Get Mystery Box with random crypto!

'አህጉር አቋራጭ ሮኬት ሰርቼ የሀገሬን ወታደራዊ ኃይል አጠናክራለው' - ተማሪ ሳሙኤል ዘካርያስ | ETHIO-MEREJA®

"አህጉር አቋራጭ ሮኬት ሰርቼ የሀገሬን ወታደራዊ ኃይል አጠናክራለው" - ተማሪ ሳሙኤል ዘካርያስ

የ16 ዓመቱ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪ ሳሙኤል ከዋልታ ጋር በነበረው ቆይታ ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን በመስራት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሀገር ከፍ እንድትል እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡ ታዳጊው አህጉር አቋራጭ የሆነ ሮኬት ሰርቼ ሀገሬን በወታደራዊ ኃይል ጠንካራ አንድትሆን አደርጋታለው ሲል ያለውን እቅድ ገልጿል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር እንዳሉት ታዳጊ ሳሙኤል ዘካሪያስን በመቀበል በአስተዳደሩ በሚገኘው የኢትዮ-ሳይበር ታለንት ማዕከል እንዲታቀፍና የፈጠራ ሥራዎቹን ወደተሻለ ደረጃ እንዲያደርስ እገዛ እየተደረገለት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እንዲህ አይነት ትውልድ ነው ለሀገራችን የሚያስፈልጋት። ኢትዮጵያ በጠላት እንዳትደፈር ለሀገር የሚቆም፣ ለሀገሬ ብሎ የሚሰራ ትውልድ ነው የሚያስፈልገን። በርታ ወንድማችን

T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ