Get Mystery Box with random crypto!

#መቁጠርያ ማለት አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ | እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

#መቁጠርያ ማለት

አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ ይጠቀሙበታል።መቁጠርያን ለፀሎት ስለተጠቀሙ መክሰስ አይገባም ያው እንደዘመኑ እንደጌጥ ከመጠቀማችን ውጭ በእጃችን በአንገታችን ከማድረጋችን ውጭ በተለይ እጃቸው ላይ መነኮሳት ናቸው ማደርጉት ። መፅሀፍ ቅዱስን ስናይ ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ በ 《1ኛ ተሰ 5፥18》 ላይ 《ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ...》ይላልና።

እንዲሁም በተለያዩ ጥቅሶች ላይ ፀሎትን አብዝተን እንድናደርግ መፅሀፍ ቅዱስ ይመክራልና። እኛ ኦርቶዶክሳውያን መቁጠርያን የምንጠቀመው

1ኛ.በትኩረትና በተመስጦ ሆነን ለመፀለይ
2ኛ.ይዘነው በመጓዝ ፀሎትን መፀለይ እንድናስታውስ
3ኛ.እንዳንፀልይ ከሚያግዱን ክፉ መንፈሶች ለማሸነፍ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙባቸው መቁጠርያዎች ባለ 《41》 ድብልብል ነገሮች 《በውስጡ 41 ድብልብል ነገሮች ያሉት》እና ባለ 《64》 ድብልብል 《በውስጡ 64 ድብልብል ነገሮች ያሉት》 ናቸው።

41 የመሆኑ ምስጢር የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን 《41》 ግርፋት《ቁስል》 ለማሰብ ሲሆን

64 የመሆኑ ምስጢር ደግሞ የእናታችን
የእመቤታች በምድር ላይ የኖረችበት እድሜ ለማሰብ
ነው።

አንዳንድ ቀሳውስትና መነኮሳት 《150,300》 ወይም ከዛም በላይ ድብልብሎች በመቁጠርያ ውስጥ ይጠቀማሉ። መቁጠሪያችን ለፀሎት እንዲያመች በ5 ፣ በ7 ፣ በ12 መከፋፈል አለበት ከዚህ በኋላ መቁጠርያ ላይ በመደጋገም
ከስር ያሉትን ፀሎቶች መፀለይ ይገባል።

እነርሱም፦

1ኛ.ጌታ በመዋዕለ ስጋው እንድንፀልይ ያስተማረን ፀሎትን እና የቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ። ይህም፦ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልዓኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ...《12 ጊዜ》

2ኛ. እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

3ኛ. በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

4ኛ. ኪርያላይሶን《41 ጊዜ》

5ኛ.ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ ሮዳስ 《5 ጊዜ》

6ኛ. ኦ! አምላክ《41 ጊዜ》

7ኛ .ኦ! ክርስቶስ 《41 ጊዜ》

8. ኤሎሄ 《አምላኬ》 《41 ጊዜ¡

9.አቤቱ እንደ ምህረትህ እንጂ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን! 《12 ጊዜ》

10. አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ! 《12 ጊዜ》

11. የእመቤታችን ፀሎት 《ሰላም እለኪ》《7 ጊዜ》

ከዚህ በላይ የተጠቀሱት 11ዱ በፀሎት ጊዜ በመቁጠርያው በመደጋገም የሚፀለዩ ናቸው።

እኚህ የተለመዱ ስርዓት ወጥቶላቸው በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች ሲሆኑ ከዚህ በላይም የራስን የግል መሻት 《ጨምሮ》ጨምሮ መፀለይ ይቻላል።

ባለ ስልሳ አራቱን ድብልብሎች 《በውስጡ 64 ድብልብሎች የያዘውን》 ስንጠቀም መቁጠርያ ስንጠቀም ደግሞ 《41 ጊዜ》 ተደጋግመው የሚፀለዩትን 《64 ጊዜ》 ማድረግ
ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ 12 7 እና 5 የነበሩት እንደዛው ሆነው ይቀራሉ።

መቁጠሪያ ሲያይ የሚቅበዘበዝ ዲያብሎስ ብቻ ነው!!
እግዚአብሔር ይርዳን ፡፡