Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በ | እንደወረደ ®✔

ማስታወቂያ
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንድታደርጉ እንጠይቃለን
1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።


ትምህርት ሚኒስቴር

@endewerede1