Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ሚካኤል:- አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚ | ✟የማለዳ ፀሀይ✟

ቅዱስ ሚካኤል:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው::

በዚህች ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው::

ኢሳይያስም መልአኩ እንደነገረው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሔዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለው ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው::

ሚስት አግብቶም ምናሴን እስከ ወለደው ድረስ በተጨመረለት ዕድሜ እያመሰገነ ስለኖረ እንዲህ ሆነ::

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ቸርነት አያችሁን!

አብቅቶልአል በቃ ልትሞት ነው ብሎ ብቻ አይተወንም:: መልአኩን ልኮ ይመክረናል::

በተለያዩ መምህራን በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ እያባበለ አስተምሮ ይመክረናል::

ሰምተንም በቶሎ ስለ ኃጢአታችን ተጸጽተን ንስሐ ስንገባ በዕድሜአችን ላይ አምስት ዐሥር ዐሥራ አምስት ሠላሳ ከዚያም በላይ ዓመት ይጨምርልናል::

ከእኛ የሚጠበቀ ስለ ሠራናት ኃጢአት መናዘዝ ስለተደረገልን ነገር ማመስገን ብቻ ነው::

በእውነት ፍጹም ፍቅሩን ከእኛ ያላራቀ የቅዱሳኑ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን::
@ewkete_orthodox