Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ//mergaa

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethomergaa — መረጃ//mergaa
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethomergaa — መረጃ//mergaa
የሰርጥ አድራሻ: @ethomergaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

@ethomergaa
🎩ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ፣
🎩የአስተሳሰብ ምህዳሮች ፣
🎩የምሁራን እይታዎች እና መጽሐፈቶች ፣
🎩የአለም ሙሉ መረጃ እና የታሪክ ልዩ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ 👉 @Natiyt
ኢትዮጵያዊ ሆኘ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ ያደኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ መሞት የምፈልግ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር አሜን !!!
የናንተው ቻናል ነው

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-26 20:26:03
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መግለጫ አውጥቷል።

<< …የአሸባሪው እና ተስፋፊው ቡድን ዓላማ ኢትዮጵያን ለመበተን እና መላ ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ለማባላት ቆርጦ የተነሳ ጠላት መሆኑ የታወቀ እና በሁሉም ኢትዮጵያውያን ግንዛቤ የተያዘበት ጉዳይ ቢሆንም ፣ ቡድኑን ልንዋጋው የሚገባው ገና ከመነሻው እንጅ በእያንዳንዳችን በር ላይ ሲደርስ ባለመሆኑ ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሽብር ቡድኑን እና የሽብር ቡድኑ ተከፋይ ከሆኑ ሚዲያዎች ሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ እራሱን እንዲጠብቅ እና በጀግንነት እየተዋጋ ላለው ጥምር ጦራችን እና ለጀግናው መከላከለያ ሠራዊታችን ሙሉ ድጋፉን እንዲሰጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡…>>

የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
420 viewsmenty (ßoss), 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:03
371 viewsmenty (ßoss), 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:02
358 viewsmenty (ßoss), 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:02 ሰበር መረጃ

በተኩለሽ ግንባር ሰብሮ ለማለፍ ሲውለከለክ የነበረው የህወሓት ጉጀሌ ቡድን ጀመዶ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ፣ በአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ ብርቱ ቅጣት ሰራዊቱን ካረገፈው ቡሃላ አንዱን ብ/ጀኔራላቸው ሊማረክ ችሏል።

ስሙን ማን እንደሆነ መንግስት ይፋ እስኪያደርገው ድረስ የምንጠብቅ ይሆናል !!! በዞብል እና ራማ ላይ የማጥቃት ሙከራ አድርጎ የነበረው ትህነግ በመከላከያ ሰራዊቱ አማራ ልዩ ሃይል ፋኖ እና በጀግናው የአፋር ልዩ ሃይል እና የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት ወደ መጣበት በብርቱ ግንድ ተመልሷል።
343 viewsmenty (ßoss), 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:02
በህውሃት ተንኳሽነት ከቀናት በፊት በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች አንድ የተባለው ጦርነት እየተጋጋለ እና እየተፋፋመ ሂዶ ዛሬ ላይ ደርሷል ።

በዚህም አይበገሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአሸባሪው የህውሃት ሃይል የተሰነዘረውን ጥቃት በከፍተኛ ወኔ እየመከተ እና እየተከላከለ ሃገራዊ እና ህዝባዊ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል።

ታድያ የምስራቅ አማራ ፋኖወች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከመከላከያ ጎን በመሆን ድጋፍ ለመስጠት በዘመቱበት በራያ ግንባር በራማ በኩል የወገንን ሃይል ለመቁረጥ አስቦ ተሹለክልኮ ወደ ውስጥ ገብቶ የነበረ አንድ ክፍል ጦር የህወሃት ኮማንዶ ቀለበት ውስጥ በማስገባት በጀግናው ህዝባዊ ሃይል አመድ መደረጉን ከግንባር የተገኙ መረጃወች ያስረዳሉ።

ለመሆኑ የውጊያ ታክቲክ ጠበብቶች ነን ባዮች የጁንታው ሰዎች ማታ ማታ በድሃው የትግራይ ምስኪን ወጣት ደም የተጠመቀ ውስኪያቸው ላይ በስላቅ አለማቸውን ሲቀጩ እና ሲንፈላሰሱ አምሽተው ታከቲኩን በወል ለጀሌወቻቸው ሳያሳዩ እና የጥንቃቄ መልክት ሳያስተላለፉ ረስተው ይሆን የሚል የግርምት ጥያቄን አጭሯል።

ታድያ ቀድሞ የኮማንዶው አላማ ተደብቆ ገብቶ ወገንን ከጀርባ መምታት እንደነበረ መረጃ የደረሳቸው የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ ጠላት ወደ ውስጥ አሰልፈው ከጀርባ በቆረጣ አብዛኛውን የኮማንዶ ሃይል መደምሰሳቸው ተገልጿል፤የቀሩትን የፈረጠጡ የጁንታው ታጣቂወች ከነ ነፍሳቸው በቁጥጥር ለማዋል በአካባቢው ሰፊ አሰሳ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተሰምቷል ።

ኢትዮጵያን የነካ ፤በእሳት የተጫወተ መሆኑን ለሌሎች የውች እና የሃገር ውስጥ ጠላቶች በተግባር እየታየ በመሆኑ የአሸባሪው የህውሃት ጦር እኔን ያየ ይቀጣ እያለ ይገኛል።
357 viewsmenty (ßoss), 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:51:27
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ' ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022  'የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ' ሽልማትን ማሸነፉን አስታወቀ፡፡

ግሎባል ትራቭል ማጋዚን  'ትሬዚስ አዋርድ' በተሰኘው ውድድር ድምጽ የማሰባሰብ ሂደት አየር መንገዱ አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ አግኝቷል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ  ጊዜ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም  በደንበኞቻችን ዘንድ የአፍሪካ ተመራጩ አየር መንገድ እንድንሆን ድምጻቸውን ስለሰጡን እናመሰግናለን ፤ ኩራትም ይሰማናል ብሏል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ  ጊዜ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

#EBC
419 viewsmenty (ßoss), 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:51:26
የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በ 9977 አጭር ቁጥር  ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል አስታዉቋል፡፡

#Ethio Fm
385 viewsmenty (ßoss), 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:40:42
አሸባሪው ህወሃት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

መነሻውን ከሰመራ ያደረገ ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር A47679 አይሱዙ ተሽከርካሪ መዳረሻውን ወደ አሸባሪው ህወሓት ቡድን በማድረግ 3000 /ሦስት ሺህ/ ሊትር ናፍጣ እና 2000 /ሁለት ሺህ/ ቤንዚል ካልዋን ላይ ሲደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙት መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት አሸባሪው ህወሓት በሀገራችን ላይ ጦርነት ቢከፍትም በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን አፀፋዊ ምላሽ እየተሠጠ ባለበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ለጠላት ሊደርስ የነበረን ነዳጅ መቆጣጠር ችለናል ብለዋል።

መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ አክለውም በቀጣይም ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን በህገወጥ መንገድ ሊደርስ የሚችል ማንኛውም ነገር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
360 viewsmenty (ßoss), 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:40:41
344 viewsmenty (ßoss), 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:40:41
332 viewsmenty (ßoss), 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ