Get Mystery Box with random crypto!

#ነዳጅ 'ያለፈው ሚያዚያ ወር በበዓላቱ ምክንያት ነዳጅ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ባለመጫኑ | ETHIO-MEREJA®

#ነዳጅ

"ያለፈው ሚያዚያ ወር በበዓላቱ ምክንያት ነዳጅ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ባለመጫኑ በተፈጠረ ክፍተት ጊዜያዊ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ በየማደያዎቹ የተሽከርካሪዎች ሰልፍ መስተዋሉ ተገልጿል"

ህጋዊ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በማስተጓጎል ነዳጅ ለኅብረተሰቡ በወቅቱ እንዳይደርስ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ምክክር በሚኒስቴሩ ተካሂዷል፡፡

በምክክሩ ላይ አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ ከንግድ ቢሮዎች፣ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን እንዲሁም ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የተስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ያለፈው ሚያዚያ ወር የትንሳኤ በዓል እና 1443ኛው የኢድ በዓል የተከበሩበት ወቅት በመሆኑ በበዓላቱ ምክንያት ነዳጅ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ባለመጫኑ በተፈጠረ ክፍተት ጊዜያዊ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ በየማደያዎቹ የተሽከርካሪዎች ሰልፍ መስተዋሉ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ችግሮቹን በመፍታት ምርቱን ለተጠቃሚው ለማድረስ አሰራርን ከማስተካከል ጀምሮ መንግሥት ከዘረጋው የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ሂደት ውጭ በሚፈጽሙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳልም ተብሏል፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ share ያድርጉ።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ