Get Mystery Box with random crypto!

ሼር ያድርጉት # ቡሄ_ጅራፍ_ማስጮህ_ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ # ሐይማኖታዊ_ምስጢራቸው_ምንድነ | እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ሼር ያድርጉት

# ቡሄ_ጅራፍ_ማስጮህ_ችቦ_ማብራትና
#ሙልሙል_ዳቦ
# ሐይማኖታዊ_ምስጢራቸው_ምንድነው ?
ደብረ ታቦር ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ
ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን
የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን
አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ
አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን
በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል
የሚፈጸሙ (#ቡሄ ፣ # ጅራፍ ማስጮህ፣ # ችቦ ማብራትና
#ሙልሙል_ዳቦ ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች
ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
# ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ፣
ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣
ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን
ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት
የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ
ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
# ሙልሙል_ዳቦ ሙልሙል ዳቦ
አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት
በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ
ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት
ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ
ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው
ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን
በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች
ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ
በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም
መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ
ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል
ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡
መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች
ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት
በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን
አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው
መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ
ይመሰላሉ፡፡
# ችቦ_ማብራት ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት
መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር
መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን
በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን
አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ
ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት
ብርሃን ነው፡፡
# የጅራፍ_ምሳሌነት በደብረ ታቦር በዓል
በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም
ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ
መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
# የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን
ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
# ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን
ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና
በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን
ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ በዓለ
ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና
ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን
እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ
ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ
ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ
የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም
ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት
መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ
ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡
ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና
የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል
ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን
ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ
አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም
እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው። ከበዓሉ
በረከት ያሳትፈን
።።።። # ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።