2022-02-24 20:46:25
(ብንያም ወጋየሁ)
...ንድፍ ወጉድፍ..
.
.
የነገዬን ንድፍ ሰራሁት : ቃሉን: ቅሉን ሰማሁት
ላይ ዛሬ:መንዝሬ : ቃኘሁት አየሁት
አሁኔ ሰጠገን ሲደገን በትላንቱ ውልቃት
ጉብታ አስለቅቆ ተባጥቆ ያገባኝ ንቃቃት
ለተስፋ አለም ነበረ ህልም ጥቃት ንቃት
ለነቂስ ቄስ ቢታወጅም
ሰው ነው እንጂ እድሜ አይጃጅም
ምን ቢጃጅም ቢደረጅም
እድሜ ሊያድም ቢዶለዱም አያረጅም
ትላንት ያልከው የከተብከው : በይበቃል ቃል የፃፍከው
ይፈርሳል
ይደርሳል ሁሉም ያልከው የካብከው
በዛሬ አምሮ ተሞሽሮ ሲደገስ ሲለገስ በቀን
እንጂ:
አይሞላም የሞላ እንጀራም : ነጥቀን ልቀን ሰቀቀን
እናም ወዳጄ የአምላክ ስጦታ ግደጄ
እንዲህ የሚል ቃል ልቀልም : ከተራመድከው ደጄ
"የነገዬን ንድፍ ሰራሁት : ቃሉን ቅሉን ሰማሁት
ላይ ዛሬ መንዝሬ : ቃኘሁት አየሁት"
የእምነት ድህነት ቃል ነው እውነት : የመታያህ ፅንፍ ገነት
ተራመድ ተላመድ ወደ እኔነት ከፍታው ላይ ከሰገነት
በትላንትህ ልድፍ ጉድፍ : ዛሬን ማሬን አታሳድፍ
አውጣ ውጣ ወደ ተስፋ ስፋ ተስፋ የነገ ንድፍ
አላለፈም ብለክ ያልከው በተራ እንደ ጎተራ ንቃቃት
ተሰንጥቆ ተወጥቆ ስስ ነፍስህን ሲያስጨንቃት
ጋሻ ባሻ ልመድ ግመድ ለከፈትከው ላልከው ጥቃት
ሩህን አታስጨንቃት ከአምላኳ አታራርቃት
ከአጥቢያ ኮከብ አታጣልቃት
ከጥጋጥግ ከልግ ከፍግ አታጣብቃት
ፍላፃ ነፃ ምርጫ ሆና ትቅና ትቃና አትጭመቃት
ል-ቀ-ቃ-ት
የሚሹት የሚያበላሹት ዘመንን የሚያመንን ትላንት ላንት
ይክሰል አመድ ስሩ ይጠመድ ዛሬን ማሬን ከሚያመክናት
ሁሉ:
በልቡ ሰሌዳ በህሊናው ጓዳ በሜዳ ሰርጓዳ ቃሌን ያቅናት
እንደኔ ትላንቴን ቅናቴን ፍቄው ንቄው ነገን ላፅናት
ተስፋ በሌለው ባለው ሙታን ሲያዝ የማዘዝ ስልጣን
ስም ልንሰይም ለእኩይ ሰብእ መስለን መጣን ያጣን ሰይጣን
በተስፋ ስፋ ነገን ቋጥር በአሉ አሉ አትጠርጥር
ዛሬህን ከትላንትህ አዛምደህ ንደህ ነገህን አታሳጥር
አታብጠርጥር
አታበጥር
ከፍጥረት ጥረት ንጠር ፍጠር አትታጠር
አ-ት-ጠ-ር-ጠ-ር
አምላክ መላክ እርከን ያልከን
ገደብ አደብ እንኩ ብለክ
አይደል ክፋት መስሎን እንጂ ይሻል"መ'ሻል"ከማለክለክ
አንዱን ማምለክ
እናም ወዳጄ የአምላክ ውላጅ ግዳጄ
እንዲህ የሚያልም ቃል ልቀልም ከተራመድከው ደጄ
"የነገዬን ንድፍ ሰራሁት ቃሉን ቅሉን ሰማሁት
ተስፋ ሁሉን ይሰፋ ዘንድ ተሰጥቷልና ለየሁት።"
(ሩህ ብሩህ)
''''''''''''''''';;;;;;;;;;;;;;;;;''''''''''''''''''';;;;;;;;;;;;;;;
@ethiopianpoem1
@yoyo556
2.6K viewsYoni Mak, 17:46