Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዘይት ጉዳይ አስተያየት ሰጥተው ነበር ? በኢትዮጵያ ባለው የዘይት | እንደወረደ ®✔

ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዘይት ጉዳይ አስተያየት ሰጥተው ነበር ?

በኢትዮጵያ ባለው የዘይት እጥረትና የዋጋ ውድነት ምክንያት ነዋሪዎች ክፉኛ ተማረዋል። በዚህም አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈለግና ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከምግብ ዘይት ውድነትና መጥፋት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለጉዳዩ ዜጎች ብዙ እያሉ ነው። የዘይት መጥፋቱን፣ ህዝቡን እያማረረ ያለውን የኑሮ ውድነት መቀለጃ ያደረጉ አንዳንድ ሰዎችም አልጠፉም።

ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ግን የሀገሪቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል የተባለው ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት ተሰራጭቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ የእርሻ ቦታ ላይ ሆነው ለምግብነት የሚውል ቦለቄ እያሳዩ "...እኛ በምግብ ራሳችንን አልቻልንም እንላለን ግን ደግሞ #ዘይቱን፣ በርካታ ሽንኩርት፣ ቅቤ ጨማምረን የመመገብ ስርዓታችን በጤናችን ብቻ ሳይሆን ዋጋን ከፍ አድርጎታል።...1 ኪሎ ይሄን ገዝቶ ሶስት አራት ሰው እራት ሊያበላ ይችላል ፤ ለጤናውም ጥሩ ነው ውሃ ብቻ ይበቃዋል" እያሉ ሲናገሩ ይደመጣል።

ይኸው ንግግር ነው ለሰሞኑ የዘይት ዋጋ ውድነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ ተናግሩ እየተባለ እየተሰራጨ የሚገኘው።

ነገር ግን ይህ ንግግርና ቪድዮ ከዛሬ 4 ወር በፊት የተሰራጨ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ሆነ #በአርሲ_ዞን የመስክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተናገሩት ነው።

በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት በአርሶ አደሮች የለማውን የ #ቦለቄ ምርት ከጎበኙ በኃላ ለሚዲያዎች የሰጡት አስተያየት አሁን ላይ ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ጠቅለይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ የተናገሩት መልዕክት ተብሎ እየተሰራጨ ነው።

የዘይት ጉዳይ ግን ህዝብን ማማረሩን የቀጠለ ሲሆን መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ ጥሪ እየቀረበ ነው።

@endewerede1