Get Mystery Box with random crypto!

እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የሰርጥ አድራሻ: @enes_ortodoxs_tewahedo_negen
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.22K
የሰርጥ መግለጫ

የተዋህዶ ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ
join አድርጉ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-11 19:38:44 #መብራት /ሻማ/ጧፍ ለምን ይበራል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብርሃን እንዲሞላ ያዛል። ለዚህም ሻማ ወይም ቀንዲል፣ ጧፍ፣ የወይራ ዘይትና ዘመናዊ መብራቶች ናቸው። ይህም የሆነበት ጥልቅ የሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ መንፈሣዊ ማሳሌነት ስላለው ነው። በዘወትር ጸሎት፣ በቅዳሴ ሰዓት፣ መጽሕፍ ቅዱስ ሲነበብ፣ በቅዱሳን ፣ሥዕሎች ፊትና በመንበሩ ላይ ይበራል።
ኦርቶዶክሳዊያን ካላቸው ጥልቅ የመንፈሣዊነት የተነሳ ብርሃን የሚሰጠውን ጥቅምና ምሳሊያዊነት በመረዳት ትልቅ ሥፍራ ይሰጡታል። ይህም አምላካዊ የሆነ ትዕዛዝ እንደሆነ በመገንዘብ ነው። “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ። እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ” (ዘፍ. 1፥3-4) ከዚህም ሌላ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የሚጠቀሙበት እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል “ ተሰብስበን በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ።” (ሐዋ. 20፥8)
ከሁሉም በላይ ቤተ ክርስቲያን በብርሃን መሞላት የሚገባው ቅዱስና ብርሃን የሆነው የአምላካችን ማደሪያ ቦታ ስለሆነ ነው። “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” (ዮሐ. 8፥12 ፣ 1፥5) “እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማ በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም” (1ኛ ዮሐ. 1፥5)
ቤተክርስቲያንም “የወርቅ መቅረዝ ተብላ ትጠራለች” ወንጌላዊው ዮሐንስ በመንፈስ ሆኖ ክርስቶስን በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል ሆኖ አየው። “ሰባቱ መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርቲያናት ናቸው።” (ራዕ. 1፥20)
በወይራ ዘይት የሚበሩ መብራቶች ምሥጢራቸው ጥልቅ ነው። በብሉይ ኪዳን ጊዜ ካህናትና ነገሥታት ሲነግሡ የሚቀቡት ዘይት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ይመስል ነበር። ለዚህም በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እንዲህ እናነባለን “ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ውስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ።” (1ኛ ሳሙ. 16፥13)
በቤተክርስቲያን የምናበራው ሻማ ከዘይት የተሰራ ነው ይህም የሚያመለክተው በመንፈስ ቅዱስ መቀባታችንንና የምሕረትን ሥራዎቹን በልባችን ውስጥ መስራቱን ነው። (1ኛ ዮሐ. 2፥20 ፣ 27) በተለይ ያለማቋረጥ የሚነደው ዘወትር ከኛ በማይለየውን ጥበቃው ልባችን ያደረገልንን ድንቅ የመንፈስ ቅዱስ ስራዎቹን እያስታወሰ እንዲገዛ ነው።
የቤተክርስቲያን ብርሃንና መብራቶች የጻድቃንንና ሰማዕታትን ይመስላሉ መሀሪ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” “ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” (ማቴ. 5፥16 ፣ ዳን. 12፥3) እንዲሁም በመቅረዝ ላይ እንዳለ መብራት ናችሁ ተብለዋል። (ማቴ. 5፥15)

ስለዚህ በጻድቃንና ሰማዕታት ሥዕል ፊት መብራት ማብራት በሥራቸውና በአንደበታቸው ብርሃናት እንደነበሩና በእግዚአብሔር ፍቅር እሳት እንደ ጧፍ ነደው ለዓለም ብርሃን መፈንጠቃቸውን ያስታውሰናል። (ማቴ. 13፥43 ፣ ዮሐ. 5፥35)

ጌታችንም አለ “ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ።” (ሉቃ. 12፥35) ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መብራትን ስናይ መብራቱ እንደበራ እንዲቆይ የታዘዘውን ትዕዛዝ ለመፈጸም መሆኑን እንረዳለን።
ወንጌል በሚነበብበት ወቅት ጧፍ የሚበራው በመንፈሳዊ ጉዟአችን የአምላካችንን ቃል የመሪነት ሥራን ሰለሚመስል ነው። “ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴ ብርሃን ነው።” (ዳዊ. 118/119/ ፥ 105) “የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ልብንም ደስ ያሰኛል፣” (ዳዊ. 19፥8)
በአጭሩ ጻድቅ የሆነው አምላክ ትእዛዝ መብራት ሁልግዜም በቤተ ክርስቲያን እንዲበራ ያዛል በዛም አኳያ የብርሃን ማብራት ሥርዓት በቤቱ ውስጥ በአግባቡ እንዲፈጸም ያስገነዝባል ብርሃንን ያለማብራትና በሥርዓትም ያለማከናወን ጽኑ የሆነ ቅጣትን አንደሚያስከትል ያሳያል። (2ኛ ዜና 29፥6-8)
1.2K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:59:03
1.3K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 09:52:19

1.4K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 09:49:24
1.3K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:25:32 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ማለት_ምን_ማለት_ነው?~
አብቡት ሼርሼር አርጉት
1. ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
2. ተዋህዶ የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
3. ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

1. ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው ትርጉሙ እውነተኛ ፣ ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት ማለት ነው።
ቀጥተኛ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ። [ ኤር 6፥16]
ነቢዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ ሐይማኖት ማለት ነው።

""ኢየሱስ ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት ሕይወት ነኝ ብሏል። [ዮሐንስ 14፥16]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታችሁ እኔ ነኝ ማለቱ ነው።
ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን
ወንድሞች
ሆይ የሐይማኖታችንን ሊቀ ካህን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ። [ዕብራውያን 3፥1 ]
#ሰለዚህ_ኦርቶዶክስ_ማለት_ይህ_ነው።

2. ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው?

" ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ሥጋ አንድ ሆነ ማለት ነው። ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ
ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው።

" ይህም ደግሞ ግልጽ የሆነ እውነት ነው።
በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። [ዮሐንስ 1፥1] ቃልም ስጋ ሆነ፤ ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። [ዮሐንስ 1፥14]
#ሰለዚህ_ተዋህዶ_ስንል_ቃል_ሥጋ_ለበሰ_ማለታችን_ነው።

" በበለጠ ደግሞ ብርሃናዊው የሆነ የዓለም ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቃል በቃል ተዋህዶ የሚለው ጽፎልናል።
ክርስቶስ እርሱ ሰላማችን ተውና ፥ ሁለቱን ያዋሀደ
በአዋጅ
የተነገረለት በራሱ አዲስ ሰውን ይፈጥር ዘንድ ሰላምም አደረገ። [ኤፌሶን 2፥14-15]
#ሰለዚህ_ተዋህዶ_ማለትም_ይህን_ይመስላል።

3. ክርስቲያን የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?

" ክርስቲያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን ክርስቶስ ተከታዮች ፤ አማኞች ማለት ነው።
ክርስቶስ አምላክ ነው ፤ ጌታ ነው፤ ፈጣሪ ነው፤ ፈራጅ ነው፤ ብለን የምናምን ክርስቲያን ተብለን እንጠራለን።
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን ተባሉ። [ሐዋርያት 11፥26]

" በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ ፤ ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን። [1ኛ.ጢሞ 3፥16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ሰለዚህ
ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
[ 1ኛ.ጴጥሮስ 4፥16]
#ሰለዚህ_ሁሉም_ከመጽሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_የተነሳ_ነው።

" ኦርቶዶክስ ነው ሐይማኖቴ ስንል ቀጥተኛ ናት ሃይማኖታችን እያልን ነው።
=> የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን እያልን ነው።
=> ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ የምናምን ክርስቲያን ነን። ማለታችን ነው።

@ ሌላው እምነት ሐይማኖት ግን ጴንጤ፣ ፕሮቴስታንት ፣ ካቶሊክ ፣ ጆባዊስትን ክርስቲያነን ቢሉም እነዚን የመሳሰሉ ግን። ከጥንትም ያልነበረ ስም አዲስ ድርጅት ነው በመጽሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ ላይ የለም።
ከጊዜ በኋላ ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ምንፍቅና የተመሩ ድርጅቶች ናቸው።

+ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ከጥንት የነበረች የነቢያት የሃዋርያት የቅዱሳን ሰማእታት ሃይማኖት ናት።
1.5K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 16:25:59

1.2K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:59:34 ልደታማርያም የልደትሽ ዕለት ልደታችን ነው!!!!
ማርያም ሆይ እንወድሻለን እውነተኛ የህይወት ምግብ እና እውነተኛውን የህይወት መጠጥ ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደሽልናልና እናከብርሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን!!!!
(በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ ...)
እመቤቴ ማርያም ሆይ ስለልጅሽ ስለቀራንዮ ንጉስ አልፋና ኦሜጋ ብለሽ አስራት ሀገርሽን ጠብቂልን ሰላሙን አውርጅልን በምልጃ በፀሎትሽ አትለይን
የጌታዬ እናት እናቴ እመቤቴ ልደታ ማርያም ሆይ የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው!
የእመቤታችን ቅድስት ልደታ ማርያም ወዳጆች እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ምልጃና ጸሎቷ እረድኤት በረከቷ የእናትነት ፍቅሯ ይብዛልን አሜን!
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለው
ማርያም ብዬ መች እወድቃለው
የምፅናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና
አዝማች"""""""""""
ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያቢሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የአለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶች እርስት ከሀገር ወጥቼ
በአሕዛብ ሀገር ስኖር ተሽጬ
ደርሰሽ አፅናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ
አዝማች።።።።።።።።።
ድንኩዋኑ ሞልቶ ሰው ታድሞ
አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
ምን አቀርባለው ብዬ ስቸገር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ያሰብኩት ሀሳብ ደመና ሆኖ
ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀርም
በእማምላክ እኔስ ተስፍም አልቆርጥም
አዝማች።።።።።።።።።።
እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይቺ አለም ንቃ ገፍታ ብታየኝ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለው
አውሎንፍሱን ባህሩን አልፍለው
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያሰቃየኝ
አላቁዋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝ ገና
አዝማች።።።።።።።።።
ክፍዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ
አንቺን መውደዴን አያስተውኝ
በአሕዛብ መሀል ስምሽን ስጠራ
መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝ
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝ
አልአቁዋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝ ገና
በእለተ ቀንሽ እናቴ ሆይ ሰላሙን አውርጅልን ምልጃ ፀሎትሽ አይለየን
የተዋህዶ መረጃዎች እንዲደርሶ የቴሌግራም አካውንታች ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀላሉ
https://telegram.me/enes_ortodoxs_tewahedo_negen
1.4K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:33:28 # ቅዱስ__ባለ_ወልድ
ባለ ወልድ ማለት ወር በገባ በ 29 ኛው ቀን የሚከበር በአል ነው።
ይህም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስና ነጭ፣ጥቁር፣ ህንፃ ሳይል የሰውን ልጅ ነፃ ለማውጣት ሲል ከእናታችን ከድንግል ማርያም
የተወለደበትን ቅዱስ እለት የምናስብበት ቀን ነው።
# እግዚአብሔር_ሲናገር__ ,,,,,,,,,,,ሙት ይነሳል
# እግዚአብሔር_ሲናገር__ ,,,,,,,,,,,,ዳዊ ይፈወሳል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,ጎባጣ ይቀናል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,,ሸባ ይተረተራል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,ዲዳ ይሰማል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,እውር ያያል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,የታሰረ ይፈታል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,ያዘነ ይደስታል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,ያለቀሰ በሳቅ ይሞላል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,ሰላም ያጣ ሰላም ያገኛል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,ጠማማ ይስተካከላል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,,ባህር ይከፈላል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,,ዲያብሎስ ድል ይሆናል
# እግዚአብሔር_ሲናገር_ ,,,,,,,,,,,,,,,ሁሉ መልካም ይሆናል
# ክብር_ምስጋና_አምልኮት_ውዳሴ_ለእርሱ_ይሁን_አሜን
1.6K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:05:26

1.3K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 18:39:00 የመጥምቁ ወዳጅ ሁሉ ሼር ያድርግ Share
በመጀመሪያ ከነገ ወዲያ በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበረው አመታዊ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ። ስለ ሸንኮራ ፀበል ትንሽ ልበላችሁ።
ታላቁ የሸንኮራ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከመዲናችን አዲስ አበባ ደቡብ ምሥራቅ144 ኪ.ሜ. ከባህርዳር 701 ኪ.ሜ. ከደብረ ብረሃን 274 ኪ.ሜ ከአረርቲ 11 ኪ.ሜ ከባልጪ ከተማ 2.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በጨሬቻ ቀበሌ ዉስጥ ይገኛል፡፡ ፅላቱ ለ30 አመታት በዋሻ ከቆየ በኋላ በ1620 ዓ.ም አሁን በሚገኝበት ቦታ እንደተተከለ ታሪክ ያስረዳል፡፡
ፀበሉ በፈዋሽነቱ የሚታወቀዉ የሸንኮራ ዮሐንስ ለአይን የሚማርክ ዉብ ተፈጥሮ አዊ ገፅታ ያለዉ ሲሆን በየአመቱ ሰኔ 30 በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡
# ቅዱስ_ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: # ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
" # ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት # ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 (75) የዘካርያስ ደግሞ 100 (90) ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተእርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ : ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ
# የአርያም_ንግሥት # ድንግል_እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው # መንፈስ_ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና : ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ (ሰኔ 30) ተወልዶ : አባቱ ዘካርያስ " # ዮሐንስ " ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
" መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ "
√ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
√ በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
√ በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
√ እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
√ የጌታችንን መንገድ የጠረገ
√ ጌታውን ያጠመቀና
√ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
•ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን•
# ነቢይ :
# ሐዋርያ :
# ሰማዕት :
# ጻድቅ :
# ገዳማዊ :
# መጥምቀ_መለኮት :
# ጸያሔ_ፍኖት :
# ቃለ_ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::
የቅዱስ ዬሐንስ ረድኤት በረከቱ ምልጃው በያለንበት
ይድረሰን አሜን
ዝማሬውን ደሞ

1.9K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ