Get Mystery Box with random crypto!

1,040 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ! በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን | ETHIO-MEREJA®

1,040 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 40 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾች ውስጥም 303 ሴቶች ሲሆኑ 90 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ23 ሺሕ 640 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ እንደተቻለ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ