Get Mystery Box with random crypto!

ቡናችን👆

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_coffee_sc — ቡናችን👆
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_coffee_sc — ቡናችን👆
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_coffee_sc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.79K
የሰርጥ መግለጫ

🍵ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-11 20:23:35
የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 23ተኛ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ ይህን ይመስላል።

ክለባችን ኢትዮጲያ ቡናም በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል!

ትኩረት ለ ክለባችን ኢትዮጲያ ቡና!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
2.1K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 08:01:19
እስከመቼ ግን

በኢትዮጲያ ቡና ዙሪያ ሀሳብ የምንሰጥው ግለሰብ ጠልተን አልያም የማንወደው ሰው በክለቡ ዙሪያ ስላለ አልያም የሆነ ቡድን ለማጠልሸት ወይም ስራ ለማጥላላት ወይም ስለኢትዮጲያ ቡና  ከኛ በላይ የሚያስብ ሰው የለም እያልን  አይደለም::

ስለኢትዮጲያ ቡና እድሜ ልካቸውን የሰሩለትን እና የደከሙለትን ሰዎች ክብርንም ለመንካት ወይም ስራቸውንም ለማቃለል አይደለም:: ግን ኢትዮጲያ ቡና የብዙ ሚሊዮን ደጋፊዎችን ልብ ቤተሰብ የሚነካ ብዙ ደጋፊዎች የአካልም የህይወትም መስእዋትነት የከፈሉለት ህዝባዊ ክለብ ነው ::

አሁንም በርካቶች የግልም ሆነ የቤተሰብ ህይወታቸውን ጭምር ጥለው ለቡድኑ መስውአትነት እየከፈሉ ነው ያለው !

.....ሆኖም ግን ከተመሰረተ 47 አመት የሞላው የንጋት ኮከብ  ክለባችን ትላንት ከተመሰረቱት ክለቦች እንኳን መወዳደር አቅቶት እንደዚህ ወርዶ ሲንኮታኮት ማየት በእጅጉ ያማል !!!

...የሚመለከተን አካላቶች በሙሉ በቡድን እርስ በርስ ከመበሻሸቅ ወጥተን በተከባበረ እና በሚያግባቡን ቋንቋዎች እንነጋገር ከእልህ ወጥተን ክለባችንን በሚያድን መድሀኒት እንረባርብ አለም የደረሰበትን የእግር ኳስ ሳይንስ የሚከተል ዘመናዊ እና ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ቡድን የሚከተለውን መዋቅር እንትከል እንዲሁም እንከተል!!

ኢትዮጵያ ቡና እንደዚህ ሆኖ ማየት ስለሚያመን ሁሌም እንናገራለን !!

  እትዮጲቡና መዋቅራዊ ለውጥ ያስፈልገዋል እባካችሁን እባካችሁን ራሳችሁን ፈትሹ!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
679 views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 16:53:29
ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ

     ጨዋታው ተጠናቀቀ

ኢትዮጲያ ቡና 1–3 ባህርዳር ከነማ
ማሜ 24‘       ሀብታሙ 30‘

ድል ለኢትዮጲያ ቡና

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
2.3K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 15:49:28
ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ

     የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቀቀ

ኢትዮጲያ ቡና 1–1 ባህርዳር ከነማ
ማሜ 24‘       ሀብታሙ 30‘

ድል ለኢትዮጲያ ቡና

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
1.9K viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 15:01:56 ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ

     ጨዋታው ተጀመረ

ኢትዮጲያ ቡና – ባህርዳር ከነማ
     አዳማ ሳ/ዩ  ስታድየም

ድል ለኢትዮጲያ ቡና

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
1.7K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 14:08:15
የዛሬ ጨዋታ አሰላለፍ!

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
1.8K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:45:28
የጨዋታ ቀን
            የድል ቀን

      
ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ

ዛሬ 01/09/2015    
ኢትዮጲያ ቡና ከ ባህርዳር ከነማ
           09:00 ሰዐት
   ሀዋሳ ስታድየም

ጨዋታው ከ09:00 ሰዐት ጀምሮ በቀጥታ በቻናላችን ይተላለፋል! 

የጨዋታው ውጤት ግምታችሁን ከታች ባለው ሀሳብ መስጫ አስቀምጡልን !

ድል ለተወዳጁ ክለባችን ቡንዬ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
2.0K views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:10:16 47 ዓመታትን የዘለቀ አብሮነት!!

የንጋት አብሪዋ ኮከብ ተመስሎ የተወለደው ቡና እነሆ የሀገር ኩራት የብዙሃን መሰባሰቢያ እና የደስታቸው ምስጢር ሆኖ 47ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።

እግር ኳስ ውበቱ.....  ደጋፊው የክለብ መቆሚያ ካስማ.... ታማኝ ደጋፊ የታማኝ ደጋፊዎች መገለጫ ያላቸውን ሳይሰስቱ ለሚወዱት መስጠት መሆኑን ያየነዉ በታላቁ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ነው

....የ47 ዓመቱ ጎልማሣ የሚሊዮኖች መሰባሰቢያ ዋርካ የሸገር አርማዉ የኢትዮጵያዊነት ተምሣሌት ........ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ

ለቡና መወለድ ምክንያት የሆናችሁ መከራዉን በድፍረት ተጋፍጣችሁ ለወግ ማዕረግ ያበቃችሁ የብዙ ሚሊዮኖች መሰብሰቢያ ያደረጋችሁ ባለዉለታዎች እንኳን አደረሳችሁ!! ስምና ሥራችሁ ቡና ባለበት ሁሉ ሁሌም በበጎ ይነሳል። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን መታደል አለ? እናንተ ታድላችኋል እኛ ደግሞ እጅ ነስተን በክብር እንኳን አደረሳችሁ እንላችኋለን።

በነዚህ 47 ዓመታት ዉስጥ ሚሊየኖች ለቡና ተደብድበው ታስረዉ የአካል መጉደል እንዲሁም የህይወት መስዋዕትነት ከፍለውለታል...

እናንተ በቃላት የማይገለፅ ፍቅር የለገሣችሁት ..... በዉጤት ምክንያት ያልራቃችሁ ...... ከግል ጉዳይና ኑሮ በላይ ለቡና የሚትጨነቁ በሄደበት ሁሉ ድምቀቱ እና መከታው የሆናችሁ..... በጎነትን ካለዉ ማካፈልን አብዝታችሁ ያስተማራችሁ ...... ሮጣችሁ ላባችሁ አፍስሳችሁ ለቡና መቆም ምክንያት የሆናችሁ...... የሜዳዉ ድምቀት የጥበብና የፈጠራ ባለቤቶች የኢትዮጵያ ቡናቤ ተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ!!

እግር ኳስ ዋጋ ባልተሰጠው ዘመን ጀምሮ ገንዘባችሁ በድፍረት አውጥታችሁ ስፖርታዊ አጋርነትን ፈር የቀደዳችሁ ተቋማትና ግለሰቦች አጋሮቻችን እንኳን አደረሳችሁ!! ...... ነግዳችሁ አትርፉ ..... ፍቅር ተወዳጅነት ስኬትና ከፍታ ሁሌም እንመኝላችኋለን!! ..... የምንወደውን ስለደገፋችሁ ምርጫችን ምርትና አገልግሎታችሁ ነዉ!! ...... አምባሳደራችሁ ሆነን በየሄድንበት መልካም ስማችሁ ከማስተዋወቅ አንቦዝንም!! ......ምክንያቱም ማደግ በመደጋገፍ ዉስጥ መሆኑ አብረን በቆየንባቸዉ አመታት ዉስጥ እኛም እናንተም ተገንዝበናል።

በሀገሪቱ ዘመናዊ አደረጃጀት ያለዉ በህግና በዕውቀት የሚመራ ብቁ የሠዉ ኃይል ያለዉ የራሱ ሜዳና ካምፕ ባለቤት ...... ከመጀመሪዋ ዕለት ጀምሮ ክለቡን በመምራት በትጋት በማገልገል የሚጠበቅባችሁን ብቻ ሳይሆን ያላችሁን በሙሉ በመስጠት ያገለገላችሁ አመራሮች እና ሠራተኞች የዚህ አኩሪ ታሪክ ባለቤት ናችሁና እንኳን ደስ ያላችሁ!! እንኳን አደረሳችሁ!!

በባዶ እግር በራስ ልብስ ጭምር ታላቁ ቡና እንዲታወቅ በብዙዎች እንዲወደድ ባለታሪክ እንዲሆን በታማኝነት ለክለባችን የተጫወታችሁ፣ ያስለጠናችሁ፣ ያማከራችሁ ዛሬ ልፋታችሁ መና አልቀረም...... የዘራችሁት በቅሎ በዝቷል  እንኳንም ደስ ያላችሁ!! እንኳን አደረሳችሁ!!

....በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያው ህጋዊ ደጋፊ ማህበር ባለቤት ....የኢትዮጵያ ቡና እንደ አሸዋ በዝቶ እንደ ክዋክብት ደምቆ እንዲታይ ሀሳብ ያመነጫችሁ ያስተባበራችሁ የመራችሁ በገንዘብ የደገፋችሁ ቅን የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ!!

ገና እንበዛለን..... በዛሬ ድክመታችን ውስጥ ውጤታማ ነገን እናያለን ... ሁሌም እንተጋለን!! በዝማሬ ታጅበን የታላቁ ክለባችንን ፍልሚያ ባለበት ተገኝተን እናደምቃለን .... በፍቅርና በአክብሮት አጋሮቻችንን ይዘን እንበዛለን!! ታላላቆቻችንና ባለውለታዎቻችንን እያከበርን.... ሌሎች ባለታሪኮችን እናፈራለን!! እንደ ቤተሰብ እየተወቃቀስ እና እየተመካከርን በጠንካራ መሠረት ላይ ቆመን.... በህብረት ቡናችንን እያጣጣምን ገና ብዙ ዓመታትን እንዘልቃለን!!

#ከምናልመው_ከፍታ_እና_ከምንናፍቀው_ደስታና_መዳረሻችን_ቅርብ_ነው!!

ኢትዮጲያ ቡና የሚሊዮኖች የልብ ትርታ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
2.1K viewsedited  04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:10:09
1.9K views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 20:38:21 የቡንዬ መዝሙር

አሆዬ - አሆዬ
አሆዬ - አሆዬ
ጉደሬ - ጉደሬ ጋሞ ጎፋ
ጉደሬ - ጉደሬ ጋሞ ጎፋ

አይጉደሬ ኮ -  አይዞ አይዞ
አይጉደሬ ኮ -  አይዞ አይዞ
ቡንዬ እኮ - አይዞ አይዞ
ያገባል እኮ - አይዞ አይዞ

ዋሳ ዋሳ  -  ዋሳ
ዋሳ ዋሳ  -  ዋሳ

ኤቼሬሬ - ኤቼሬሬ
ኤቼሬሬ - ኤቼሬሬ

ዋር ኢስ ዘቢቾ - ዋር ኢስ ዘቢቾ
ዋር ኢስ ዘቢቾ - ዋር ኢስ ዘቢቾ
አሂያ ማሳ ኢቼ - አሂያ ማሳ ኢቼ
አሂያ ማሳ ኢቼ - አሂያ ማሳ ኢቼ

ኦ አሻም በሞት - ኦ አሻም በሞት
ኦ አሻም በሞት - ኦ አሻም በሞት
ቡንዬ ግባ ከቤቴ - ኦ አሻም በሞት
ወያላ ውጣ ከቤቴ - ኦ አሻም በሞት

ባሊሾ ባናና - ባና ባና
ቡንዬ የኛ - የኛ የኛ የኛ
ኮፊዬ የኛ - የኛ የኛ የኛ
ቃዋዬ የኛ - የኛ የኛ የኛ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc
2.5K viewsedited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ