2022-08-26 14:35:04
ህወሃት የመንከባለል ፖለቲካውን ሊጀምር ነው
መንግስት የሰለም አማራጭ በሚፈልግበት በዚህ ወቅት፣ ለወራት ዕድሜ ድርድር ፈላጊ መስሎ ለመታየት ጥረት ሲያደርግ ከርሞ ህወሃት ነሐሴ 18 ጦርነትን ጀምሮል። በአዲስ አመት ዋዜማ ህዝብ የሰላም ተስፋን ያአነገበበትን ጊዜ ጠብቆ ህዝብንም መንግስትንም የሚያናድድ፣ ፍፁም ሀገር ጠልነቱን የሚያረጋግጥ ተግባሩን የሰላም ፀር የሆነው ወያኔ ፈፅሞል።
በድብቅ ሲዘጋጁበት የከረሙበትን ጦርነት ሰበዓዊ ዕርዳት በሚጠይቀው ህዝባቸው ላይ መጀመር ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል እነዚህ አመራሮች ይጠፋቸዋል ማለት ይከብዳል፤ ዳሩ ግን ለህዝብ ምንም ደንታ ስለማይኖራቸ ጦርነቱን ከመጎሰም አልተቆጠቡም፤ ለእንዲህ ያለ መደንዘዝ የሚወስዱት ሃሺሺ መቼም ሳይጠቅማቸው አይቀርም።
ሰፊ ሽንፈት ሲያጋጥማቸው፣ በምዕራብውያን ጦርነትን ለምን ጀመራቹ የሚል ጫና ሲበዛባቸው ከዚህ በፊት እንዳደረጉት “ተገደን የገባንበት ነው ጀማሪ የኢትዮጵያ መንግስት ነው” የሚል ነጭ ውሸት ማወሻተቸው እንደማይቀር ይታወቃል፤ ዳሩ ህዝቡን ለርዓብ እና ለሞት የሚያጋልጠው ህወሃት ውሸት ማዝነቡን እንደ ሚያኮራ ተግባር ነው የሚቆጥረው።
አሁንም ለጀመረው ጦርነት ነጭ ውሸቱን ይዞ በመንከባለል ዘዴ ምዕራብያንን ለማባበል እንዳሰበ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እንደ ፈሪ ከጀርባ መውጋት እና ጨለማን ተገን አርጎ ተኩስ መክፈት መገለጫው የሆነው ወያኔ ዛሬ ለፈፀመው ስህተት በሀሰት መከላከያ ሰራዊት ላይ ለማለካክ ቆርጦ ተነስቶል። በሞቅታ ይሆን በዕቅድ በስሜታውነት ይሁን በትልቅ ውሳኔ ብቻ በሻቸው መንገድ የከፈቱትን ጦርነት በኢትዮጵያ መንግስት ለማሰባብ ተዘጋጅተዋል። ጦርነትን የጀመረው በድርድሩ ተስፋ ቆርጦ የመከላካያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ የሚል የሀሰት ዲስክሩ ለምዕራብውያን ለማስተጋባት በደብዳቤ እና በመግለጫ ለመጫነቃቅ የትልቅ ትንሽ ፖለቲካኞች ተነስተዋል።
ህወሃት ጦርነቱን መጀመሩን ሳር ቅጠሉ መናገር ቢችሉ ሁሉ መመስከር አያቅተውም፤ እንኳን ሁኔታውችን ማገናዘብ እና ማስታዋል የሚችል የሰው ልጅ ቀርቶ። የኢትዮጵያ መንግስት በድርድሩ ትልቅ ተስፋ እንዳለው እና ብዙ ርቀት እንደተጎዛ በተግባራቹ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡
ይህን የፈጠጠ ውሸታቸው እውነት እንዲመስል ሌት ተቀን የሚደክሙ ተካፋይ ሚዲያዎች መኖራቸው የበለጠ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል እንጂ ውሸቱን እውነት ሊያስመስለው ሁሉ አይስመስለውም። ለነደዚህ ያለ ፕሮፖጋንዳ የሚሸነፍ የኢትዮጵያ ህዝብም የለም፣ ጦርነቱን ራሳቸው መጀመራቸውን፣ ለሰላም የማይመቹ ስብስቦች እንደሆኑ ከስር መሰረቱ ህዝቡ ጠንቅቆ ያቃል። ምን ቢንከባለሉ፣ ምንም መግለጫ ደብዳቤ ቢያወጡ ውሸት እንደው ውሸት ነው መቼም እውነት ሆኖ አያቅም! መገላጡም አይቀርም፤ ስለዚህ ህወሃቶች ሞኞቹን ፈልጉ የሚታለልላቹ አታገኙም። ይልቅ ቆም ብላቹ፣ ከአንደንዛዥ ዕፅ ሀሳብ ወጥታቹ ሀስቡ።
340 viewsmenty (ßoss), 11:35