Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ//mergaa

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethomergaa — መረጃ//mergaa
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethomergaa — መረጃ//mergaa
የሰርጥ አድራሻ: @ethomergaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

@ethomergaa
🎩ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ፣
🎩የአስተሳሰብ ምህዳሮች ፣
🎩የምሁራን እይታዎች እና መጽሐፈቶች ፣
🎩የአለም ሙሉ መረጃ እና የታሪክ ልዩ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ 👉 @Natiyt
ኢትዮጵያዊ ሆኘ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ ያደኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ መሞት የምፈልግ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር አሜን !!!
የናንተው ቻናል ነው

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 18:27:38
ወልቃይት ወፍ እርግፍም ዘመቻውን ተቀላቅለዋል
411 viewsmenty (ßoss), 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:27:38
አርማጭሆ ወልቃይት ጠገዴ በየ ግንባሩ እየዘመተ ነው
422 viewsmenty (ßoss), 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:27:38 በግዳን በኩል በወራሪው ህወሓት ጉጀሌ ይዞታ ስር የነበሩ ቦታወች በሙሉ ወራሪው ወያኔ ተገርፎ በጥምር ጦሩ እጅ ስር ገብተዋል።

ጋሽ ደርቤ
449 viewsmenty (ßoss), 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:27:38
ኢትዮጵያ በምንም ተዓምር ጦርነት አሸንፋ አታውቅም በዚህ ጦርነትም ኢትዮጵያ አታሸንፍም!

ለታሪክ ይቀመጥ ከሁለት ቦታ የወለደው ልጆቹ ሲያድጉ ያዩታል:: እርግጥ ነው የመጀመሪያ ሚስቱ ልጅና ሚስቱ ያውቁታል ሚስቱም አሽቀንጥራ ሻንጣውን አሲዛ ከቤቱ አሰወጥታዋለች ከሁለተኛው ሚስቱ የወለደው ልጁ ሲያድግ ያየዋል!
466 viewsmenty (ßoss), 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:06 ይሄ ነህ ስራ ማለት ይሄ ነው ለጦሩ ደጀን መሆን ማለት

ከወልዲያ በወሬ ተሸብሮ ወደ ደሴ የመጣው ህዝብ ወደ ወልዲያ መመለስ ጀምሯል፣ ቀይ ቦኔት ለባሽ የመከላከያ ኮማንዶዎች የሚሠሩትን ሥራ እጅግ ደስ የሚል ነው::

እናሸንፋለን
453 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:06 ዳር ላይ ያለች ትንሽ ከተማ ተያዘችም፣ ትልቅ ከተማ ተያዘም ክብራችን ተነክቷል። የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ከተማ ቢያዝ ከብዙ ፋይዳ አንፃር ሊታይ ይችላል። ክብር ግን የትኛም ላይ ተመሳሳይ ነው። ከራሱ ድንበር አንድ ኢንች ሲያልፍ ተወርረናል የሚል ስሜት መኖር አለበት። ትንሽ ከተማ ሲያዝ ምንም የማይመስለን፣ ትልቅ ሲያዝ እንቅልፍ የምናጣ መሆን የለብንም። ከሩቅ ያለቦታ ሲያዝ ግድ የለሽ ወደእኛ ሲቀርብ የምንሰጋ መሆን የለብንም።

ህወሓት ወያኔ የራሱን አልፎ ከመጣ ቆይቷል። አሁን የራሳችን ከተማ የምንቆጥርበት አካሄድ መቆም አለበት። ከወረረው እስካልወጣ ድረስ የትም ይሁን የት ህመሙ እኩል መሆን አለበት። የራሳችን ከተማ እየተወረረ ዛሬ ከዚህ ደርሷል፣ ነገ ከዚህ ይደርሳል እያልን መቁጠር ለውጥ አያመጣም። ከየትኛውም እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መስራት አለብን።

የትም ደረሰ፣ የት እንደምናሸንፈው ደግሞ ጥርጥር የለውም። ባለፈው ገና ከራያ ጀምሮ ባለው ከህዝባችን ከፍተኛ ትግል ገጥሞታል። በየመንደሩ ሲያልፍ በጀግናው ህዝባችንና ሰራዊቱ በርካታ ኃይሉን እያጣ ነው ሸዋና ጎንደር ድረስ የደረሰው።

ሸዋ ደርሶ ተመትቶ ተመልሷል። ከደብረታቦር ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ከደባርቅ ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ተስፋ በቁረጡት ሳይሆን ተስፋ ባልቆረጡት ተሸንፏል። ወገናቸውን በጎነተሉት ሳይሆን በቻሉት ከወገናቸው ጋር በቆሙት አቅም ተመትቷል። ባቅማሙት ሳይሆን በቆረጡት ተመትቷል። ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ባራገቡት ሳይሆን ያለበት ድረስ ሄደን እንገጥዋለን ባሉ ክንደ ብርቱዎች ተመትቷል። ከቻልን አሁን ባለበት አስቁመን ወደመጣበት ለመሸኘት መስራት ነው። ባይቻል ደግሞ የትም ይግባ የት መሸነፉ እንደማይቀር አምነን መስራት አለብን። ደብረብርሃን ይድረስ ጎንደር፣ ላሊበላ ይድረስ ደጀን እንደምናሸንፈው ሳንጠራጠር መስራት አለብን።

እነሱ ዋሻ ገብተው ወጥተዋል። መቀሌም ይሁን አዲግራት ሲያዝባቸው ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ብዙ አጀንዳ አላደረጉትም። ሲይዙ እንጅ ሲያዝባቸው ከተማ አልቆጠሩም። ከማን ጋር እንደገጠምን ማወቅ አለብን። የራስን ከተማ መቁጠር መቆም አለበት።

ባለፈውም ዘንድሮም መወረር አልነበረብንም። ግን ሆኗል። በሆነ ጉዳይ ጉንጭ ማልፋት የለብንም። ባለፈው እንዳደረገው ዘንድሮም ከራያ ጀምሮ ሕዝባችን የቻለውን እያደረገ ነው። ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ወደፊት ሲያልፍ አጨብጭቦ አያሳልፈው፣ ባገኘው አጋጣሚ እየገጠመው ኃይሉን እያጣ ነው የሚያልፈው። የትም ይድረስ የት ተመትቶ ይመለሳል።

ባለፈውም ብለናል። ሆኗልም። እንዳትጠራጠሩ እናሸንፋለን!
447 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:05 ማሸነፋችን አይቀሬ ነው::

ድል በየጦር ግንባር ህይወታቸው እየሰጡ ላሉ የመከላክያ ሰራዊት አባልት አማራ ልዩ ሃይል ፋኖ! ሽንፈት ከህወሓት በላይ በየፌስቡኩ ህይወታቸው እየገቡሩ ባሉ የጥምር ጦሩ አባላት እያንቋሻሽና ለሚሳደቡ ለምን ሸሸ ለሚሉ ተውሳኮች!
401 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:05
ወልዲያ አደርን ጠላት በከበባ ውስጥ አድርጎ ሊበትነን ቢመኝም እስከ ቀኑ 5: :00 ሠዓት ድረስ በጀኔራል ሀሠን ከረሙ በአዋጊው ሻለቃ ሞገስ ከበደ, በደምሌ አራጋው , በወርቄ ጀግኖች እየተመራ በአማራ የወሎ ፋኖ ጦር ከመከላከያ ከልዩሀይል ጋር በመሆን ወልዲያን አላሥደፈራትም ።

በአሁኑ ሠአት በወርቄ ቂልጡ ,በአላ ውሀ, በጎብየ , በሶስት ግንባሮች ተሠልፎ እየተፋለመ ይገኛል ።
ህዝባችን በተረጋጋ መንፈስ ይጠብቅ ጦርነት የብዙ ነገሮች ውጤት ነውና !!!

አማራነት ይለምልም በምስጋን ደስዬ ከስፍራው የተጻፈ
393 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:05
352 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:14:04 ከዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ ዙሪያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል!

1ኛ. በከተማዉ ዉስጥ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 2:00 ስዓት በኃላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

2ኛ. ማንኛዉም መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 በኃላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው

3ኛ. በከተማችን ማንኛውም ተሽከርካሪ ባጃጅን ጨምሮ ከምሽቱ 12:00በ በኋላ እና ጧት ከ12:00 ስዓት በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል።

4ኛ. የከተማችን ማህበረሰብ በአደረጃጀቶቹ አካባቢውን የመጠበቅና ከፀጉረ ልውጦች እና ስርጓ ገቦች በንቃት እንዲጠብቅ ።ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካል ጥቆማ መስጠትና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል የመተባበር ግዴታዎች አስቀምጧል።

5ኛ. በከተማችን የምትገኙ አልጋ ቤቶች ፣ቤት አከራዮች እና ሆቴሎች ማንነቱ ያልታወቀ ማንነቱን በመለየት በመረጃ ፎርም ሞልቷ ማከራየት እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንድታሳውቁ።

6ኛ. የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከዳባት ዳራ እና ከዳባት ወቅን ብቻ እንድታሽከረክሩ የተወሰነ ሲሆን ከዳባት ወደ አጅሬ መስመርና ከዳራ ገደብየ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።

7ኛ. የዳባት ከተማ ፈቃድ የሌለዉ ባጃጅ ከዳባት ወደ ሌላና ከሌላ ቦታ ወደ ዳባት ማሽከርከር ተከልክሏል።

8ኛ. ለፀጥታ ስራ ከተሰማሩት ዉጭ ማንኛዉም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ በከተማ መንቀሳቀስና በመጠጥ ቤትም ሆነ ምግብ ቤቶች ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

9ኛ. ወራሪና አሸባሪዉ የህዉሓት ቡድን ከሚያሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ለህዝባችን ስነ ልቦና የማይነጥኑና ለጠላት ጉልበት የሚሆኑ ወሬዎችን ከማሰራጨት ሁሉም ህዝብ እንዲቆጠብ

10ኛ. በከተማችን ተከራይተዉ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጋር ተያይዞ ወደ ካፕ የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ከሚመለከታቸዉ አካለት ጋር ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማችን ህዝብ እንዲገነዘብ እያሳሰብን ከዚህ ጎን ለጎን ስራዎች ስለሚያስፈልጉ

ሰርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ጉዳዩ በጥንቃቄ በፀጥታ ሀይሉ እየተገመገመ የሚመራና የሚከወን ይሆናል ይህ ተግባር በጥንቃቄ ካልተመራ ለከተማችን የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽኖ ከፍ ያለ በመሆኑ ህዝባችን ጉዳዩን በእያለበት ክትትል እንዲያደርግ።

ሁሉም አከራይ ተክክለኛ ኤርትራዊ ስደተኛ መሆኑን ማረጋገጥና እንቅስቃሴዉን መከታተል የተለየ ነገር ሲመለከት ለፀጥታ መዋቅሩ እንዲጠቁም።
367 viewsmenty (ßoss), 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ