Get Mystery Box with random crypto!

እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የሰርጥ አድራሻ: @enes_ortodoxs_tewahedo_negen
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.22K
የሰርጥ መግለጫ

የተዋህዶ ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ
join አድርጉ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 06:49:50 https://youtube.com/channel/UC9S7fUL_4w8L3pVzqoLZI7A
1.1K views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 15:23:27 ነገ ነሀሴ 16 የእመቤታችን በአለ ትንሳኤና በአለ እርገት ነው
በስላም አደርሳችሁ አደርስን
ዐረገች በስብሐት ዐረገች በዕልልታ
በስብሐት በዕልልታ ዐረገች/2/ በዕልልታ/2
ከሙታን ተነስታ ዐረገች በዕልልታ/2
ዐረገች/2/ በዕልልታ/2
††† "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ"፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት
ግን ሁሉን ያስደንቃል ፡፡ ቅዱስ ያሬድ
††† ‹‹ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ
በቀኝህ ትቆማለች››(መዝ 44(45)፥9)
††† «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ÷ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣
የዜማም ጊዜ ደረሰ ÷ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ
ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡» (መኃ.2 ፥10-14)፡፡


✙ እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ትንሳኤና በዓለ ዕርገት በሰላም በጤና አደረሰን:: ጾማችን ፥ሱባዔያችንና ጸሎታችንን
በሰላም አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሄር ምስጋና ይግባው:: የእመቤታችን ቸርነትና አማላጅነት
ለዘለዓለሙ ከኛ ጋር ይሁን:: መልካም አወደዓመት! ✙ ✙
2.7K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:50:19 #ዕለተ_ሰንበት

ስድስት ቀን ስራ ተግባርህም ሁሉ አድርግ በሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው። እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን አርፏልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡(ዘጸ 20፦10-11)

#ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?

#ሰንበት ማለት #አቆመ፣አረፈ ማለት ነው፡፡ይህ ቀን የጌታ ዕረፍት የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡ ሰው እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ (ዘዳ 5፡14)፣(ማር 2፡38)

ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለእረፍት የተቀደሰው የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት
የተነገረው ‹‹ ያ መልካም እንደሆነ አየ››የተባለው ብቻ ነው፡፡ ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ (ዘፍ 1፡12፣ 18፡ 20፣ 25፡31) በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለ ቀዳሚት ሰንበት(ቅዳሜ) እና ሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ)

#ቀዳሚት_ሰንበት (ቅዳሜ) ጌታ ያረፈባት ለእስራኤል ዘሥጋ የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡(ዘዳ 5-2-16) በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ 3፡17) ፣ (ሕዝ 20፡12) ፣ (ዘኁ 15፡32-36) ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ (ማቴ 12፡14) ፣ (ሉቃ 4፡16)፣ በዘመነ ሐዲስ የክርስቲያኖች የቀዳሚት ሰንበት አከባበር እንደ አይሁድ ለሰው የሚከብድ እንዳይሆን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ላይ ተገልጿል፡፡

ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)

#እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10) ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡- እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፣ ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት ፣ የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያኙባት ዕለት

ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት (1ኛ ቆሮ 16፤1) ፣ የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7)
በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ (ራዕ 1፡10)

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)

መልካም ዕለተ ሰንበት
አሜን
1.7K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:03:34 ሼር ያድርጉት

# ቡሄ_ጅራፍ_ማስጮህ_ችቦ_ማብራትና
#ሙልሙል_ዳቦ
# ሐይማኖታዊ_ምስጢራቸው_ምንድነው ?
ደብረ ታቦር ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ
ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን
የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን
አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ
አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን
በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል
የሚፈጸሙ (#ቡሄ ፣ # ጅራፍ ማስጮህ፣ # ችቦ ማብራትና
#ሙልሙል_ዳቦ ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች
ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
# ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ፣
ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣
ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን
ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት
የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ
ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
# ሙልሙል_ዳቦ ሙልሙል ዳቦ
አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት
በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ
ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት
ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ
ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው
ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን
በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች
ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ
በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም
መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ
ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል
ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡
መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች
ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት
በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን
አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው
መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ
ይመሰላሉ፡፡
# ችቦ_ማብራት ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት
መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር
መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን
በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን
አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ
ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት
ብርሃን ነው፡፡
# የጅራፍ_ምሳሌነት በደብረ ታቦር በዓል
በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም
ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ
መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
# የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን
ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
# ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን
ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና
በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን
ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ በዓለ
ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና
ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን
እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ
ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ
ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ
የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም
ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት
መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ
ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡
ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና
የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል
ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን
ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ
አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም
እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው። ከበዓሉ
በረከት ያሳትፈን
።።።። # ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።
1.7K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:03:04
1.1K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:02:31 #መቁጠርያ ማለት

አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ ይጠቀሙበታል።መቁጠርያን ለፀሎት ስለተጠቀሙ መክሰስ አይገባም ያው እንደዘመኑ እንደጌጥ ከመጠቀማችን ውጭ በእጃችን በአንገታችን ከማድረጋችን ውጭ በተለይ እጃቸው ላይ መነኮሳት ናቸው ማደርጉት ። መፅሀፍ ቅዱስን ስናይ ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ በ 《1ኛ ተሰ 5፥18》 ላይ 《ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ...》ይላልና።

እንዲሁም በተለያዩ ጥቅሶች ላይ ፀሎትን አብዝተን እንድናደርግ መፅሀፍ ቅዱስ ይመክራልና። እኛ ኦርቶዶክሳውያን መቁጠርያን የምንጠቀመው

1ኛ.በትኩረትና በተመስጦ ሆነን ለመፀለይ
2ኛ.ይዘነው በመጓዝ ፀሎትን መፀለይ እንድናስታውስ
3ኛ.እንዳንፀልይ ከሚያግዱን ክፉ መንፈሶች ለማሸነፍ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙባቸው መቁጠርያዎች ባለ 《41》 ድብልብል ነገሮች 《በውስጡ 41 ድብልብል ነገሮች ያሉት》እና ባለ 《64》 ድብልብል 《በውስጡ 64 ድብልብል ነገሮች ያሉት》 ናቸው።

41 የመሆኑ ምስጢር የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን 《41》 ግርፋት《ቁስል》 ለማሰብ ሲሆን

64 የመሆኑ ምስጢር ደግሞ የእናታችን
የእመቤታች በምድር ላይ የኖረችበት እድሜ ለማሰብ
ነው።

አንዳንድ ቀሳውስትና መነኮሳት 《150,300》 ወይም ከዛም በላይ ድብልብሎች በመቁጠርያ ውስጥ ይጠቀማሉ። መቁጠሪያችን ለፀሎት እንዲያመች በ5 ፣ በ7 ፣ በ12 መከፋፈል አለበት ከዚህ በኋላ መቁጠርያ ላይ በመደጋገም
ከስር ያሉትን ፀሎቶች መፀለይ ይገባል።

እነርሱም፦

1ኛ.ጌታ በመዋዕለ ስጋው እንድንፀልይ ያስተማረን ፀሎትን እና የቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ። ይህም፦ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልዓኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ...《12 ጊዜ》

2ኛ. እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

3ኛ. በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

4ኛ. ኪርያላይሶን《41 ጊዜ》

5ኛ.ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ ሮዳስ 《5 ጊዜ》

6ኛ. ኦ! አምላክ《41 ጊዜ》

7ኛ .ኦ! ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

8. ኤሎሄ 《አምላኬ》 《41 ጊዜ¡

9.አቤቱ እንደ ምህረትህ እንጂ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን! 《12 ጊዜ》

10. አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ! 《12 ጊዜ》

11. የእመቤታችን ፀሎት 《ሰላም እለኪ》《7 ጊዜ》

ከዚህ በላይ የተጠቀሱት 11ዱ በፀሎት ጊዜ በመቁጠርያው በመደጋገም የሚፀለዩ ናቸው።

እኚህ የተለመዱ ስርዓት ወጥቶላቸው በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች ሲሆኑ ከዚህ በላይም የራስን የግል መሻት 《ጨምሮ》ጨምሮ መፀለይ ይቻላል።

ባለ ስልሳ አራቱን ድብልብሎች 《በውስጡ 64 ድብልብሎች የያዘውን》 ስንጠቀም መቁጠርያ ስንጠቀም ደግሞ 《41 ጊዜ》 ተደጋግመው የሚፀለዩትን 《64 ጊዜ》 ማድረግ
ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ 12 7 እና 5 የነበሩት እንደዛው ሆነው ይቀራሉ።

መቁጠሪያ ሲያይ የሚቅበዘበዝ ዲያብሎስ ብቻ ነው!!
እግዚአብሔር ይርዳን ፡፡
1.3K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:02:26
1.2K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 08:34:20 ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው።
.
ቅዱስ ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤
.
ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥
.
ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥
.
ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።
.
የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው።
ቅዱስ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል (ዳን.10፥13 2፥1) ውስጥ ነው፡፡
በመጽሐፈ ሄኖክም በብዙ ቦታ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡
.
ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል።» (ዳን.12፥1) በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ «ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።»(ዳን. 10፥13)
.
የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ከመከራ ነፍስ፣ከመከራ ሥጋ ያድነን ።
1.8K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 10:29:55 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው??
"""""""" """""""""""""""""""""""""""""
የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡
በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡
ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ፣ ጌሾ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡
የበዓሉ እረዴት በረከት ይደርብን
አሜን
2.0K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 10:33:38 ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)

እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
አንድም ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
አንድም የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
አንድም ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
አንድም የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሳትፈን!
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
ይቆየን ፡፡
2.3K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ