Get Mystery Box with random crypto!

እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ enes_ortodoxs_tewahedo_negen — እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
የሰርጥ አድራሻ: @enes_ortodoxs_tewahedo_negen
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.22K
የሰርጥ መግለጫ

የተዋህዶ ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ
join አድርጉ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-12 18:49:21 ሥሉስ ቅዱስን ያለማጉደል ያለመጠራጠር እናምናለን፣የአብርሃምና የሳራን ቤት በበረከት የጉብኙ ስላሴዎች የኛንም ጎደሎ ህይወታችንን በበረከት ይጎብኙን ይባርኩን።
2.1K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:59:21 ስማኝ ልጄ

1.ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!

እግዚአብሔር አምላክ መልካሙን አዊዋቂዎች ያድርገን
2.3K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:45:45 ሰማእትነትን ከ ቅድስት አርሴማ እንማር
ሰማእትነት ስር ነው ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚህ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡
ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡
የሰማእቷ ቅድስት አርሴማን ፅናት ለኛም ያድለን
1.7K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:39:35 #ይህን_ያውቁ_ኖሯል?

አሐዱ ተብሎ ቅዳሴ ከተገባ በኃላ (በቅዳሴ ሰአት)፡-
- ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር፣
- ቅዳሴ አቋርጦ መውጣት
- የግል ፀሎት ማድረግ፣
- የጸሎት መጽሐፍትን ማንበብ፣
- ሳቅ፣ ወሬ፣
- ሞባይል ማስጮህና ማነጋገር
- ምግብ ይዞ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
- ወደ አውደ ምህረት አካባቢ መጠጋት
- እህቶች ሱሪ አድርገው መምጣት እንዲሁም ፀጉርን በሚገባ ሳይከናነቡ ለቅዳሴ ጸሎት መቆም
- ልጆችን ያለ ነጠላ ማቁረብ
- ቅዱስ ቁርባን በሚሰጥበት ግዜ ስነ-ስርአቱን በቪዲዮ፣ ፎቶ ካሜራ እና በሞባይል መቅረጽና ማንሳት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን
- በተጨማሪ ህፃናትን ማቁረብ ሲያስቡ በተቻለ መጠን ካህናት ቅዳሴ ከመግባታቸው በፊት ይዘዋቸው ወደ ቤተ-መቅደስ ቢደርሱ መልካም ነውና ዘወትር ይህንን ተግባራዊ ያድርጉ።

#ለሰው_ሳይሆን_ለጌታ_እንደምታደርጉ፤
#የምታደርጉትን_ሁሉ_በትጋት_አድርጉ።
1.6K views04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 19:08:57 †††ቅድስት አርሴማ ሆይ ፦†††
††† ሰላም ለመልክዕኪ ፤
ደመና ዝሙት የሸፈነው የወንጀለኛ ንጉስ ልብን በገደለ መልክሽ
ሠላም ይገባል ።
አርሴማ ሆይ ቅዱስ በሚሆን መስቀል ምልክት አድኝኝ ወደ ምሥጋናና ወደ ደስታ የፍቅርሽ
ገመድ ልቤን
ስቦታልና ።
ሰላም ለጸአተ ነፍስኪ ፤
ወደ አዘነበለ አንገትሽ በሚያልፍ ሰይፍ ጊዜ ለነፍስሽ መውጣት
ሰላምታ ይገባል።አርሴማ ሆይ መስዋዕትን በሚቀበል ጌታሽ
ዘንድ የተረፈ ረድኤትሽ በእኔ ላይ ይወርድ ዘንድ በከንፈርና በአፍ
እለምንሻለሁ ።የተቆጠሩ ሞትሽ ይሄን ነገር አሳይቶኛል ።
††† ሰላም ለበድነ ስጋኪ ፤
ጨረቃን ለመሰለ ለስጋሽ በድን ሠላምታ ይገባል ።
በምሥጋና
ወገንተኞች መላዕክት እጅ ለተቀደሰ መገነዝሽም ሠላምታ
ይገባል ።
ቅድስት አርሴማ ሆይ ከጥልቅ ጥፋት ወደ ውሥጥ ከግብፅ
ከተማ ጠላቶችን በምስጋና ቃልኪዳንሽና ሙሴ ሀይልሽ ያሠጥማቸው ዘንድ
ሠላምታ ይገባል ።
††† ሰላም ለመቃብርኪ ፤
ከሰማዕታት ጋር ካረፍሽበት አርማንያ ቦታ ለመቃብርሽ
ሠላምታ ይገባል ። በአርያምና በምሳሌ ከተናገርኩት ክብርሽ የተነሳ የሸንገላ እጅ ያልዳሰሰሽ የመነኮሳት ዕቃ አርሴማ ሆይ
ከከንፈርና አፍ
ምሥጋናን ይጥገቡ ።
††† ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ፤
በፈጣሪ ቃል ለተመሰገነ ለሥጋሽ መፍለስ
ሠላምታ ይገባል ። የዚህ አለም ኑሮንም ላልፈለገ ሥጋሽ
ሠላምታ ይገባል ። ብጽዕት
አርሴማ ሆይ
ችግርን እንዳላይ ከበረከተ ዕቃሽ መግቢያ ማረስን አልችልምና ጥቂት በረከትን ትሰጭኝ ዘንድ እለምንሻለሁ ።
††† ሰላም ለዘአእረፋ ምስሌኪ ፤
ከአንች ጋር ለአረፉ ለሀያ ሰባቱ ሰማዕታት
ሠላምታ ይገባል ።
ከብዙ ይቅርታ ጋር እና ቅድሥት ከምትሆን ሥምሽም ጋር ሥማቸው ወደ አለበት ቦታ ረድኤታቸው በእኔ ላይ
ትወርድ ዘንድ አርሴማ ሆይ በሁሉ ዘመንና በሁሉ አመታት
የሞትና የህማም በሽታ ዳግመኛ አይቅረብ ።
የቅድሥት አርሴማ አምላክ ሆይ ከነፍስና ከሥጋ መከራ አድነን ጠብቀንም ለዘላለሙ አሜን ፫
1.9K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 16:26:34

1.8K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 10:05:58
እንካን አደረሳችሁ
#በአታ_ማርያም
ባጭሩ የበአታ ማርያም ታሪክ
“እበውዕ ቤተከ ምስለ መባእየ” ፤ “ከመባዬ ጋራ ወደ ቤትህ እገባለሁ።” መዝ. ፷፭(፷፮)፥፲፫

እመቤታችን አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ። በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ ወልደዋታል። የብፅዓት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ።

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መጥቅዕ መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ አለ። ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ። ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ። መልአኩ ወደ ላይ ራቀበት። የእርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለእኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ። ራቀበት። ካህናቱም ሕዝቡም በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው። ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት። ትታት እልፍ አለች።

ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ። የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ እንጁ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት። “ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ዐሠርተ ወክልዔተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት” ይላል። ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት እየጎበኟት ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች።

የእናታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን፤ ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን፤ ከበዓሏ በረከትም ያሳትፈን። የዓመት ሰው ይበለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
2.5K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:43:12 ለሱባኤያችን የተመረጡ የእመቤታችን ዝማሬዎች


3.0K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:21:30 ሀምሌ 7
እንኳን ለፈጣሪያችን ለቅድስት ስላሴ አመታዊ በአል በሠላም አደረሠን ።
☞በዚችም ቀን ልዩየሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የይስሐቅንም ልደት አበሠሩት ባረኩት አከበሩትም፡፡መጽሐፈ ስንክሳር ዘሐምሌ ሰባትሥላሴ ማለት በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንዳለ ለአበው ለነቢያትና ለሐዋርያት መገለጡን አምነን የምንማረው ትምህርት ነው፡፡ሥላሴ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስት፤ ሦስትነት ማለት ነው፡፡የአንድ አምላክ በሦስትነት መገለጥን ለመረዳት በኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 ላይ በተገለጠው መሠረት “እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌችን እንፍጠር” ይላል ይህ አገላለጽ “እግዚአብሔርም አለ” ሲል አንድነትን (አንድነታቸውን) “እንፍጠር” ሲል ከአንድ በላይ (ሦስትነትን) መሆንን ያስረዳል፡፡በኦሪት ዘፍጥረት 3፡22 ላይ “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለው አገላለጽ ከአንድ በላይ መሆንን የሚያስረዳ ነው፡፡በኦሪት ዘፍጥረት 11፡5-7 የተጠቀሰው “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቅ”በማለት ሥላሴ የተናገሩት ከአንድ በላይ (ሦስትነት) መሆንን የሚያመለክት ነው፡፡በኦሪት ዘፍጥረት18 ላይ ሥላሴ ለአብርሃም እንደተገጹለት የሚያስረዳ ሀሳብ የያዘ አገላለጽ ሲሆን ሥላሴ ለአብርሃም በመገለጻቸው አብርሃም ሥላሴን በእንግድነት አሰተናግዷል፡፡የሥላሴ ባለሟል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በእርግናው ጊዜ ልጅ እንደሚያገን ተበስሮለታል፡፡ ዘሩ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ እንደሚበዛ በሥላሴ ቃል ተገብቶለታል፡፡አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠመቅበት ጊዜም የሥላሴ ምስጢር ተገልጧል፡፡ “እግዚአብሔር አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል እግዚአብሔር ወልድ ሲመጠቅ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ማቴ.3፡13 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን ሂዱና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀመዛሙርቴ አድርጉ” ማቴ. 14፡28 ሲል ሦስትነት የሚገልጽ መልእክት አስተላልፏል፡፡ እንግዲህ ሥላሴ ስንል በስም በአካል፣ በግብር የተለዩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ይኸውም፡-የአካል ሦስትነት፡-አብ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡ወልድ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡መንፈስ ቅዱስ፡- የራሱ መልክ፣ ገጽ አካል አለው፡፡የስም ሦስትነት ስንል፡- የአንዱ ስም ለአንዱ የማይሆን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በመባል ይጠራሉ፡፡የግብር ሦስትነት ስንል፡- አብ ወላዲ፣ አስራጺ ሲሆን ወልድ ተወላዲ ነው የተወለደውም ከአብ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነው፡፡ የሰረጸውም ከአብ ነው፡፡የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡በዓለ ሥላሴበዓላት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተደረገለትን የቸርነት ሥራ በማሰብ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎና ተአምራት በመስማትና በማሰማት የተደረገውን ድንቅ ነገር በመዘከር በደስታ የሚከበሩ ዕለታት ናቸው፡፡ “በቃለ አሜን ወበትፍስሕት ድምፁ እለ ይገብሩ በዓለ፡- በዓለ የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና የምስጋና ቃልአለው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ.41፡5 የበዓል መከበርን ያሳወቁት ሥላሴ ሲሆኑ፤ ሥላሴ ፍጥረታትን ስድስት ቀናት ፈጥረው ሰባተኛውን ቀን ቀዳሚትን አርፈውበታል፡፡ “በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ፡፡ እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባርከውም ቀድሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፏልና” ዘፍ.1፡1-3 እንዲልበዚህ መሠረትነት በዓል እንዲከበር የመደቡት ሥላሴ ሲሆኑ የመጀመሪያው የሥላሴ መታሰቢያና የበዓል አከባበር መጀመሪያ የሆነችው ቀዳሚት ናት፡፡
☞የዛሬው ሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ አብርሃምን የባረኩትና ልጅ እንደሚወልድ፣ መጻዒው ሕይወቱን የነገሩት ዕለት ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ቸርነታቸው፣ ፍቅራቸው፣ ትድግናቸው እንዳይለየን እንማጸናለን፡፡ የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን፡፡
844 views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:30:56 #የቅዳሴ ጠበል«ጸበል»ለማን

1_የቅዳሴ ጠበል መጠጣት ለማን ይፈቀዳል?
2_የቅዳሴ ጠበል ከማየ ገቦ ይለያል?
ጥያቄ፡-የቅዳሴ ጠበል ሁሉም ምዕመን መጠጣት ይችላልን? ምክንያቱም አንዳንዶች የቆረበ ሰውና ደዌ ሕመም ያለበት ሰው ብቻ ነው መጠጣት ያለበት ሲሉ ሌሎች ደግሞ ቅዳሴ የገባ ሰው ሁሉ ባይቆርብም መጠጣት ይችላል ይላሉ ፡፡

ለመሆኑ የትኛው ነው ትክክል ;
• መልስ ፡- በቅድስት ቤተክርስቲያን ጠበልን በአራት ዓይነት መልክ እናገኛለን

1. ማየ ገቦ 《ልጅነት የምናገኝበት ጥምቀት》
2. ማየ ጸሎት ፡- በጸሎት የተቀደሰ ውኃ ሲሆን ካህናት በቤታችን የሚረጩን ፣ ካህናትና ምዕመናን ውኃ አድርገው ጸሎት ካደረሱ በኋላ ‹‹ እፍ ›› በማለት የሚያከብሩት የጠበል ዓይነት ነው ፡፡ በግብሩ በፊታችን በቤታችን . . . በመረጨቱ ማየ ምንዛኅ 《የሚረጭ ውኃ》 ተብሎ ይጠራል
3. በገዳማትና በአድባራት ዐጸድና ሰበካ በቅዱሳን ስም የሚፈልቅ ጠበል
4. የቅዳሴ ጠበል ፡- በጸሎተ ቅዳሴ የከበረ ፣ ከሌሎች ጠበላት ሁሉ የተለየ ጠበል ነው ፡፡ በመሆኑም ሥጋወ ወደሙ ከመቀበል ጋር በቅዳሴ ጠበል ዙሪያ የቀረቡልንን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲህ እናቀርባለን ፡፡

የቅዳሴ ጠበል አገልግሎት ሥጋውን ደሙን ለተቀበሉ ምዕመናን በአፋቸው ተጣብቆ ቀርቶ ወደ ውጭ እንዳይነጥብ ለማድረግ ነው ፡፡ ስለዚህም የተቀበሉ ሰዎች ቅዳሴ ጠበል እንዲጠጡ ይታደላቸዋል ፡፡
በተጨማሪም በተለያየ ምክንያት ሥጋወ ወደሙ
መቀበል ያልተቻላቸው ሰዎች ቢኖሩ ሌሎች ሲቀበሉ ብቻ እያዩ እዳይመለሱ ንስሓ ገብተው ቀኖናቸውን ጨርሰው ሥጋወ ደሙን እስኪቀበሉ ድረስ ተስፋ እንዳይቆርጡ ቅዳሴ ጠበል ከደዌ ሥጋ እየተፈወሱ እዲቆዩ ለሥጋወ ወደሙ መቅድም እንዲሆናቸው የቅዳሴ ጠበል እንዲጠጡ ይቀዳላቸዋል ፡፡

የቅዳሴ ጠበል የሚጠጡት በ3 ዓይነት ወገን ከፍለን ብናይ

1. ሥጋውን ደሙን ለተቀበሉ
2. በደዌ ለተያዙ ሰዎች
3. ሥጋወ ወደሙ ለመቀበል ላልበቁ ነገር ግን በጸሎት ቅዳሴው ተሳታፊ ለነበሩት ሁሉ የሚጠቅም ነው ፡፡

ይሁን እንጂ ሁሉም ቅዳሴ ጠበል የሚጠጡበት ዓላማና የሚያገኙት ጥቅም የተለያየ ነው

የቅዳሴ ጠበል ከማየ ገቦ ይለያል?

አንዳንድ ሰዎች ቅዳሴ ጠበልን ከማየ ገቦ ጋር አንድ አድርገው ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ የቅዳሴ ጠበል ክብር ከማየ ገቦ ጋር አንድ እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡

በመሠረቱ ሁለቱም አስተሳሰቦች ፈጽመው የተሳሳቱ ናቸው ፡፡ ምክንያቱም ማየ ገቦ በዕለተ ዓርብ
ሌንጊኖስ የተባለ ሐራዊ የጌታን ቀኝ ጎን በጦር ሲወጋው
በ‹‹ለ›› (ሐ) ፊደል ቅርጽ ከደም ጋር የወረደ ውኃ ነው ፡፡

ማየ ገቦ ማለትም ‹‹ የጎን ውኃ ›› ማለት ነው ፡፡ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ማየ ገቦ ልጅነት የምናገኝበት ፣ መዝገበ ውሉድ የተባለች አማናዊት ጥምቀት አንዲት ናት አትከለስም አትደገምም የቅዳሴ ጠበል ግን ይደገማል በተጨማሪም የቅዳሴ ጠበል ማየ ገቦ አይባልም የምንለውም የልጅነት ጸጋ ስለማያሰጠን ነው ፡፡

የቅዳሴ ጠበል ማየ ገቦ ቢሆንማ ከቅዳሴ
በተለየ ጸሎት ለሕፃናት ሀብተወልድና ስመ ክርስትና ለመስጠት መጽሐፈ ክርስትናን መድገሙ ሥርዓተ ጥምቀት መፈጸሙ ባላስፈለገ ነበር ፡፡

አንድ ነው የሚሉት ወገኖች ምክንያታቸው
በሥርዓተ ቅዳሴ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመለወጥ ካህኑ የሚለውን ኣሓዱ ኣብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ እንሚለው ሁሉ ልጅነት ሃብት የምናኝበት የክርስትና ጥምቀትንም ለመፈጸም መጽሐፈ ክርስትናን አድርሰው ውኃውን ወደ ማየ ገቦ ለመለወጥ ካህኑ የሚለውን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ አንድ በማድረግ ነው ይህ ግን ስህተት ነው ሁለቱም ቃሉ
አንድ ይሁን እንጂ ከኋላቸው ያለው ጸሎት የተለያየ ስለሆነ አገልግሎቱም የተለያየ ነው ፡፡

አለበለዚያማ በየዓመቱ በ《ጥር 11 ቀን》 የጥምቀት በዓል ሲከበር ውኃውን ለመባረክ የሚደርሰው ጸሎት አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ
ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ስለተባለ ብቻ ጠበሉ ወደ ማየ ገቦነት ተለውጧል ካልን ቤተክርስቲያን ልጅቿን የልጅት ጥምቀት ታጠምቃለች ወደሚለው የተሳሳተ ድምዳሜ እንደርሳለን ፡፡

በ《ኤፌ 4፡5 》ጥምቀት አንዲት ናት ከሚለው
ትምህርተ ሃይማኖት ጋር የሚጋጭ ሃሳብ እናነሳለን ፡፡
ነገር ግን የቅዳሴ ጠበል የአምልኮት ማዕከል የሆነው ጸሎተ ቅዳሴ የደረሰበት በመሆኑ ልጅነትን ከምናገኝበት ከማየ ገቦ ጠበል ውጪ ከላይ ከዘረዘርናቸው ከሌሎች ጠበላት በእጅጉ የከበረ ነው ፡፡

ስለዚህ ጠበሉን መሬት ላይ ማፍሰስ በየቤታችን
ጥግ መድፋት ፈጽሞ የተከለከለ ነው ፡፡ ይቆየን
1.4K views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ