Get Mystery Box with random crypto!

እንደወረደ ®✔

የቴሌግራም ቻናል አርማ endewerede1 — እንደወረደ ®✔
የቴሌግራም ቻናል አርማ endewerede1 — እንደወረደ ®✔
የሰርጥ አድራሻ: @endewerede1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.71K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-23 09:52:59
የማመልከቻ ቀኑ የተራዘመ ማስታወቂያ

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጠይቃለን

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር



ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች
@endewerede1
2.6K viewsedited  06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 20:16:32
በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የጸጥታ ችግር አጋጥሞ በነበረባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በ43ቱ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ187 ሺ በላይ ተማሪዎች ይገባሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው በእርማት ወቅት የነበሩ ስህተቶችን በወቅቱ አስተካክለናል፡ የሚሻሻል የነገር የለም ብለዋል።

@endewerede1
2.3K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 01:51:54 ማስታወቂያ
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንድታደርጉ እንጠይቃለን
1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።


ትምህርት ሚኒስቴር

@endewerede1
1.9K viewsedited  22:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 06:05:26
#Update

በዚህ አመት 152ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን እንደሚቀላቀሉ ተገለፀ።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152ሺ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287ሺ 223 ናቸው ።

የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።


            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@endewerede1
╚═══════════╝
1.7K viewsedited  03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:06:02
#MoE

የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦

#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች !

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351

• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300

• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254

• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250

• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250

• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250

(የ2ኛው ዙር ተፈታኞች የመቁረጫ ነጥብ ሙሉ መረጃ ከላይ በምስሉ ተያይዟል ያንብቡ)



ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች
@endewerede1
@endewerede1
1.6K viewsedited  15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 19:49:37
ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ከተጠቀመች ኔቶ ወደ ጦርነቱ ሊገባ እንደሚችል የፖላንድ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአሁኑ ሰዓት የትኛውንም ነገር ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የፖላንድ ፕሬዝዳንት አስታወቁ። ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ቭላድሚር ፑቲን “የኬሚካል ጦር መሳሪያን ይጠቀማሉ ወይ” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። የፖላንዱ መሪም፤ የሩሲያው አቻቸው በዚህ ከባድ ጊዜ የትኛውንም ነገር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የሰው ልጅ የኬሚካል ጦር መሳሪያን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አይቶት እንደማያውቅ ያነሱት ፕሬዝዳንት ዱዳ፤ ፑቲን ግን ይህንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገምተዋል። ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ የምትጠቀም ከሆነ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወደ ጦርነቱ አልገባም ያለውን ጉዳይ ሊያጤነው እንደሚችል ተናግረዋል።

ኬሚካል ጦር መሳሪያን ሞስኮ ከተጠቀመች ኔቶ ወደ ጦርነቱ ሊገባ የሚችልበት ዕድል የተፋጠነ ሊሆን እንደሚችል የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው ፖላንድ መሪ ጠቁመዋል።“የምትጠይቁኝ ፑቲን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ይጠቀማሉ ወይ ብላችሁ ከሆነ፣ እኔ እንደማስበው አሁን ላይ ፑቲን ሁሉንም ነገር ሊጠቀሙ ይችላሉ፣ በተለይ በዚህ ከባድ ጊዜ” ሲሉ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፖለቲካ“ተሸንፈዋል፤ በወታደራዊ መስክም እያሸነፉ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያን ከተጠቀመች ሁሉም ነገር ይቀያየራል ብለዋል። ይህ ደግሞ ኔቶችን በጠረንጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ እንዲወያይ እንደሚያደርገው ገልጸው ኬሚካል ጦር መሳሪያ ለአውሮፓ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም አደገኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

@endewerede1
1.4K viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 20:58:45
የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ። ትናንት አንደኛ ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው ዛሬ ባካሄደው ምርጫ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል።

@endewerede1
1.3K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 15:23:21
በሁለት ወር ተራዝሟል !

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላለፉት 6 ወራት ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ሲሰሩ ነበር።

በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የ2 ወር ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የባንክ ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከወዲሁ ወደ ባንክ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

#CBE

@endewerede1
1.4K viewsedited  12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 15:22:09
1.3K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 15:04:01
ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዘይት ጉዳይ አስተያየት ሰጥተው ነበር ?

በኢትዮጵያ ባለው የዘይት እጥረትና የዋጋ ውድነት ምክንያት ነዋሪዎች ክፉኛ ተማረዋል። በዚህም አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈለግና ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከምግብ ዘይት ውድነትና መጥፋት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለጉዳዩ ዜጎች ብዙ እያሉ ነው። የዘይት መጥፋቱን፣ ህዝቡን እያማረረ ያለውን የኑሮ ውድነት መቀለጃ ያደረጉ አንዳንድ ሰዎችም አልጠፉም።

ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ግን የሀገሪቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል የተባለው ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት ተሰራጭቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ የእርሻ ቦታ ላይ ሆነው ለምግብነት የሚውል ቦለቄ እያሳዩ "...እኛ በምግብ ራሳችንን አልቻልንም እንላለን ግን ደግሞ #ዘይቱን፣ በርካታ ሽንኩርት፣ ቅቤ ጨማምረን የመመገብ ስርዓታችን በጤናችን ብቻ ሳይሆን ዋጋን ከፍ አድርጎታል።...1 ኪሎ ይሄን ገዝቶ ሶስት አራት ሰው እራት ሊያበላ ይችላል ፤ ለጤናውም ጥሩ ነው ውሃ ብቻ ይበቃዋል" እያሉ ሲናገሩ ይደመጣል።

ይኸው ንግግር ነው ለሰሞኑ የዘይት ዋጋ ውድነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ ተናግሩ እየተባለ እየተሰራጨ የሚገኘው።

ነገር ግን ይህ ንግግርና ቪድዮ ከዛሬ 4 ወር በፊት የተሰራጨ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ሆነ #በአርሲ_ዞን የመስክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተናገሩት ነው።

በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት በአርሶ አደሮች የለማውን የ #ቦለቄ ምርት ከጎበኙ በኃላ ለሚዲያዎች የሰጡት አስተያየት አሁን ላይ ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ጠቅለይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ የተናገሩት መልዕክት ተብሎ እየተሰራጨ ነው።

የዘይት ጉዳይ ግን ህዝብን ማማረሩን የቀጠለ ሲሆን መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ ጥሪ እየቀረበ ነው።

@endewerede1
1.3K viewsedited  12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ