Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ሥምምነት ፈረመ ዓለም ባንክ | ETHIO-MEREJA®

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ሥምምነት ፈረመ

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር (300 ሚሊዮን ዶላር) ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዶኔ ጋር ተፈራርመዋል።
የድጋፍ ሥምምነቱ በጦርነቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችና ማህበረሰብ ለመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን በአስቸኳይ ለመደግፍ ያለመ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ