Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131.05K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 294

2022-05-18 11:05:56
ማነው የማያዘው?

የሚያስጎመጅ ቅናሽ ያደረግንባቸው ምግቦች:
◉ ስፔሻል በርገር - 89 ብር
◉ ቋንጣ ፍርፍር -59 ብር
◉ ቺዝ በርገር - 79 ብር
◉ ድርቆሽ - 49 ብር
◉ ቢፍ በርገር - 69 ብር

በbeU delivery ብቻ!

አሁኑኑ ይዘዙ!!!
: http://onelink.to/beudelivery16
: 9533
13.7K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 22:10:19
#ነዳጅ

"ያለፈው ሚያዚያ ወር በበዓላቱ ምክንያት ነዳጅ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ባለመጫኑ በተፈጠረ ክፍተት ጊዜያዊ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ በየማደያዎቹ የተሽከርካሪዎች ሰልፍ መስተዋሉ ተገልጿል"

ህጋዊ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማስተጓጎል ነዳጅ ለኅብረተሰቡ በወቅቱ እንዳይደርስ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ምክክር በሚኒስቴሩ ተካሂዷል፡፡

በምክክሩ ላይ አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ ከንግድ ቢሮዎች፣ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን እንዲሁም ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የተስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ያለፈው ሚያዚያ ወር የትንሳኤ በዓል እና 1443ኛው የኢድ በዓል የተከበሩበት ወቅት በመሆኑ በበዓላቱ ምክንያት ነዳጅ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ባለመጫኑ በተፈጠረ ክፍተት ጊዜያዊ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ በየማደያዎቹ የተሽከርካሪዎች ሰልፍ መስተዋሉ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ችግሮቹን በመፍታት ምርቱን ለተጠቃሚው ለማድረስ አሰራርን ከማስተካከል ጀምሮ መንግሥት ከዘረጋው የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ሂደት ውጭ በሚፈጽሙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳልም ተብሏል፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ share ያድርጉ።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
7.1K viewsedited  19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 21:08:35
#BreakingNews

የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ!!

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡
⊰━━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━━⊰
10.0K viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:42:18
መንግሥት በሕወሃት ኩባንያዎች በኢፈርት፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኡንጂነሪንግና ትራንስ ኢትዮጵያ ላይ የመሠረተው ክስ ዛሬ በችሎት ለተከሳሾቹ እንደተነበበ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ክሱ ኩባንያዎቹ ሕወሃት ፌደራል መንግሥቱን ከሥልጣን አስወግዳለሁ ብሎ የተነሳለትን ዓላማ ለማስፈጸም በከባድ ተሽከርካሪዎቻቸው ለትግራይ ወታደራዊ ዕዝ የሰው ኃይል፣ ነዳጅ፣ ጦር መሳሪያ እና ስንቅ እንዳጓጓዙ ይገልጣል። ዓቃቤ ሕግ የኩባንያዎቹን የተናጥል ወንጀሎች ጭምር ዘርዝሮ አቅርቧል።

⊰━━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━━⊰
12.4K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:39:38
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
11.5K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:39:28
በርካታ የመኪና ግብይት አማራጭ ያሉትን ይህን ቻናል ይቀላቀሉ፣ ይጎብኙ፣ ይገበያዩ!

http://T.me/EthioCarMarket
10.5K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:36:05
Double A፣ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር ተመልሷል

የ“Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ፡-
 የተለያዩ ስጦታዎችን ለምሳሌ፦ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የውሃ ማጣሪያ፣ ማይክሮዌቭ/የምግብ ማሞቂያ ማሽን፣ የጁስ መፍጫ እና የመሳሰሉትን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

የ QR ነጥብ መሰብሰቢያ ፕሮግራማችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ! ደጋግመው QR ስካን ሲያርጉ ፤ ተጨማሪ ሽልማቶችን ያገኛሉ፡፡

መተግበርያውን ለማውረድ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or

https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
10.3K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 18:47:59
በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ሥራ ገቡ!!

የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ፕሮሞሽን ባለሙያ ተስፋዬ ይመር በከተማው በክልል እና በፌዴራል ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም በባንኮችና በመሠረተ ልማት አቅራቢዎች ድጋፍ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል ብለዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል 10 የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ከክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክክር ጉባኤ በኋላ ወደ ሥራ የገቡ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 19 ሚሊየን 806 ሺሕ 957 ከ80 ዶላር ማግኘት መቻሉን ባለሙያው ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ በምርት ላይ የሚገኙት አምስት የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚሊየን 698 ሺሕ 27 ከ54 የአሜሪካ ዶላር ማስገኘታቸውን ተናግረዋል።

በግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በምርት ላይ የሚገኙ አምስት ድርጅቶች 11 ሚሊየን 108 ሺሕ 930 ከ26 የአሜሪካ ዶላር አስገኝተዋልም ብለዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
11.4K viewsedited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 16:58:47
ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ሥምምነት ፈረመ

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር (300 ሚሊዮን ዶላር) ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዶኔ ጋር ተፈራርመዋል።
የድጋፍ ሥምምነቱ በጦርነቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችና ማህበረሰብ ለመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን በአስቸኳይ ለመደግፍ ያለመ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
13.1K viewsedited  13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 16:55:32
1,040 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 40 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾች ውስጥም 303 ሴቶች ሲሆኑ 90 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ23 ሺሕ 640 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ እንደተቻለ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
12.8K viewsedited  13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ