Get Mystery Box with random crypto!

➲➲ # ቀና_በል ➲➲ (ሜሮንጌትነት) ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው ከጎንህ ሰው አ | ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

➲➲ # ቀና_በል ➲➲

(ሜሮንጌትነት)


ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው
ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።
ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ
ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።
ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ
የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤
በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ
ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።
አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ
አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።
አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ
ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።
ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም
እንኳን ያበላኸው…..
እንኳን. ያጠጣኸው….
የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው
አለሁ ባይህ ኪስህ....
የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ
አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።
ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤
የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።
መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።

# አርቲስት_ሜሮን_ጌትነት


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@ethiopianpoem1
@yoyo556