Get Mystery Box with random crypto!

ዜና እረፍት እውቁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) በተወለደ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞ | ETHIO-MEREJA®

ዜና እረፍት

እውቁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) በተወለደ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዶክሌ በሚለው ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ወንድወሰን ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት በአሜሪካ ዋሽንግተን ሜድስታር ሆስፒታል ውስጥ ማረፉን የሙያ አጋሩ አርቲስት ቴዎድሮስ ለገሰ ገልጿል።

“ዶክሌ ቅንና ታዛዥ ባለሙያ ነበረ” ያለው አርቲስት ቴዎድሮስ ኢትዮጵያውያን ኮሜዲያን ዶክሌን ሲረዳው ቢቆይም ለሁለተኛ ጊዜ ታሞ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እንዲያገኝ ቢደረግም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

በስታንድ አፕ ኮሜዲ እጅግ በርካታ አጫጭር ቁምነገር አዘል ቀልዶችን ያቀረበው ኮሜዲያን ዶክሌ በሙሉ ጊዜ የፊልም ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ዕውቅናና ዝናን ያተረፈ ነበረ።

በሥራ አጋጣሚ ከስምንት አመታት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንቶ ኑሮውን በዚያው አድርጎ የነበረው ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነበር።

ነብስ ይማር
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ