Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር_ዜና ትጥቅ በፈቱ በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ። ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት | Fano Media

#ሰበር_ዜና

ትጥቅ በፈቱ በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ።

ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት በሁለት መኪና ተጭነው ይጓዙ በነበሩ ትጥቅ የፈቱ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት የከፈተው ኦነግ ሸኔ መሆኑን ለፋኖ ሚዲያ መረጃውን ያደረሱ ምንጮች ገልጸዋል።እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ጥቃቱ የተከፈተባቸው፤ ገርቢና ባልጪ በተባለ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ ነው።

የጥቃቱንና የተጎጂዎችን መጠን ለማወቅ ከሚመለከተው የክልሉ ቢሮ ደጋግመን ያደረግነው ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም። ሆኖም እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የአማራ ልዩ ሀይል የህይወት መስዋዕት መክፈላቸውን ለማወቅ ችለናል።

በተያያዘ ዜና በወልቃይትና በራያ አላማጣ እና በኮረም በኩል ህወሓት ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ ሲሆን፤ በመተማ ዮሀንስ ሰፈር 4 የልማት ቦታ ደግሞ የሱዳን ጦር ዘልቆ መግባቱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።