Get Mystery Box with random crypto!

✟የማለዳ ፀሀይ✟

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewkete_orthodox — ✟የማለዳ ፀሀይ✟
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewkete_orthodox — ✟የማለዳ ፀሀይ✟
የሰርጥ አድራሻ: @ewkete_orthodox
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

✝️የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ ይህ ቻናል የተከፈተበት ዋናው ምክንያት ህልውናችን የሆነችውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያልተመረመሩና ያልተነገሩላትን ታላላቅ እውቀቶቿን እና ትምህርቶቿን ለመማማር ነው።
ስለዚህም በእግዚያብሔር ስም ይህን ቻናል ለኦርቶዶክሳዊያን እውቀቷን ለሚሹ ቤተሰቦቻችሁ share በማድረግ ሁላችንም እንማማር ሀይማኖታችንን እንወቅ።👇
@ewkete_orthodox
@ewkete_orthodox

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-10-12 22:11:34


የትኛውን መጽሐፍ በPDF ይፈልጋሉ





█ ድርሳናት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ ገድላት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ ተዓምራት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ መልከዐት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ ውዳሴ ማርያም
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ መዝሙረ ዳዊት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ ህማማት
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ መፅሀፈ ቅዳሴ
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ የሰዶም መጨረሻ
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ ባህረ ሀሳብ
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ የሳጥናኤል ጎል
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵
█ አንድሮሜዳ
▓⇨→ 𝑶𝑷𝑬𝑵


◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▣ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ◄░▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▣ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ◄░▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▣ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ◄░▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▣ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ◄░▒▓█
12 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 21:18:26 #መስከረም_29

#ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

በዚችም ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕት ቅድስት አርሴማ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_መስከረም)
https://t.me/joinchat/D8TC9g_CJ-plM2U8
177 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-02 20:22:37 አንተ ክርስቲያን ከኾንህ፥ ከምድራውያን ከተሞች (አገሮች) አንዲትዋስ እንኳን የአንተ አይደለችም፡፡ [አንዲት ከተማስ ይቅርና] ምድርን በሞላ በእጃችን ጭብጥ በእግራችን እርግጥ ብናደርጋትም እንኳን፥ አሁንም ቢኾን መጻተኞችና እንግዶች ነን፡፡ አገራችን በላይ በሰማይ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@ewkete_orthodox
@ewkete_orthodox
494 views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 13:15:02
የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
#share & join
subscribe  
@ewkete_orthodox
@ewkete_orthodox
subscribe  
675 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 11:47:46
551 views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 08:08:26 የደመራ ዓመት

መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው
ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው
ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ
ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራ

ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩ

ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ
በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ
ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው
ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?

ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ
ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
በዕጣን ያልተገኘ ጌታ ያልሞተበት
ቅርፁ መስቀል ሆኖ መዳን የሌለበት
የወንበዴው መስቀል መስቀሉ መስሏቸው
ስንቶች ትተው ሔዱ ከእሌኒ እናታቸው?

ዓለም የዳነበት መስቀሉን ጨብጦ
ስለዘር የሚሰብክ እጅግ ተመስጦ
የተቃጠለውን መቅደስዋን እያየ
"ራስሽን አድኝ" ሲል ሲስቅ የታየ
ዘንድሮ አይደለም ወይ አይሁዱ የለየ?

ዘንድሮ ከበረ ለአንድ ዓመት ደመራ
በማያቆም ጥቃት በማያቆም ሴራ
ቅድስት ተዋሕዶ በጭንቅ ተወጥራ
አባቶችዋን ከፊት እንደ ጦር ሰድራ
በልጆችዋ ጩኸት በገና ደርድራ

በሰማዕታትዋ ደም ተረጭታና ርሳ
በየአደባባዩ ምሕላን አድርሳ
በፓትርያርክዋ ዓይን በምሬት አልቅሳ
እንደ ራሔል ለአምላክ ዕንባዋን አፍስሳ

ለመስቀሉ ቀን ግን ነጭ ልብስዋን ለብሳ
እንደ ቆስጠንጢኖስ በድል ልትነሣ
አምላክዋን ከፍ አድርጋ ኀዘንዋን ልትረሳ
ተስፋ ያደረገችው በመስቀል ታድሳ

ዘንድሮ ነው በዓል ዘንድሮ ደመራ
በዚህ ዓመት ተገኘን ከመስቀሉ ሥፍራ!!
515 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 07:46:12 ++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
532 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 09:59:58
እናቴ አማላጄ ወዳጄ መጠጊያዬ ተስፋዬ ብርሀኔ
አረ ምኔ ብልሽ ምን ይገልፅሻል
626 viewsedited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-23 13:41:58 "እኔስ ክርስቲያን እንድባል ክርስቲያን ሁኜም እንድኖር እወዳለሁ:: እንደ አባቶቼ ሐዋርያት ትምህርት በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ክርስቲያን ሁኜ እንድውል ክርስቲያንም ሁኜ እንዳድር እወዳለሁ:: እንደ አባቶቼ ሐዋርያት ክርስቲያን ሁኜ በመቃብር ውስጥ እንዳንቀላፋ እወዳለሁ:: በትንሣኤዬም ከአባቶቼ ሐዋርያት ጋር ክርስቲያን ሁኜ እንድነቃ እወዳለሁ:: በጽዮን ተራራም በአባቶቼ ሐዋርያት እቅፍ ውስጥ እንዳርፍ እወዳለሁ::"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
@ewkete_orthodox
609 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 08:36:37 ✞ ኦ ቅዱስ ሚካኤል

ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል
ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል
ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን
ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)

እረቂቁመላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል
ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል
የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ
እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2)

አዝ__________________

እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት
ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት
ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው
ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)

አዝ__________________

እርህሩነው እና የነፍሳችን ወዳጅ
ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ
ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ
ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2)

አዝ__________________

የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ
በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ
በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ
ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2)


ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE
372 views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ