም እንዲዘጋጅ

3/ የልዩ ኃይል አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ባሉበት ሆነው ለሚሰጠው ተልዕኮ እንዲጠብቁ

4/ የመንግስት አካላት የህዝባዊ አመጹን አስተባብረዋል በሚል የጠረጠራቸውን ወጣቶች ከማንገላታት እንዲታቀብ ይህን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ካሉም እርምጃ እንዲወሰድባቸው

5/ የአገር ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት አባቶች የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ትሆኑ ዘንድ መልዕክት ተላልፏል። ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነው ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ፣ፍትህ እና እኩልነት ነው ።

    (የአማራ ሕዝብ ኮሚቴ )

@FanoMedia24