Get Mystery Box with random crypto!

አጅሬዋ ስለመጡ ህዝቡ ደስታውን አልቻለም ወገብ ማሳረፊያ አተው | ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

አጅሬዋ ስለመጡ
ህዝቡ ደስታውን አልቻለም
ወገብ ማሳረፊያ አተው
ሞልተዋል የቆሙም።
እንደ ልማዱ አስተዳዳሪው
ከመቀመጫቸው ብድግ አሉና
ወደ ጉዳያቸው ገቡ
የአክብሮት ሰላምታቸውን ሰጡና ...

"እንደምን ከረማችሁ
የተከበራችሁ ነዋሪዎቻችን
እናመሰግናለን ውድ
ጊዜያችሁን ስለሰጣችሁን።"አሉና
"አምና መንግስት ወተት
እንደሚልክ ቃሉን ሰቶ ነበረ
ግን ጥጆቹ ጡት
ገና አንለቅም ብለው ስለተቸገረ
እስኪለቁ እየጠበቀ
ወተቱን ሳይልከው ቀረ።"
ብለው ቀጠሉና
"ዛሬ ግን ህዝቤ እንኳን ደስ አላችሁ
የሚላስ ማር በቤታችሁ ላጣችሁ
ችግራችሁን አይቶ
ታዛዡ መንግስታችሁ
ቃል ገብቷል በቧንቧችሁ ሊልክላችሁ።"

ብለው ሲጨርሱ ካዳራሹ ያለው ህዝብ
በእልልታ ደባለቀው ምኑንም ሳያስብ።
በድንገት አቶ ካሴ
ብድግ አሉ እጅ ሳያወጡ
"ንቦቹስ ግን አያስቸግሯችሁም እንዴ?"
ብለው ተቀመጡ
በአሽሙር ከንፈራቸውን
ወደ ጎን እያሞጠሞጡ።
ሊቀ መንበሩም አሰብ አረጉና
አፀፋውን ሰጡ...

"ንቦቹ እንኳን ለእረፍት መቀሌ ስለገቡ
ቶሎ አይመለሱም
ለሱ እንኳን ብዙ አታስቡ።"

ብለው ሲናገሩ ሴቶቹ በእልልታ
ወጣቱ በፉጨት ህፃናት በዋይታ
አጨበጨቡላቸው ሁሉም በደስታ!!!
ከዚያም ቀጠሉና የሰፈሩ ጌታ...
"በሉ! እንደዚህ በደስታ እንደቦረቃችሁ
ቀፎ መግዣ የሚሆን
ያላችሁን እያዋጣችሁ
ወደ ቤታችሁ ሂዱ ለእኔ እየሰጣችሁ።"
ሲሉ ዋይታ እና እልልታው
በድጋሚ ተሰማ
ሁሉም ያለውን መዘዘ
ምንም ሳያቅማማ

ታዲያ እንዲህ ነው ወዳጄ
የመቀበያ ህግ
ለነገው ጥፋትህ መካሻ
ዛሬ ሰበብ ፈልግ!!!
ከማስተዋል ገዛኸኝ!!!(ማስቴ አፍሮ )


@ethiopianpoem1
@yoyo556