Get Mystery Box with random crypto!

#EthiopiaCheck Monitoring በደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የተሰራጨው መረ | Ethiopia Check

#EthiopiaCheck Monitoring በደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ "ሀሰት" ነው በማለት የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት መሰረት መንገሻ እንደገለጹት ከትላንት ጀምሮ መርዝ ተጨምሮበት ውሃ ተበክሏል እየተባለ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋማቸው አንዱ ተግባሩ የሚያመርተውን ውሃ ጥራት አረጋግጦ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት ሃላፊነታቸው በመሆኑን ባለሙያዎች እሁድ ቅዳሜን እና የበዓላትን ቀናት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖች ታጥረው የሚጠበቁ ከመሆኑም በላይ ሁል ጊዜ በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው ውሃው በባለሙያ ጥራቱ ተረጋግጦ ለደንበኞች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል፡፡

የፀጥታ ችግር ሲከሰት ደግሞ በልዩ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡ ችግር ካጋጠመም ውሃው እንደማይለቀቅ ጠቅሰው ህብረተሰቡ የውሃ ተቋሙ የሚያደርገውን ጥንቃቄ በአግባቡ ተረድቶ በአሉባልታ ወሬ እንዳይረበሽ መክረዋል።

@EthiopiaCheck