Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianpoem1 — ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianpoem1 — ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianpoem1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.20K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ በመድብል ደረጃ ለንባብ የበቁ እና ያልበቁ የፍቅር ፣ የሀገር ፣የትዝታ ፣ እና ሌሎች ሀገርኛ ጣዕመ ዜማ ያላቸውን ግጥሞች ያልተሠሙ ወጎች እንዲሁም የገጣሚያንና የታዋቂ ሰዎች ታሪኮችን ያገኛሉ።ግጥም ከቃላት ስደራ በላይ የእውነትና የእምነት ውጤት ፤ የምስጢር ዋሻ ነው፡፡አባላችን ይሁኑ
@ethiopianpoem1
አሰተያየት እና ግጥሞች ካሏችሁ
👉👉 @Yoyo556

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-14 21:52:07
#ሜርሲ _ሞዴሊንግ_ማሰልጠኛ_ተቋም

#ሲያሰለጥናቸዉ የቆዪትን ተማሪዎች በለዩ ሁኔታ ለሁለተኛ ዙር ነሐሴ 29/2014 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰአት በEast Gate hotel በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል በእለቱ ታዋቂ እና አንጋፋ ሞዴሎች እንዲሁም አርቲስቶች ይገኛሉ ። የተለያዩ ፋሽን ሾዎች በተመራቂ ተማሪዎች ይቀርባል ፕሮግራማችን ላይ ተገኝተው ይህን ድንቅ ምርቃት ይታደሙ ።
#መግቢያ 150 ብር ትኬቱን ለመግዛት ከፈለጉ @tomishyee ያገኙናል
467 viewsYoni Mak, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 22:41:15
897 viewsYoni Mak, 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:57:51
@Ethiopianpoem1
@yoyo556
2.8K viewsYoni Mak, 19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:56:21
@Ethiopianpoem1
@yoyo556
2.5K viewsYoni Mak, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 17:03:30 ➲➲ # ቀና_በል ➲➲

(ሜሮንጌትነት)


ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው
ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።
ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ
ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።
ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ
የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤
በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ
ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።
አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ
አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።
አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ
ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።
ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም
እንኳን ያበላኸው…..
እንኳን. ያጠጣኸው….
የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው
አለሁ ባይህ ኪስህ....
የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ
አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።
ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤
የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።
መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።

# አርቲስት_ሜሮን_ጌትነት


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@ethiopianpoem1
@yoyo556
3.3K viewsYoni Mak, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 11:30:27 ሰላም ሰላም የግጥም ወግ እና መድብል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ? የሽልማት ትንሽ ትልቅ የለውም እና
ይህን ውድድር እንዳሸንፍ በማንበብ እና ላይክ በማድረግ ለረዳችሁኝ የዚህ ቻናል ቤተ ሰቦች ከልቤ በእግዚአብሄር ስም አመሰግናችኋለሁ ።
በተጨማሪም የዚህ ታላቅ ቻናል አድሚን እንድሆን የጋበዘኝን የቻናሉ አስተዳዳሪ Yoni Mak (#yoyo556) ንም አመሰግናለሁ ።
ሰናይ እለተ ሰንበት
2.9K viewsንጉሰ ነገስት አይቫር, edited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 20:54:59 Yezih wididir ashenafi
Yosef 41
Congra @yoyo556 lay awran ena shlmatkn mekebel tichlalek.
Congra belut like like like
2.9K viewsYoni Mak, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:48:10 ሽንቁር ዕምነት

-ሁለት መንታ ሀሳብ ፣
ውስጤ ይመላለሳል -አንተ ጋር ስመጣ፣
አለም ይታየኛል
- አንዴ ዘማሪ ነኝ ፣
ሲያሻኝ ግን ዘፋኝ
-ሽንቁር ዕምነት ኖሮኝ፣
ምጨብጠው ጠፋኝ።



ሔለን አማረኝ

@ethiopianpoem1
@yoyo556
3.5K viewsYoni Mak, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:47:01 ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

ካወኩሽ በኋላ
የደስታን ምንነት ለይቼ አውቄያለሁ ፤
ከልቤ መሳቅን በ'ውነት ለምጃለሁ።
የተወሳሰበው
የህይወቴ መንገድ ግልፅ ሆኖልኛል ፤
አስሮኝ የነበረው ችግሬ ተፈቷል።
ስህተት እንዳልሰራ
አገኘሁ ያልኩትን አጥፍቼ እንዳላጣው፣
የኔ ውድ ንገሪኝ
አንቺው መልሺልኝ ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

አጠገቤ ስትሆኚ ክፋት ይርቀኛል ፤
የፍቅር ተዋጊ
የፈጣሪን መልአክ የሆንኩ ይመስለኛል።
አንቺ ስታወሪኝ
የዙርያዬ ድምፀት ፀጥታ ይሞላዋል፤
ከቃሎችሽ ውጪ
ጆሮዬ 'ሚገባ ኮሽታም ይጠፋል።
ከኔ ጋር ስትሆኚ ንፃት ይወርሰኛል፤
ራቅ ያልሽ እንደሆን ፍርሃት ያርደኛል።
የኔ ውድ ስላንቺ
ብዙ ይሰማኛል መግለጽ የማልችለው፤
እኔ እንዳልሳሳት
ራስሽ ንገሪኝ ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

ሳቅሽን ካመጣልኝ እንደይስሀቅ መሰዋት ፣
በአብርሃም መታረድ በደስታ መሞት፣
ዳዊትን ይመስል
ለብቻዬ ሆኜ እልፍ ጦር ለመግጠም፣
አንዲት እድል መሻት በጠጠር ድል ማለም፣
ልክ እንደ አምላኬ
መስቀል ተሸክሞ ቀራንዮ መውጣት፣
ባመጣሁት መስቀል
እኔው ተቸንክሬ አንድ ህይወቴን ማጣት፣
ቀላል ይመስለኛል፤
ቅጭም እንኳን ሳልል ባደርገው ያምረኛል።
እስኪ መልሺልኝ፣
እንዲህ ከተሰማኝ ፣
ልብና አንጎል ላንቺ ይሄን ካለው፣
ውዴ ምን ተሻለኝ ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

ባንቺ ስም ብጠ'ራ የኔን ስም ብሰጥሽ፣
በኮከብ አይነቶች
በአስደናቂ ስሞች ባዲስ ብሰይምሽ፣
የኔ ውድ ስልሽ ፍርሃት ባይኖረኝ፣
የኔ ፍቅር ስልሽ ያዝ ባያደርገኝ፣
ልቤን ከገላዬ
ለይቼ አውጥቼ ካንቺ ውስጥ ባኖረው፣
እኔ ተቀብሬ
ልቤ ከልብሽ ጋር አንድ ምት ቢኖረው፣
የትም ቦታ ብሆን በደስታ እሞላለው፤
ታዲያ ምን ትያለሽ ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

ለኔ ህይወት አልባው እስትንፋስ መሆንሽን፣
ጨለማ ውስጥ ለኖርኩ ብርሃን ማብራትሽን፣
ተጠምቼ ስኖር
ፍቅርን የተሞላ እንስራ ማምጣትሽን፣
በልቤ ክፍተት ውስጥ
የማይነቃነቅ ቀስት ማኖርሽን፣
አንዱንም ሳልነግርሽ ሁሉንም ሳታውቂው፣
ባጣሽ ስለማልችል
በቅድሚያ ንገሪኝ ላፍቅርሽ ወይ ልተው?

CanCazım

@ethiopianpoem1
@yoyo556
3.0K viewsYoni Mak, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 21:56:56 ውድድሩ ሊጠናቀቅ ትንሽ ቀን ቀርቶታል like like
2.5K viewsYoni Mak, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ