Get Mystery Box with random crypto!

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ሥራ ገቡ!! የኢን | ETHIO-MEREJA®

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ሥራ ገቡ!!

የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ፕሮሞሽን ባለሙያ ተስፋዬ ይመር በከተማው በክልል እና በፌዴራል ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም በባንኮችና በመሠረተ ልማት አቅራቢዎች ድጋፍ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል ብለዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል 10 የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ከክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክክር ጉባኤ በኋላ ወደ ሥራ የገቡ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 19 ሚሊየን 806 ሺሕ 957 ከ80 ዶላር ማግኘት መቻሉን ባለሙያው ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ በምርት ላይ የሚገኙት አምስት የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚሊየን 698 ሺሕ 27 ከ54 የአሜሪካ ዶላር ማስገኘታቸውን ተናግረዋል።

በግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በምርት ላይ የሚገኙ አምስት ድርጅቶች 11 ሚሊየን 108 ሺሕ 930 ከ26 የአሜሪካ ዶላር አስገኝተዋልም ብለዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ