Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia Check

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiacheck — Ethiopia Check
ርዕሶች ከሰርጥ:
Medialiteracy
Explainer
Ethiopiacheck
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiacheck
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.08K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-04 09:46:25
#EthiopiaCheck Video Explainer

የማህበራዊ ሚዲያ 'ቦቶች' (Social Media Bots) ምንድን ናቸው? እንዴትስ እንለያቸዋለን?

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ያዘጋጀውን አጭር ቪድዮ እንመልከት።

@EthiopiaCheck
1.3K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 09:17:05 #ErgaaWiixataa Hojii odeeffannoo qulqulleessuu fi tumsa facaatii odeeffannoo sobaa hir’isuuf taasifamu

https://ao.ethiopiacheck.org/home/hojii-odeeffannoo-qulqulleessuu-fi-tumsa-facaatii-odeeffannoo-sobaa-hirisuuf-taasifamu/
2.9K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 14:32:00 #ScamAlert ኣብ ኢንተርነት ምትላል ዝፍጽሙ ሰባት ካብ ዝዀነ ግዜ ንላዕሊ ብብዝሒ ይመጽኡ ኣለው፤ ክሪፕቶከረንሲታት ድማ ነዚኦም ዓብዪ ሓገዝ ይገብሩሎም ኣለው። ካብ ቀረባ ዓመታት ናብዚ ሸርፊ ክሪፕቶ ካብ ግዜ ናብ ግዜ ተጠላብን ተፈታውን እናዀነ መጺኡ እዩ። ጐና ጐኒ ምስ ክሪፕቶከረንሲ ብዝተሓሓዝ ዝፍጸሙ ምትላላት ቑጽሮም ይውስኽ ኣሎ።

https://tig.ethiopiacheck.org/home/coinmvscamwebsitetigrigna%e1%8a%ae%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%8a%a4%e1%88%9d%e1%89%aa/
2.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 13:08:45 #EthiopiaCheck Scam Alert የኢንተርኔት አጭበርባሪዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያደጉ መጥተዋል፣ ለዚህም ክሪፕቶከረንሲዎች ትልቅ እገዛ እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ከቅርብ አመታት ወዲህ የክሪፕቶ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል፣ ከዚህ ጎን ለጎን ከክሪፕቶ ጋር የተያያዙ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ለዛሬ ያዘጋጀውን ትንታኔ እንድታነቡ እንጋብዛለን: https://ethiopiacheck.org/home/coinmvscamwebsite%e1%8a%ae%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%8a%a4%e1%88%9d%e1%89%aa/
2.9K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 18:23:45 #FridayRoundUp በዛሬው ሳምንታዊ የአርብ ዳሰሳችን "በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የሚደረግ የማበልጸግ ስራ ገታ እንዲደረገ ደብዳቤ ተሰራጨ" የሚል እና ሌሎች መረጃዎችን አካተን እንዲሁም በሳምንቱ ያጋራናቸውን መረጃዎች አሰባስበን በሶስት ቋንቋዎች አቅርበናል።

ለአማርኛ:
https://ethiopiacheck.org/home/fridayroundups%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%88%88%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b5/

ለአፋን ኦሮሞ:
https://ao.ethiopiacheck.org/home/dhaabbatni-meta-beeksisawwan-feesbuukii-fi-inistaagiraam-irratti-maxxanfamaniif-hojimaata-haaraa-beeksise/

ለትግርኛ:
https://tig.ethiopiacheck.org/home/tigirignafridayroundupsai%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%88%88%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b5/
3.9K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:23:25
#FactCheck ከተቀረፀ ሶስት አመት ቢሞላውም ማክሰኞ በፓርላማ እንደሆነ ተደርጎ የቀረበ አሳሳች ቪድዮ።

"Iyoba" የሚል ስያሜ ያለውና ከ222 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት "የፓርላማው ጥያቄ" በሚል ርዕስ ስር መጋቢት 19/2015 ዓ.ም በተደረገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበ ነው በማለት አንድ ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል። 

በቪዲዮው ላይ አንድ ግለሰብ ሕገ-መንግስቱን፣ ብልጽግና ፓርቲን፣ መፈናቀለን ወዘተ የተመለከቱ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ይታያል።  

ሆኖም ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ቪዲዮ ከሶስት ዓመት በፊት የተቀረጸ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።  

ቪዲዮውም  የተወሰደው "ሕገ-መንግስትን እና ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራሊም ስርዐትን የማዳን መድረክ" በሚል መሪ ቃል ከሶስት ዓመት በፊት በመቐለ ከተማ በተደረገ ጉባዔ ወቅት ነበር። 

ጥያቄውን ያቀረቡት ግለሰብም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የመጡና ስማቸውም አልማዝ መሆኑም በቪዲዮው ላይ ተጠቅሷል።

ሙሉው ቪዲዮ በወቅቱ በትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የዩትዩብ ቻናል የተጋራ ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: 



በቅንብር ከሚሰሩ፣ ከአውድ ውጭ ከሚቀርቡ እና አሳሳች ከሆኑ ሌሎች ምስሎች እና ቪዲዮዎች ራሳችንን በመጠበቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

@EthiopiaCheck
4.3K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 20:49:35
#Explainer ይህ ምስል አዲስ ነው ወይስ የቆየ?

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በአንድ ላይ የሚታዩበት ይህ ምስል ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

የዚህ ምስል መሰራጨትን ተከትሎ ግን አንዳንዶች "የቆየ ምስል" ነው ብለው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ የቅርብ ግዜ እንደሆነ ለማስረዳት ሲሞክሩ አስተውለናል፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ጉዳዩን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ምስል ጉዳይ በተመለከተ መረጃዎችን አሰባስቧል።

በዚህም መሰረት ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ ሁለት ሰዎች ባገኘው መረጃ ፎቶው ከሶስት ቀናት በፊት መጋቢት 16/2015 በአዳማ ከተማ ከነበረ ፕሮግራም ላይ የተወሰደ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

ፕሮግራሙ በሰሜኑ ጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ዙርያ ክልሎች እና የፌደራል መንግስት ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና ውይይት የተደረገበት እንደነበር፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ተወካዮችም ተገኝተውበት የነበረ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

አቶ ጌታቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መጋቢት 14/2015 በጠ/ሚር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወሳል።

@EthiopiaCheck
2.8K viewsedited  17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 18:05:44
#FakeAccountAlert በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን ስምና መለያ ምልክት በመጠቀም የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን ስምና መለያ ምልክት በመጠቀም የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል አሳሳች መረጃዎችን በማጋራት ላይ መሆኑን ኤምባሲው ዛሬ አስታውቋል።

ይህ "U.S Embassy Addis Ababa" የሚል መጠሪያን የሚጠቀም የቴሌግራም ቻናል የአሜሪካ ጉዞን፣ የዲቪ ሎተሪን እንዲሁም ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን የተመለከቱ መረጃዎች የሚያጋራ ሲሆን አሁን ላይ ከ77,700 በላይ ተከታዮች አሉት።

ከላይ የተጠቀሰው የቴሌግራም ቻናል ሀሠተኛ መሆኑንና በቻናሉ የሚጋሩ መረጃዎችም ትክክለኛ አለመሆናቸውን ኤምባሲው አስታውቋል። ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለውና ኹነቶችና መርሐግብሮች የሚገለጹበት የቴሌግራም ቻናል በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ብቻ የሚገኘው መሆኑን ጨምሮ ገልጿል: https://t.me/SatchmoAmericanCenter

እንዲሁም ስራንና የድጋፍ ዕድሎችን የተመለከቱ መረጃዎች በኤምባሲው ድረ-ገጽና የትክክለኛነት ማረጋገጫ ምልክት ባላቸው የኤምባሲው የፌስቡክና የትዊተር አካውንቶች እንደሚጋሩም አስታውቋል።

ተመሳስለዉ የተከፈቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ እናድርግ።

@EthiopiaCheck
3.0K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 14:31:56 #EthiopiaCheck #FactCheck

https://ao.ethiopiacheck.org/home/odeeffannoonfinfinneefdhiyaaterajechuundhiyaatedogongora/
3.2K viewsedited  11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 12:25:03
#EthiopiaCheck Explainer

Miidiyaa hawaasaafii odeeffannoowwan dhugummaan isaanii hin mirkanoofne (conspiracy theories)!

Odeeffannoowwan dhugummaan isaanii hin mirkanoofneef akka hin saaxilamneef tarkaanfilee fudhachuu qabnu baruuf viidiyoo Itoophiyaa Cheek qopheesse kana daawwadhaa!

@EthiopiaCheck
3.2K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ