Get Mystery Box with random crypto!

ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። . ቅዱስ | እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው።
.
ቅዱስ ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤
.
ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥
.
ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥
.
ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።
.
የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው።
ቅዱስ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል (ዳን.10፥13 2፥1) ውስጥ ነው፡፡
በመጽሐፈ ሄኖክም በብዙ ቦታ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡
.
ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል።» (ዳን.12፥1) በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ «ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።»(ዳን. 10፥13)
.
የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ከመከራ ነፍስ፣ከመከራ ሥጋ ያድነን ።