Get Mystery Box with random crypto!

✞ ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምና | ✟የማለዳ ፀሀይ✟

✞ ኦ ቅዱስ ሚካኤል

ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል
ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል
ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን
ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)

እረቂቁመላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል
ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል
የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ
እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2)

አዝ__________________

እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት
ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት
ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው
ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)

አዝ__________________

እርህሩነው እና የነፍሳችን ወዳጅ
ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ
ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ
ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2)

አዝ__________________

የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ
በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ
በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ
ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2)


ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE