2022-05-18 23:31:37
#ጤናመረጃብጉርን መከላከያ እና ማስለቀቂያ ዘዴዎች!ብጉር የሚከሰተው በቆዳችን የሚመነጭ ቅባት ወይንም የሞቱ ሴሎች የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎቻችን ሲደፍኑ ነው። በአብዛኛው በጉርምስና ጊዜ የሚመጣው ብጉር የሆርሞን መለወጥን ተከትሎ ነው።
ብጉርን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?*የሆርሞኖች በሰውነታችን መለዋወጥ
*መድሃኒቶች በተለይም ሆርሞኖችን የያዙ ከሆኑ
*ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም
*ጭንቀት እና የወር አበባ መምጣት ናቸው።
*በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
ብጉር እንዳይባባስ ምን እናድርግ?*ብጉር የወጣበትን ቦታ በስሱ ማጽዳት በውሃና በሳሙና መታጠብ (በቀን 2 ጊዜ)።
*ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን መጠቀምን ያስውግዱ።
*በብጉር የተጎዳ ቆዳዎን በእጅዎ አይነካኩ።
*ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በሗላ ገላዎንና ፊትዎን ይታጠቡ።
ቡጉርን በ1 ሳምንት ውስጥ የማስለቀቂያ ዘዴዎች!
1-የፈረንጅ እርሾ (baking soda)፦ የፈረንጅ እርሾ የቆዳዎን የሞቱ ሴሎች ያስወግዳል፡፡
ሁለት የሻይ ማንኪያ የፈረንጅ እርሾ ከትንሽ ውሀ ጋር አደባልቀው ይቀቡ። ከዚያም ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ይታጠቡ፡፡
2- ገብስ፦ ወዝ የበዛበትን ቆዳ በማፅዳት የሞቱ ሴሎችን ያስወግዳል፡፡
በ1 የሻይ ስኒ ዱቄቱ የበሰለ ገብስ ላይ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ና ግማሽ የሎሚ ጭማዊ መደባለቅ፣ ድብልቆቹን በቆዳ ላይ ማሸት፣ ለ30 ደቂቃ በማቆየት ለብ ባለ ውሀ መታጠብ፣ ይሄንን በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ያድርጉት
3- የሎሚ ጭማቂ፦ በሎሚ ውስጥ ያለው አሲድነት ብጉርን ለማስወገድ ጥሩ ጠቀሜታ አለው።የተቆረጠ ሎሚ ቆዳዎትን ይቀቡ ከትንሽ ደቂቃም በኋላ ይታጠቡት።
በተጠቀሱት መከላከያ መንገዶች የማይሻሻል ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ያማክሩ።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ!
T.me/ethio_mereja
2.7K views20:31