Get Mystery Box with random crypto!

ነገ ነሀሴ 16 የእመቤታችን በአለ ትንሳኤና በአለ እርገት ነው በስላም አደርሳችሁ አደርስን ዐረ | እኔስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ

ነገ ነሀሴ 16 የእመቤታችን በአለ ትንሳኤና በአለ እርገት ነው
በስላም አደርሳችሁ አደርስን
ዐረገች በስብሐት ዐረገች በዕልልታ
በስብሐት በዕልልታ ዐረገች/2/ በዕልልታ/2
ከሙታን ተነስታ ዐረገች በዕልልታ/2
ዐረገች/2/ በዕልልታ/2
††† "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ"፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት
ግን ሁሉን ያስደንቃል ፡፡ ቅዱስ ያሬድ
††† ‹‹ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ
በቀኝህ ትቆማለች››(መዝ 44(45)፥9)
††† «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ÷ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣
የዜማም ጊዜ ደረሰ ÷ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ
ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡» (መኃ.2 ፥10-14)፡፡


✙ እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ትንሳኤና በዓለ ዕርገት በሰላም በጤና አደረሰን:: ጾማችን ፥ሱባዔያችንና ጸሎታችንን
በሰላም አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሄር ምስጋና ይግባው:: የእመቤታችን ቸርነትና አማላጅነት
ለዘለዓለሙ ከኛ ጋር ይሁን:: መልካም አወደዓመት! ✙ ✙