Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia Check

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiacheck — Ethiopia Check
ርዕሶች ከሰርጥ:
Medialiteracy
Explainer
Ethiopiacheck
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiacheck
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.08K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-17 19:02:50 #EthiopiaCheck Explainer ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ነው፤ ለዚህም ከባለፈው አመት መጨረሻ ወራት ጀምሮ እንደመጣው ቻትጂፒቲ አይነት ወይም እንደ ዲፕፌክ ያሉ የምንፈልገውን ሃሳብ እና የሰው ድምጽ የሚሰጡን መሳሪያዎች ማሳያ ናቸው።

በዚህ ዙርያ ያዘጋጀነውን ዘገባ ያንብቡ:

https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-ai-generated-images-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%b4%e1%8d%8a%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%88%88%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b5/
1.7K viewsedited  16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 10:11:38 #የሰኞመልዕክት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ከብሔር፣ ከሀይማኖት እንዲሁም ከሌሎች ሌሎች ማንነቶች አንጻር የሚሰነዘሩ የጥላቻ መልዕክቶች ከሚተላለፉባቸው ዘዴዎች መካከል ቀልዶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቀልዶች በጽሁፍ፣ በንግግር፣ በምስል፣ በቪድዮ ቅርጽ ሊቀርቡ ይችላሉ።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን የሰኞ መልዕክት ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/tips-on-how-to-counter-hate-speech-on-tiktok-%e1%89%b2%e1%8a%ad%e1%89%b6%e1%8a%ad/
2.9K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 08:46:57
ሰላም የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች፣

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
3.7K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:04:52
#EthiopiaCheck Video Explainer

Google Earth ተጠቒምና ሓደ ፎቶ ዝተወሰደሉ ቦታ ምጽራይ ይካኣል እዩ!

ኸመይ? ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዋ ነዛ ሓጻር ቪዲዮ ንርአ።

@EthiopiaCheck
2.4K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 17:35:30
#የአርብሳምንታዊዳሰሳ በዛሬው የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳችን "ትዊተር ቀደም ባሉት ጊዜያት በነጻ ሰማያዊ ባጅ የወሰዱ አካውንቶች ወደ ክፍያ ስርዐት የማይገቡ ከሆነ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ አስታውቋል" የሚሉ እና ሌሎች ጉዳዮችን እንዲሁም በሳምንቱ ያቀረብናቸውን መረጃዎች አጠናቅረን በሶስት ቋንቋዎች እንዲህ አቅርበናል።

ለአማርኛ: https://ethiopiacheck.org/home/twitter-blue-badge-subscription-and-other-friday-roundup-stories-%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8b%8a%e1%89%b0%e1%88%ad-%e1%88%b0%e1%88%9b%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%89%a3%e1%8c%85/

ለትግርኛ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/twitter-blue-badge-subscription-and-other-friday-roundup-stories-%e1%89%b5%e1%8b%8a%e1%89%b0%e1%88%ad/

ለአፋን ኦሮሞ: https://ao.ethiopiacheck.org/home/dhimma-baajii-cuquliisa-tiwiitaraa-fi-odeeffannoowwan-hordoffii-miidiyaa-jimaataa-kunneen-biroo/

@EthiopiaCheck
2.3K viewsedited  14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 13:59:59
#EthiopiaCheck Video Explainer

Google Earth በመጠቀም አንድ ምስል የተወሰደበትን ቦታ ማጣራት ይቻላል!

እንዴት? ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን ይህን አጭር ቪድዮ እንመልከት።

@EthiopiaCheck
2.8K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:35:56 #FactCheck ይዘቶቹን በዩትዩብ የሚያሰራጨው ኢትዮ 360 ሚዲያ “በአማራ፣ በአፋር፣ በሱማሌ እና በጋምቤላ እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት” በሚል ርዕስ በትናንትናው ዕለት ባቀረበው የቀጥታ ስርጭት በበርካታ ቶዮታ-ቴክኒካል ተሽከርካሪዎች የተጫኑ የፌዴራል ፖሊሶች የሚታዩበትን ፎቶ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ:

https://ethiopiacheck.org/home/image-shared-by-ethio-360-media-does-not-show-members-of-the-ethiopian-military-in-amhara-region-360-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab/
3.0K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 19:09:35
#EthiopiaCheck Monitoring በደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ "ሀሰት" ነው በማለት የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት መሰረት መንገሻ እንደገለጹት ከትላንት ጀምሮ መርዝ ተጨምሮበት ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋማቸው አንዱ ተግባሩ የሚያመርተውን ውሃ ጥራት አረጋግጦ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ሃላፊነታቸው በመሆኑን ባለሙያዎች እሁድ ቅዳሜን እና የበዓላትን ቀናት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች ታጥረው የሚጠበቁ ከመሆኑም በላይ ሁል ጊዜ በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው ውሃው በባለሙያ ጥራቱ ተረጋግጦ ለደንበኞች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል፡፡

የፀጥታ ችግር ሲከሰት ደግሞ በልዩ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡ ችግር ካጋጠመም ውሃው እንደማይለቀቅ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋሙ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በአግባቡ ተረድቶ በአሉባልታ ወሬ እንዳይረበሽ መክረዋል።

@EthiopiaCheck
350 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 20:36:44
#FactCheck የኤርትራው ፕሬዝደንት ሰጡት ተብሎ የተሰራጨ ሀሰተኛ መግለጫ።

"Wolkayt Tgedie Amhara Revolutio# ወልቃይትጠገዴ የአማራ ንቅናቄ" የሚል ስያሜ ያለው የትዊተር አካውንት በትናንትናው እለት አንድ አነጋጋሪ መረጃ አጋርቶ ነበር።

ይህ ከ5,400 በላይ ተከታታዮች ያሉት አካውንት "ታላቅ ሰበር ዜና" በሚል መረጃውን ይጀምርና "የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ የአማራ ልዩ ኃይልን መፍረስ የለበትም ሲሉ በ ERI TV መግለጫ ሰጥተዋል" የሚል መረጃ አጋርቷል።

አክሎም "በመግለጫቸው ከአማራ ልዩ ኃይልና ሕዝብ ጎን መሆናቸውንና አስፈላጊውን የሎጅስቲክ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል" ይላል ይህ አሁን ላይ 520 መውደድ (like) እና 204 መልሶ ማጋራት (retweet) የተደረገ መረጃ።

ይህን መረጃ በመውሰድ (ኮፒ በማድረግ) እንደ Dessie Press፣ Tana Media Network፣ ወሎ ሚድያ ሴንተር (WMC)፣ ፩ አማራ... ወዘተ ያሉ የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶችም መረጃውን በስፋት አጋርተዋል።

ይህን መረጃ ተንተርሶ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት የኤርትራው ፕሬዝደንት ምንም አይነት ንግግር በዚህ ዙርያ በኤርትራ ቴሌቭዥን (Eri TV) ላይም ሆነ በሌሎች ሚድያዎች እንዳላደረጉ መመልከት ችለናል።

ከዚህም በተጨማሪ በኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር፣ በቃል አቀባይ፣ በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ... ወዘተ ላይ ባደረግነው ዳሰሳ ይህ መረጃ እንደሌለ አረጋግጠናል።

በመቀጠል ኢትዮጵያ ቼክ ያናገራቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የኤርትራ ዲፕሎማት መረጃው የተሳሳተ መሆኑን በዛሬው እለት አሳውቀውናል።

ምንጫቸው ያልታወቁ መረጃዎችን ባለመቀበል እንዲሁም ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

@EthiopiaCheck
2.5K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 15:25:16
#FactCheck የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደታሰሩ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደታሰሩ የሚገልፁ መረጃዎች ከዛሬ ሚያዝያ 2/2015 ጠዋት ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያ፣ በተለይ ፌስቡክ ላይ ሲሰራጭ እንደነበር ማየት ችለናል።

እነዚህ መረጃዎች ዶ/ር ይናገር "በሙስና ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የገለፁ ሲሆን በርካታ ሰዎችም በዚህ ዙርያ አስተያየት ሲሰጡ እና መልሰው ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ይህን መረጃ በቀጥታ ዶ/ር ይናገርን በማናገር ማጣራት የቻለ ሲሆን "ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት መረጃ እንደተሰራጨ እንኳን እኔ መረጃው አልነበረኝም" በማለት መልስ ሰጥተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነቶችን መረጃ የጠየቅን ሲሆን ይህ መረጃ እንደሌላቸው ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።

ዶ/ር ይናገር ከአምስት አመት በፊት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሹመው ለ13 አመት በብሔራዊ ባንክ ገዢነት ያገለገሉትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተው ነበር። ይሁንና ጥር 2015 ላይ ዶ/ር ይናገር በአቶ ማሞ ምክረቱ ተተክተዋል።

@EthiopiaCheck
3.7K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ