Get Mystery Box with random crypto!

✟የማለዳ ፀሀይ✟

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewkete_orthodox — ✟የማለዳ ፀሀይ✟
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewkete_orthodox — ✟የማለዳ ፀሀይ✟
የሰርጥ አድራሻ: @ewkete_orthodox
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

✝️የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ ይህ ቻናል የተከፈተበት ዋናው ምክንያት ህልውናችን የሆነችውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያልተመረመሩና ያልተነገሩላትን ታላላቅ እውቀቶቿን እና ትምህርቶቿን ለመማማር ነው።
ስለዚህም በእግዚያብሔር ስም ይህን ቻናል ለኦርቶዶክሳዊያን እውቀቷን ለሚሹ ቤተሰቦቻችሁ share በማድረግ ሁላችንም እንማማር ሀይማኖታችንን እንወቅ።👇
@ewkete_orthodox
@ewkete_orthodox

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2021-09-22 08:27:07 ቅዱስ ሚካኤል:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው::

በዚህች ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው::

ኢሳይያስም መልአኩ እንደነገረው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሔዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለው ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው::

ሚስት አግብቶም ምናሴን እስከ ወለደው ድረስ በተጨመረለት ዕድሜ እያመሰገነ ስለኖረ እንዲህ ሆነ::

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ቸርነት አያችሁን!

አብቅቶልአል በቃ ልትሞት ነው ብሎ ብቻ አይተወንም:: መልአኩን ልኮ ይመክረናል::

በተለያዩ መምህራን በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ እያባበለ አስተምሮ ይመክረናል::

ሰምተንም በቶሎ ስለ ኃጢአታችን ተጸጽተን ንስሐ ስንገባ በዕድሜአችን ላይ አምስት ዐሥር ዐሥራ አምስት ሠላሳ ከዚያም በላይ ዓመት ይጨምርልናል::

ከእኛ የሚጠበቀ ስለ ሠራናት ኃጢአት መናዘዝ ስለተደረገልን ነገር ማመስገን ብቻ ነው::

በእውነት ፍጹም ፍቅሩን ከእኛ ያላራቀ የቅዱሳኑ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን::
@ewkete_orthodox
579 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 13:01:25
608 views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 13:01:24
589 views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 19:47:04
671 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 11:13:35
ስዕል አድኖዎችን ለይተን እንወቅ
በመምህር ተስፋዬ
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
•➢ ሼር // SHARE//SUBSCRIBE
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ewkete_orthodox
@Ewkete_orthodox
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
830 viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 11:13:16 + ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል? +

"ከረሃብ ሰይፍ ይሻላል" የሚል የአበው ብሂል ቢኖርም አሁን ሁለቱም እሳቶች ወገናችንን እየፈጁ ነው:: ከጦርነት እሳት ያመለጠውን የረሃብ እሳት ይቀበለዋል:: ረሃብን በምን ቃል እንግለጸው? በዚህች ደቂቃ ውስጥ አንተ ይሄን ጽሑፍ ስታነብ በረሃብ አለንጋ ክፉኛ ተገርፎ እያሸለበ ያለ ብዙ ወገን አለ:: ስንፍና ሳይጫነው ከአፈር እየታገለ ልጆቹን ሲያሳድግ ኖሮ ድንገት ጦርነት አፈናቅሎት ለልመና የተዳረገ ረሃብ ልጆቹን ሲነጥቀው ቆሞ የሚያይ ወገን በሰሜን ኢትዮጵያ እጅግ ብዙ ነው:: በፖለቲካ ድንበር የተለያየው ምኑንም የማያውቀው መከረኛ ሕዝብ አሁን በረሃብ ግን አንድ ሆኖአል:: በግራና ቀኝ በኢንተርኔት ተሰልፎ የሚሰዳደበው የሩቅ ጦረኛ ቁርሱን ምሳውን ራቱን ጥርግ አድርጎ በልቶ ነው:: መሬት ላይ ግን መከረኛው ሕዝባችን አንድ ላይ እየተራበ ነው::

ረሃብን ለመግለጽ ምን ቃል አለ?? ነፍሳቸውን ይማርና ሁለቱ ዕንቁ ደራስያን ጋሽ ጸጋዬ እና ጋሽ ስብሐት እንዲህ ብለው ነበር :-

ረሃብ ቀጠሮ ይሰጣል?
ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል?
“የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል”
ይባላል፣ ድሮም ይባላል
ይዘለዝላል ይከትፋል
ብቻ እስከሚጨርስ ድረስ ሆድ ለሆድ ጊዜ ይሰጣል?

ወተት አንጀት ነጥፎ ሲላብ
ሆድ ዕቃ ደርቆ ሆድ ሲራብ
ተሟጦ አንጀት በአንጀት ሲሳብ …

የጣር ቀጠሮው ስንት ነው?
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው?
ላይችል ሰጥቶ ለሚያስችለው?
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

"የተራቡ ልጆች አባት ምሬት :-

አበላቸው እህል ከልክለህ አምስት ልጆች የሠጠኸኝ ምነው?

አምስት ልጅ ተሰብስቦ አንድ ላይ ሲውል አንዲት ሳቅ ብቅ ሳትል መምሸቱ ምነው?

ልጆቼ አንዲት ቀን እንኳን አኩኩሉ ሳይጫወቱ ማለቃቸው ምነው?

ልጆቼን በአንድ ቀን ስቀብር ዝም ብለህ ማየትህ ምነው?"

(ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር)

በያለንበት ለምግብ በተቀመጥን ጊዜ እያንዳንዱ ጉርሻ የሆነን ሰው ዕድሜ ሊያራዝም ይችል እንደነበረ እናስብ::
ጠጥተን የምንታጠብበትን ውኃ አጥቶ በዚህች ቅጽበት የሚያሸልብ ወገናችንን አንርሳ:: ደግመን እንላለን ጦርነት ክፉ ነው:: ረሃብ ደግሞ የባሰ ነው:: ሀገራችንን ከሁለቱም ዕረፍት ትፈልጋለች:: እስከዚያው ግን ለወገኖቻችን በየአቅጣጫው እንረባረብ!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 3 2014 ዓ.ም.
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
•➢ ሼር // SHARE//SUBSCRIBE
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ewkete_orthodox
@Ewkete_orthodox
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
983 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-14 21:01:01 ወዳጄ ሆይ፦
ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛቆሮ.10፥31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
•➢ ሼር // SHARE//SUBSCRIBE
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ewkete_orthodox
@Ewkete_orthodox
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
799 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-14 09:41:31 + ጌታ ያልተወለደባት ሥፍራ +

ጌታችን በተወለደባት ከተማ ቤተልሔም በተደጋጋሚ በአስጎብኚነት ሔጄ ተሳልሜያለሁ:: የተቀደሰችውን ጌታ የተወለደባትንና ኮከብ የቆመባትን ሥፍራ በተሳለምኩ ቁጥር ግን ሁሌ ትዝ የሚለኝ አንድ የዓለማችን ቁጥር አንድ ዕድለ ቢስ ቦታ አለ::

የዓለም መድኃኒት የተኛበትን በረት በሰልፍ የዓለም ሕዝብ ቆሞ ሲሳለም የቱ ጋር እንደሆነ ባላውቅም ትዝ እያለኝ የሚያሳዝነኝ አፍ ቢኖረው ጮኾ የሚያለቅስ አንድ ቦታ አለ:: ስለቦታው ላስታውሳችሁ::

ጌታን ለመወለድ የቀረበችው ድንግል ማርያምና ዮሴፍ በዚያች ምሽት ማደሪያ ፍለጋ ሲንከራተቱ ቆይተው ነበር:: ወደ አንድ የእንግዶች ማደሪያ ቤት ሔደው ሲጠይቁ ቦታ የለንም ብለው ከበር መለሱአቸው:: ስለዚህ ዮሴፍና ድንግል ማርያም ያንን የእንግዶች ማደሪያ ትተው ወደ ከብቶች በረት ገሰገሱ:: በዚያ ግርግም ውስጥም የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ ተወለደ::

እስቲ ዛሬ ለከብቶቹ በረት "በጎል ሰከበ" (በበረት ተኛ) እያልን መዘመራችንን ትተን ጌታ ላልተወለደበት የእንግዶች ማደሪያ ሥፍራ ትንሽ አብረን እናልቅስለት:: በዓለማችን እጅግ ዕድለ ቢስ ስለሆነው ስለዚያ ቤት ጥቂት ሙሾ ማውረድ አማረኝ::

የዚያ ቤት ባለቤቶች ያንን ሌሊት ከደጃፋቸው የቆመችው አንዲት ልትወልድ የተቃረበች ወጣት ነበረች:: "ቦታ የለንም" ብለው ሲመልሱአት ምንም አልመሰላቸውም ትንሽ እንኳን ቅር አላላቸውም ነበር:: በማኅፀንዋ ያለው ጨለማውን ዓለም የሚያበራ ፀሐይ : የዓለምን ጥም የሚያረካ ውኃ : በደሙ ዓለምን የሚያጥብ መድኃኒት እንደሆነ አላወቁም ነበርና “ቦታ የለንም" አሉ::

እናንተ የዓለማችን ዕድለ ቢስ ሰዎች ሆይ ያቺን ምሽት ማንን ከበር እንደመለሳችሁ እስቲ እኔ ልንገራችሁ::

ከበር የቆመችው ማን እንደሆነች : በማሕፀንዋ የያዘችው ማን እንደሆነ ብታውቁ ኖሮ ቀድማችሁ ያስገባችሁዋቸውን እንግዶች ሁሉ "በሕግ አምላክ
ውጡልን" ብላችሁ ማስወጣታችሁ አይቀርም ነበርና ትሰሙ እንደሆን እኔ ልንገራችሁ:: ብታውቁአት ኖሮ እንደ ዘመድዋ ኤልሳቤጥ "የጌታችን እናት ወደ እኛ ትመጪ ዘንድ እኛ ምን ነን?" ትሉአት ነበር::

እናንተ የእንግዶች ማደሪያ ባለቤቶች ሆይ! እርግጥ ነው እናንተ ከበር የመለሳችሁት አንዲት የፀነሰች የገሊላ ናዝሬት እንግዳን ብቻ ነበር:: ለእርስዋ ቦታ የለም ብሎ መናገርም ቀላል ነገር መስሎአችሁ ሊሆን ይችላል::

እመኑኝ ለእርስዋ "አንቺን ለማሳደር ቦታ የለንም" ስትሉአት ግን ማንን እንደመለሳችሁት አላወቃችሁም:: እርግጥ ነው ቦታው በእንግዳ ተይዞአል ትሉኝ ይሆናል:: ግን ደግሞ ለመውለድ ለተቃረበች ወጣት ሥፍራ ቢጠፋ እንኳን የራስንም አልጋ ቢሆን መልቀቅ አይገባም ነበር? ለአንዲት ለምትወልድ እናት ቸርነት ማድረግ ሰብአዊ ግዴታ አይደለምን? ብታደርጉት ኖሮ የምታገኙት ከጠበቃችሁት በላይ በሆነ ነበር::

እርስዋን ብታስገቡአት ኖሮ የሰማይና ምድሩ ንጉሥ ኢየሱስ ከቤታችሁ ይገባ ነበር:: በቤታችሁ ውስጥ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል ተዘርግቶ እልፍኛችሁ በመላእክት ዝማሬ : በእረኞች ደስታ በሰብአ ሰገል ሥጦታ ይጥለቀለቅ ነበር:: እናንተ ከሞታችሁም በኁዋላ ጭምር ለዘመናት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የዓለም ሕዝብ እየመጣ የቤታችሁን ወለል ይስም : በደጃፋችሁ ይንከባለል ነበር:: አቤት ድንግል ማርያምን "ቦታ የለንም” ብሎ ከደጅ መመለስ የሚያስከፍለው ዋጋ የሚያሳጣው ጸጋ እንዴት ያለ ነው?! ምነው እንደ እናንተ በዚያ ዘመን በኖርኩና ድንግል ማርያምን ከደጄ ቆማ አግኝቻት ከአልጋዬ ወርጄ በተቀበልኩዋት!

እመኑኝ ለድንግሊቱ ማርያም ቦታ የለኝም ያለ ሰው ቦታ ያጣው ለኢየሱስ ነው:: እርስዋን ወደ ቤቱ ግቢ ያላት ሰው ግን ጌታን ወደ ቤቱ ያስገባዋል:: ጌታ ያለው ደግሞ ሁሉም አለው:: አይ እናንተዬ! ሌላ እንግዳ ከምታግበሰብሱ ለአንዲት ድንግል ቦታ ብትሠጡአት ኖሮ ቤታችሁ ሰማይ ይሆን ነበር::

የፍልስጤም ግዛት በሆነችዋ የቤተልሔም ከተማ ስመላለስና ስሳለም ብኖርም ድንግልን ከደጅ የመለሱትን ሰዎች ቤት አድራሻ እስከዛሬ ድረስ እዚህ ነው ብሎ የሚነግረኝ ሰው አላገኘሁም:: ለነገሩ ለእርስዋ ሥፍራ ያጣ ሰው ምን አድራሻ አለው? መቼም ከሞቱ ሁለት ሺህ ዓመት ያለፋቸው ቢሆንም እኔ ግን ዛሬም ድረስ ሳስባቸው ስለ ተሳሳተ ውሳኔያቸውና ዕድለ ቢስነታቸው አዝናለሁ::

ድንግሊቱን ላስጠጋውና ልጅዋን ወልዳ ላስተኛችበት በረት "በጎል በጎል ሰብዓ ሰገል" እያልኩ ስዘምርለት ባድርም ድንግሊቱን ከደጅ ቦታ የለም ብሎ ለመለሰውና ጌታ ላልተወለደበት ሥፍራ ግን ለዘላለም አዝናለሁ!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 25 2013 ዓ ም
አዲስ አበባ ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
•➢ ሼር // SHARE//SUBSCRIBE
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
@Ewkete_orthodox
@Ewkete_orthodox
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
867 views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 17:34:25 ቀናት አዲስ የሚሆኑት በእግዚአብሔር በኩል ነው

እነሆ አዳዲስ "የሚመስሉንን" ቀናት ለመጀመር አንድ ልንል ነው፡፡ በእርግጥ በጊዜ አቆጣጠር ሥርዓታችን መሠረት አዲስ ዘመን መጥቷል፡፡ ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ተሻግረናል (ተመስገን!)፡፡ እንዴት ነው ታዲያ ኑሮአችንስ? አዲስ ዓመት ላይ አዲስ ይሆናል?

አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ እቅድ፣ አዲስ አኗኗር አብሮ ይመጣል እያልን መልካም ምኞት እንሰንቃለን፤ እንደዛም እናስባለን፡፡ ግን እንደ እውነቱ ደግሞ፤ እንኳን እኛ መስከረም አንድም ለራሱ አዲስ አይደለም፡፡ እንደ ኢትየጵያ የዘመን አቆጣጠር ስሌት ሁለት ሺህ ዐሥራ አራት መስረከም አንዶች ተቆጥረዋል፡፡ ያ ማለት ፪ሺ፬ ጊዜ መስከረም አንድ ተመልሶ መጣ እንጂ፤ አዲስ መስከረም አንድ እስከ አሁን አልተገኘም፡፡

ዝምብለን ስናስተውል ዞሮ ራሱን የሚደግመው ዘመኑ ብቻ አይደለም፡፡ በክብ ዛቢያ ላይ እንደሚሽከረከር አካል ተመሳሳይ ዓመታትን በተመሳሳይ አስተሳሰብ፣ በተመሳሳይ ፍላጎት፣ በተመሳሳይ ጠባይ፣ በተመሳሳይ ማንነት ጀምረን የምንጨርስ ብዙዎች ነን፡፡ አንዳንዴ ከአምናው ዘንድሮ ምንም ያልተለወጠ ሕይወት ስለምንመራ፤ ዓለም በምትባል ሰፊ ክፍል ውስጥ ተቆልፈን የምንመላለስ እስረኞች እንደሆንን ይሰማናል፡፡

ሰዎች ዓመቱ ገና ሲጀምር የአዲስነት ስሜት በበዓል ወከባው ምክንያት ይሰማቸውና፤ የቀኑ ሽር ጉድ ሲያልፍ አዲስነቱም በዛው ያልፋል፡፡ ስለዚህ ጳጉሜ አምስት ያቋረጡትን ለቅሶ መስከረም ሁለት ይቀጥላሉ፡፡ የነሐሴ ስሕተቶች ጥቅምት ላይ ለመታየት ይዘጋጃሉ፡፡

"ሁሉን አዲስ የሚያደርገው" እግዚአብሔር ከሕይወታችን
ስፍራ ውስጥ ቦታ የሚይዝበት ዕድል ሲጠፋ፤ የኑሮ ትርጉምና እውነተኛ ጣዕምም ይጠፋል፡፡ እናም በአዲሱ ዘመን ላይ ነባር ችግሮቻችን ነባራዊ ተጨማሪ ችግሮችን እያስከተሉብን ስንባዝን ለመገኘት እንገደዳለን፡፡ (የዮሐንስ ራእይ 21፥5) እስኪ ሁላችንም ውስጣችንን፣ ቤታችንን፣ ኑሮአችንን እና ራእያችንን እንመልከተው፡፡ እውነት አዲስ ወደ መሆን የሚሄድ አይነት ነው?

በሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ቃል ሥጋ ሲሆን፤ 'ዓመት' የአባቱን ስም ከ'ፍዳ' ወደ 'ምሕረት' ቀይሮ "ዓመተ ምሕረት" ሲባል፤ እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ልኮ ሲያፈቅረን፤ እግዚአብሔር ወልድ የመለኮቱን ሚስጢር በሥጋና ደሙ በኩል ሲያካፍለን፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሕይወት ምሪት ሆኖን ሲባርከን፤ በእርግጥም ዓመተ ምሕረቶችን በስስት ብንቆጥራቸው ትክክል ነው፡፡

ሆኖም እኛ መንፈሳዊነት እንደ ወግ አጥባቂነት እየታየን፤ ለገንዘብ እና ለሥጋ ድሎት ብቻ ዘወትር እየለፋን፤ የተሰጠንን ዓመተ ምሕረት ትተን የተለወጠልንን ዓመተ ፍዳን "አዲስ ነው" እያልን እንቆጥራለን፡፡

ከሕይወት ውስጥ እግዚአብሔር እንዲገኝ ክፋት፣ ምቀኝነት፤ ስግብግብነት፣ ተንኮለኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ምቾት አሳዳጅነት፣ የሰየጠነ ዘመናዊነት ወጥተው፤ በንስሐ በኩል ያለፉ የዕለት ተዕለት አምልኮት ስግደትና የዘወትር ጸሎት ተተክተው፤ ባበላሸነው ዓመታት ውስጥ ተደላድሎ የቆየውን ክፋትና ኃይሉን የምንቃወምበት የጽደቅ ኑሮ ካልጀመርን፤ አዲስ የሚያደርገን ዓመት ገና አልመጣልንም፡፡

"እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።"

(ወደ ሮሜ ሰዎች 6፥4)

በነገራችን ላይ በእግዚአብሔር ላሉት ዘመኑ ወደ ከፍታ የሚወጣበትን ዕድሜ ጨምሯል፡፡ የቅድስተ ቅዱሳኑን መቅደስ እያየነው ነው፡፡ ከዛም ውስጥ የሚፈልቀው ውኃ እየበዛ እየበዛ ሄዶ ማንም የማይሻገረው ወንዝ ይሆናል!

መልካም አዲስ የምትሆኑበት አዲስ ዓመት
@Ewkete_orthodox
509 viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ