Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ከተጠቀመች ኔቶ ወደ ጦርነቱ ሊገባ እንደሚችል የፖላንድ ፕሬዝዳንት አሳ | እንደወረደ ®✔

ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ከተጠቀመች ኔቶ ወደ ጦርነቱ ሊገባ እንደሚችል የፖላንድ ፕሬዝዳንት አሳሰቡ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአሁኑ ሰዓት የትኛውንም ነገር ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የፖላንድ ፕሬዝዳንት አስታወቁ። ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ቭላድሚር ፑቲን “የኬሚካል ጦር መሳሪያን ይጠቀማሉ ወይ” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። የፖላንዱ መሪም፤ የሩሲያው አቻቸው በዚህ ከባድ ጊዜ የትኛውንም ነገር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የሰው ልጅ የኬሚካል ጦር መሳሪያን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አይቶት እንደማያውቅ ያነሱት ፕሬዝዳንት ዱዳ፤ ፑቲን ግን ይህንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገምተዋል። ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ የምትጠቀም ከሆነ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወደ ጦርነቱ አልገባም ያለውን ጉዳይ ሊያጤነው እንደሚችል ተናግረዋል።

ኬሚካል ጦር መሳሪያን ሞስኮ ከተጠቀመች ኔቶ ወደ ጦርነቱ ሊገባ የሚችልበት ዕድል የተፋጠነ ሊሆን እንደሚችል የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው ፖላንድ መሪ ጠቁመዋል።“የምትጠይቁኝ ፑቲን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ይጠቀማሉ ወይ ብላችሁ ከሆነ፣ እኔ እንደማስበው አሁን ላይ ፑቲን ሁሉንም ነገር ሊጠቀሙ ይችላሉ፣ በተለይ በዚህ ከባድ ጊዜ” ሲሉ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፖለቲካ“ተሸንፈዋል፤ በወታደራዊ መስክም እያሸነፉ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሳሪያን ከተጠቀመች ሁሉም ነገር ይቀያየራል ብለዋል። ይህ ደግሞ ኔቶችን በጠረንጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ እንዲወያይ እንደሚያደርገው ገልጸው ኬሚካል ጦር መሳሪያ ለአውሮፓ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም አደገኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

@endewerede1