Get Mystery Box with random crypto!

የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡ የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን | መረጃ//mergaa

የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በ 9977 አጭር ቁጥር  ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል አስታዉቋል፡፡

#Ethio Fm